የአፍሪካ ሳምንት በፎቶ

በሳምንቱ ውስጥ ከአፍሪካና በመላው ለም ከሚገኙ አፍሪካውያን የተመረጡ ፎቶዎች

በደቡብ አፍሪካዋ ከተማ ኬፕታውን ባህር ዳርቻ አካባቢ አንድ ፔንግዊን ኮራ ብሎ ይታያል። Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ በደቡብ አፍሪካዋ ከተማ ኬፕታውን ባህር ዳርቻ አካባቢ አንድ ፔንግዊን ኮራ ብሎ ይታያል።
በደቡብ አፍሪካዊ ግዛት በረሃማ ክፍል ካሮ በምትባለው ከተማ ጊዜያዊ ቤቶች አሰራር ላይ የሚያተኩረው የአፍሪካበርን ፌስቲቫል ላይ ቢራ እየጠጣ የሚዝናና ሰው። Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ በደቡብ አፍሪካዊ ግዛት በረሃማ ክፍል ካሮ በምትባለው ከተማ ጊዜያዊ ቤቶች አሰራር ላይ የሚያተኩረው የአፍሪካበርን ፌስቲቫል ላይ ቢራ እየጠጣ የሚዝናና ሰው።
በዚህ አመታዊ ፌስቲቫል ወደ 13 ሺ ሰዎች የተገኙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አንዱ ከአጥንት የተሰራ ጭምብል ለብሶ ነበር። Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ በዚህ አመታዊ ፌስቲቫል ወደ 13 ሺ ሰዎች የተገኙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አንዱ ከአጥንት የተሰራ ጭምብል ለብሶ ነበር።
ይህ ፌስቲቫል ራስን ሙሉ በሙሉ መግለፅ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ ገንዘብ፣ የስልክ ግንኙነትም ሆነ የንግድ ዕቃዎች የሉም። Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ይህ ፌስቲቫል ራስን ሙሉ በሙሉ መግለፅ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ ገንዘብ፣ የስልክ ግንኙነትም ሆነ የንግድ ዕቃዎች የሉም።
ከፌስቲቫሉ በተለየ መልኩ ይህ ግለሰብ ደግሞ በኬፕታውን በወር 43 ብር በሰዓት የሚከፈለው የደመወዝ ጣራ እንዲሻሻል የተጠራው የተቃዋሚ ሰልፍ አካል ነው። Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ከፌስቲቫሉ በተለየ መልኩ ይህ ግለሰብ ደግሞ በኬፕታውን በወር 43 ብር በሰዓት የሚከፈለው የደመወዝ ጣራ እንዲሻሻል የተጠራው የተቃዋሚ ሰልፍ አካል ነው።
ስዋዚላንዳውያን በሰንደቅ ዓላማ ቀለም በተሽቆጠቆጠ ልብስ አሸብርቀው አምሳኛ አመት የነፃነት ቀናቸውንና የንጉሳቸውን ምስዋቲ አምሳኛ አመት እንዲህ እያከበሩ ነው። Image copyright Taiwan presidential office
አጭር የምስል መግለጫ ስዋዚላንዳውያን በሰንደቅ ዓላማ ቀለም በተሽቆጠቆጠ ልብስ አሸብርቀው አምሳኛ አመት የነፃነት ቀናቸውንና የንጉሳቸውን ምስዋቲ አምሳኛ አመት እንዲህ እያከበሩ ነው።
እነዚህም ልጆች በሰንደቅ አላማ ተሽቆጥቁጠው የክብረ-በዓሉ አካል ነበሩ። Image copyright Taiwan presidential office
አጭር የምስል መግለጫ እነዚህም ልጆች በሰንደቅ አላማ ተሽቆጥቁጠው የክብረ-በዓሉ አካል ነበሩ።
ንጉስ ምስዋቲ ለልደታቸው የተዘጋጀውን ኬክ በሚቆርሱበት ወቅት የታይዋን ፕሬዚዳንት ሳይ ኢንግ ዌንም አብረዋቸው ነበሩ። Image copyright Taiwan presidential office
አጭር የምስል መግለጫ ንጉስ ምስዋቲ ለልደታቸው የተዘጋጀውን ኬክ በሚቆርሱበት ወቅት የታይዋን ፕሬዚዳንት ሳይ ኢንግ ዌንም አብረዋቸው ነበሩ።
እነዚህ ሴቶች ደግሞ 24ኛውን ዓመት የሩዋንዳ ዘር ጭፍጨፋን ለማስታወስ በዩጋንዳ ውስጥ አበባ አስቀምጠዋል። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ እነዚህ ሴቶች ደግሞ 24ኛውን ዓመት የሩዋንዳ ዘር ጭፍጨፋን ለማስታወስ በዩጋንዳ ውስጥ አበባ አስቀምጠዋል።
ሱዳን ውስጥ የሚገኙትና በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡት የሜሮ ፒራሚዶች ይህንን ይመስላሉ። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ሱዳን ውስጥ የሚገኙትና በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡት የሜሮ ፒራሚዶች ይህንን ይመስላሉ።
በአውሮፓውያኑ ከ207-186 ዓመተ ዓለም የሜሮን ግዛትን የመሩት የንጉስ ካልማኒ መካነ-መቃብር ውስጥ የተለያዩ ቅርሶች ተገኝተዋል። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በአውሮፓውያኑ ከ207-186 ዓመተ ዓለም የሜሮን ግዛት የመሩት የንጉስ ካልማኒ መካነ-መቃብር ውስጥ የተለያዩ ቅርሶች ተገኝተዋል።
በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ህፃናት ልጆች የሜዳ አህያን በመሳል ላይ ናቸው። ይህም ሰብዓዊና የእንስሳት መብትን ግንዛቤን ለመጨመር የተያዘ ጅማሮ ነው። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ህፃናት ልጆች የሜዳ አህያን በመሳል ላይ ናቸው። ይህም ሰብዓዊና የእንስሳት መብትን ግንዛቤን ለመጨመር የተያዘ ጅማሮ ነው።
በግብጿ ከተማ አሌክሳንድሪያ አንድ አንጥረኛ በስራቸው ቦታ ላይ ትንሽ እረፍት በመውሰድ ሺሻ እያጨሱ ነው። Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በግብጿ ከተማ አሌክሳንድሪያ አንድ አንጥረኛ በስራቸው ቦታ ላይ ትንሽ እረፍት በመውሰድ ሺሻ እያጨሱ ነው።
በቱኒዝያዋ ጎሮምባሊያ ከተማ አንዲት አዛውንት በባህላዊ መንገድ ዳቦ በመጋገር ላይ ናቸው። Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በቱኒዝያዋ ጎሮምባሊያ ከተማ አንዲት አዛውንት በባህላዊ መንገድ ዳቦ በመጋገር ላይ ናቸው።
የአይቮሪኮስቷ ሙዚቀኛና ዳንሰኛ ዶቤት (ቫለሪ) ጋንሆር በመዲናዋ አቢጃን በነበረ ፌስቲቫል የተሰበሰበውን ህዝብ አዝናንታዋለች። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የአይቮሪኮስቷ ሙዚቀኛና ዳንሰኛ ዶቤት (ቫለሪ) ጋንሆር በመዲናዋ አቢጃን በነበረ ፌስቲቫል የተሰበሰበውን ህዝብ አዝናንታዋለች።

እነዚህ ምስሎች የተገኙት ከኤኤፍፒ፣ ጌቲ ኢሜጅስ፣ ሮይተርስና ኢፒኤ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች