ማክሮንና ሩሃኒ በቀጭኑ ሽቦ

ማክሮንና ሩሃኒ በቀጭኑ ሽቦ Image copyright Reuters

የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑዔል ማክሮን ከኢራን አቻቸው ሃሳን ሩሃኒ ጋር በኒውክሊዬር ጉዳይ ላይ በስልክ እንደተወያዩና ኢራን ወደ ድርድሩ እንትገባ እንዳሳሰቧቸው እየተነገረ ነው።

በስልኩ ውይይት እያካሄዱ ሳለ የኢራኑ ፕሬዚደንት ሩሃኒ ሰባት ሃገራት ተሳታፊ እየሆኑበት ያለው ውይይት ለድርድር የማይቅርብ እንደሆነ ለማክሮን ነገረዋቸዋል።

ቀደም ብሎ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ እና ጀርመን ኢራን የኒውክሊዬር መሠሪያ ማብላላቷን እንድታቆም ዋነኛው መፍትሄ ውይይት ነው ብለው አቋም መያዛቸው ተዘግቦ ነበር።

ቢሆንም የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ያነሷቸው ጉዳዮችም ከግምት ውስጥ መግባት እንዳለባቸው ሃገራቱ አልሸሸጉም።

ትራምፕ "የማይረባ" እያሉ የሚጠሩትን በአውሮፓውያኑ 2015 የተደረሰው ስምምነት በሚቀጥሉት ሳምንታት ሊያፈርሱት እንደሚችሉም ስጋት አለ።

ለአንድ ሰዓት ያህል ዘለቀ በተባለው ውይይት ማክሮን በኒውክሊዬር ጉዳይ መወያየትን የመሰለ ነገር እንደሌ አፅንኦት ሰጥተው እንደበርና ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያላትን ጣልቃ ገብነት ልብ እንድትል ለሩሃኒ እንደነገሯቸው ታውቋል።

ሩሃኒ በበኩላቸው "ኢራን ቃል ከገባችው ውጭ የሆነ ነገር ላትቀበል ዝግጁ መሆኗን" ለማክሮን በግልፅ ነግረዋቸዋል። አሜሪካ ስምምነቱን አፈረሰቸው አላፈረሰቸው ኢራን እንደማያስጨንቃት፤ ይልቁንም የትራም የቅርብ ጊዜ ድርጊት እንዳሳቆጣቸው ነው ሩሃኒ የተናገሩት።

ቢሆንም ኢራን ከፈረንሳይ ጋር ያላትን በጎ ግንኙነት ለማጠንከር ይበልጥ እንደሚተጉ አሳውቀዋል።