የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች የላውሮ ግምት

የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ሦስተኛ ወራጅ ቡድን በመጨረሻው ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ይታወቃል። ስዋንሲ ከመውረድ ለመትረፍ አሸንፎ የሳውዝሃምፐተንን ውጤት መጠበቅ ይኖርበታል።

የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን የዌልሱ ቡድን እንደሚወርድ ግምቱን አስቀምጧል። "ስዋንሲ ስቶክን እንደሚያሸነፍ ብጠብቅም በሊጉ ግን አይቆይም" ብሏል ላውሮ።

የላውሮ ግምት

እሁድ

Image copyright BBC Sport

በርንሌይ ከ በርንማውዝ

ሁለቱም ቡድኖች ጥሩ ውድድር ዓመት ቢያሳልፉም በርንሌይ ደግሞ የተሻለ ጊዜን አሳልፏል።

በጨዋታው በርንሌይ ሦስት ነጥብ እንደሚያገኝ እገምታለሁ።

የላውሮ ግምት: 2-1

Image copyright BBC Sport

ክሪስታል ፓላስ ከ ዌስት ብሮም

ውድድሩ ሲጀምር እነዚህ ቡድኖች ውጤታቸው የተለያየ ነበር። ዌስት ብሮም 10ኛ ደረጃ ላይ ሲሆን ፓላስ ደግሞ መጨረሻ ነበር። አሁን ግን ሁሉም ነገር የተገላቢጦሽ ሆኗል።

ይህንን ጨዋታ ግን ዌስት ብሮም እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።

የላውሮ ግምት: 1-2

Image copyright BBC Sport

ሃደርስፊልድ ከ አርሴናል

ሃደርስፊልድ ከቼልሲም ሆነ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አልጠበኩም ነበር።

አርሴናሎች 5 ለ 0 ካሸነፉ በኋላ 3 ለ 1 በመሸነፋቸው አልተገረምኩም። የእሑዱ ጨዋታ ጥንቃቄ የተሞላበት ይሆናል ብዬ አላስብም።

የላውሮ ግምት: 1-1

Image copyright BBC Sport

ሊቨርፑል ከ ብራይተን

ሊቨርፑሎች ያላቸውን የጎል ልዩነት ተጠቅመው አንድ ነጥብ በማግኘት ከቼልሲ በላይ ሆነው ያጠናቅቃሉ።

ብራይተኖች ማንቸስተር ዩናይትድን በማሸነፍ በሊጉ ስለመቆየታቸው አረጋግጠዋል።

የላውሮ ግምት: 2-0

Image copyright BBC Sport

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ዋትፎርድ

ማንቸስተር ዩናይትድ እንግዳ ሆነ የውድድር ዓመት ቢያሳልፍም በሊጉ ሁለተኛ ሆኖ ከማጠናቀቀ ባለፈ የኤፍ ኤ ዋንጫንም ሊያነሳ ይችላል።

ጨዋታውን ማንቸስተር ዩናይትድ በማሸነፍ ከዓመታት በፊት ዋንጫ ለማንሳት በቂ የነበረውን 80 ነጥብ ያልፋል።

የላውሮ ግምት: 2-0

Image copyright BBC Sport

ኒውካስትል ከ ቼልሲ

ቼልሲ ዘንድሮ ጥሩ ውድድር ዓመት ካለማሳለፉም በላይ በቀጣዩ ዓመት አንቶኒዮ ኮንቴ ከቡድኑ ጋር የሚቀጥሉ አይመስልም።

ኒውካስትል በሊጉ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ ሦስት ነጥብ አያገኝም።

የላውሮ ግምት: 0-2

Image copyright BBC Sport

ሳውዝሃምፕተን ከ ማንቸስተር ሲቲ

ጨዋታውን ማንቸስተር ሲቲ እንደሚያሸንፍ ብገምትም ሳውዝሃምፐተንን ወደ ታችኛው ሊግ እንዲወርዱ የሚያደርግ ጎል አያስቆጥሩም።

ባለፈው ሳምንት ሦስት ክብረ ወሰኖችን የሰበሩት ሲቲዎች በሊጉ 100 ነጥብ የማግኘት እቅዳቸውን ያሳካሉ።

የላውሮ ግምት: 0-2

Image copyright BBC Sport

ስዋንሲ ከ ስቶክ

ጨዋታውን ስዋንሲ ቢያሸንፍም በሊጉ የሚያቆያቸው ውጤት አይሆንም። ስቶክን በታችኛው ሊግ ይቀላቀላሉ።

የስዋንሲው አሰልጣኝ ካርሎስ ካርቫሃል በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ቡድኑን ይለቃሉ። ሥራቸውን ሲጀምሩ ውጤታማ መሆን ቢችሉም በኋላ ላይ አልተሳካላቸውም።

የላውሮ ግምት: 2-0

Image copyright BBC Sport

ቶተንሃም ከ ሌስተር

የሌስተሩ አሰልጣኝ በሚቀጥለው ዓመት ከቡድናቸው ጋር ስለመቆየታቸው ካልተረጋገጠላቸው አሰልጣኞች መካከል ናቸው።

በጨዋታው ቶተንሃም እንደሚያሸንፍ እና ሃሪ ኬን ጎል እንደሚያስቆትር እገምታለሁ።

የላውሮ ግምት: 2-0

Image copyright BBC Sport

ዌስት ሃም ከ ኤቨርተን

የዌስትሃሙ ዴቪድ ሞዬስ እና ኤቨርተኑ ሳም አላርዳየስ በሚቀጥለው የውድድር ዓመት ከቡድናቸው ጋር ስለመቆየታቸው ካልተረጋገጠላቸው አሰልጣኞች መካከል ናቸው።

ሁለቱም አሰልጣኞች ቡድኖቻቸው እንዳይወርዱ የተሰጣቸውን ሃላፊነት ተወጥተዋል።

የላውሮ ግምት: 2-0

ተያያዥ ርዕሶች