የአሜሪካ ባለስልጣናት የመክፈቻ ስነ ስርዓቱን ይታደማሉ።

የዶናልድ ትራምፕ ሴት ልጅ ኢቫንካ ትራምፕ በእስራኤል የአሜሪካው አምባሳደር ከሆኑት ዴቪድ ፍሬድማን ና ከባለቤቷ ጃረድ ኩሽነር ጋር በቤን ጉሪዎን አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ የዶናልድ ትራምፕ ሴት ልጅ ኢቫንካ ትራምፕ በእስራኤል የአሜሪካው አምባሳደር ከሆኑት ዴቪድ ፍሬድማን ና ከባለቤቷ ጃረድ ኩሽነር ጋር በቤን ጉሪዎን አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ

አሜሪካ አነጋጋሪ የሆነውን ኤምባሲዋን በእየሩሳሌም ልትከፍት ነው። ይህ የአሜሪካ ውሳኔ በእስራኤላውያን ቢደገፍም በርካታ ፍሊስጤማውያን ለተቃውሞ እየተሰባሰቡ ነው።

የአሜሪካውን ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሴት ልጅ ኢቫንካ እና ባለቤቷን ጃርድ ኩሽነር ጨምሮ የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በዝግጅቱ ላይ ይገኛሉ።

የዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካንን ኤምባሲ ቀድሞ ከነበረበት ቴል አቪቭ ወደ እየሩሳሌም የማዛወር ውሳኔ ፍልስጤማውያንን አስቆጥቷል። ምስራቅ እየሩሳሌም የፍልስጤም ግዛት የወደፊት መቀመጫ ናት ሲሉ ተቃውመዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ 1967 በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት እስራኤል ምስራቃዊ የፍልስጤም ግዛትን ተቆጣጥራ ነበር።

በስነ ስርዓቱ ላይ እነማን ይገኛሉ?

እየሩሳሌም በሚገኘውና ቀድሞ በነበረው የአሜሪካ ቆንፅላ ህንፃ ኤምባሲው ዛሬ ስራ ይጀምራል።

ኤምባሲው ሙሉ በሙሉ ከቴል አቪቭ ለቆ ሲመጣ ወደ ሌላ ሰፋር ይዘዋወራል።

የመክፈቻ ስን ስርዓቱ ከእስራኤል 70ኛ ዓመት ክብረ በዓል ጋር ተገጣጥሟል።

ፕሬዚደንት ትራምፕ በስነ ስርዓቱ ላይ ባይገኙም በ ቪዲዮ መልዕክት ለታዳሚያን ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኤምባሲውን መዛወር ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ከፍትኛ ቅሬታ አላቸው በዚህም ምክንያት በእስራኤል የሚገኙ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደሮች በዝግጅቱ ላይ አይገኙም። ይሁን እንጅ የሃንጋሪ፣ ሮማኒያና ቸክ ሪፐብሊክ ተወካይ ጨምሮ በርካታ ድፕሎማቶች ይገኛሉ ።

የጓቲማላ ና የፓራጓይ ፕሬዚንዳንቶችም ዝግጅቱን ይካፈላሉ። የዶናልድ ትራምፕን ውሳኔ ተከትሎ ሁለቱም አገራት ኤምባሲያቸውን ወደ እየሩሳሌም ቴላቪቭ ለማዛወር ወስነዋል።

የእስራኤላውያንና የፍልስጤማውያን ምላሽ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ እስራኤላውያን በአሜሪካን ውሳኔ ፈንጠዝያ ላይ ናቸው

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢኒያሚን ኔታንያሆ ሁሉም አገራት ኤምባሲያቸውን ወደ እየሩሳሌም በማዛወር አሜሪካን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የፍሊሊስጤማውያን መንግስት ፕሬዝደንት መሃሙድ አባስ በበኩላቸው የፕሬዚደንት ትራምፕን ውሳኔ የክፍለ ዘመኑ ወረራ ሲሉ ገልፀውታል።

Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ እስራኤል መዛወሩን ተከትሎ ፍልስጤማውያን ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ

በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስራኤልንና የጋዛ ሰርጥን ድንበር አካባቢ ለተቃውሞ እየተሰባሰቡ ነው።

ኤምባሲው የተዘዋወረበት ጊዜ በጋዛ ያለውን ውጥረት ሊያመራው ይችላል። በአውሮፓውያኑ ሚያዚያ ወር ጀምሮ ከ አርባ የሚበልጡ ፍልስጤማውያን በድንበር አካባቢ በተፈጠረ ተቃውሞ በእስራኤል ወታደሮች ተገድለዋል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት መሪ ዜይድ ራአድ አል ሁሴን ከፍተኛ ሃይል ተጠቅመዋል ሲሉ ወቅሰዋል።

የኤምባሲው መዛወር ለምን አነጋጋሪ ሆነ?

የእየሩሳሌም ሁኔታ የሁለቱን አገራት ግጭት ሊያባብሰው ይችላል።

እስራኤል የእየሩሳሌም ግዛት ይገባኛል ጥያቄ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባለማግኘቱና በ1993 የእስራኤልና የፍልስጤማውያን የሰላም ስምምነት ምንመ እንኳን እስራኤልም ባትስማማበትም እየሩሳሌም ሁለት መቶ ሺህ ለሚደርሱ አይሁዶች መኖሪያ መገንባቷና ይህም በአለም አቀፉ ህግ ተቀባይ ባለመሆኑ።

እንዲሁም በርካታ የአለም አገራት ኤምባሲያቸውን በእየሩሳሌም እሁን እንጂ እንደ አውሮፓውያኑ 1980 በሗላ ወደ እስራኤል እያዛወሩ በመሆናቸው ነው።