ለ26 ዓመቱ ወጣት የ250 ዓመት የእስር ፍርድ

Image copyright Getty Images

ደቡብ አፍሪካዊው ግለሰብ አስገድዶ መድፈር እና የግድያ ሙከራ በመፈጸመ በሚሉ ወንጀሎች 25 የዕድሜ ልክ እስራቶች ተበየነበት።

የደቡብ አፍሪካው ፍርድ ቤት የ26 ዓመቱ ወጣት ላይ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው፤ 23 የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎችን በመፈጸሙ እንዲሁም ሁለት የግድያ ሙከራዎችን በማድረጉ ነው ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም፤ በአካል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ፣ ዘረፋ፣ ጠለፋ እና የግድያ ሙከራ በሚሉ ሌሎች ተጨማሪ ወንጀሎች የ254 ዓመት እስራት ተላልፎበታል።

ግለሰቡ የአስገድዶ መደፈር ወንጀሎቹን የፈጸመው እአአ 2012-2014 ባሉት ዓመታት መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ እንደሚለው ወንጀለኛው ቤት ሰብሮ በመግባት አካላዊ ትንኮሳን ይፈጽማል ከዚያም አስገድዶ ይደፍራል።

የፖሊስ ቃል አቀባይ እንዳሉት ግለሰቡት በቁጥጥራቸው ስር የወደቀው ከሶስት ወራት በፊት የጥቃቱ ሰለባ የሆነች ሴት ለፖሊስ በሰጠችው ጥቆማ ነበር።