ትራምፕ እና ኪም ለመገናኘት የያዙት ዕቅድ እንደሚሳካ አሜሪካ ተስፋ አድርጋለች

North Korean leader Kim Jong Un inspects what is claimed to be a miniaturized nuclear weapon ( KCNA handout) Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ኪም ጆንግ ኡን የኒውክለር ጦር መሣሪያ ቦታ ሊሆን ይችላል የተባለ ቦታን ሲጎበኙ

ሰሜን ኮሪያ የእሰርዘዋለሁ ማስፈራሪያ ብትሰነዝርም የትራምፕ መንግሥት ከሰሜን ኮሪያ ጋር በቅርቡ የሚያደርጉት ጉባዔ እንደሚካሄድ ተስፋ አድርጓል።

ኪምና ትራምፕ ፊት ለፊት ተገናኝተው ለመመካከር የወሰኑት የኮሪያን ሰርጥ ከኒውክሌር ነፃ ለማድረግ ሰሜን ኮሪያ በመስማማቷ ነበር።

ይሁን እንጂ በጉባዔያቸው መዳረሻ የአሜሪካ ብሄራዊ የፀጥታ አማካሪ ጆን ቦልተን "ሰሜን ኮሪያ ሊቢያ ስትከተለው የነበረውን የጦር መሳሪያዎች ቅነሳ አሰራር ሂደት ልትከተል ትችላለች" ሲሉ የሰጡት መግለጫ ሃገሪቱን አስቆጥቷል።

ሰሜን ኮሪያ ከትራምፕ ጋር የሚደረገውን ጉባዔ ልሰርዝ እችላለሁ ስትል አስፈራራች

"አማካሪው ያደረጉት ንግግር አደገኛና ግድ የለሽነት የተሞላበት ነው" ሲሉ የሰሜን ኮሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአማካሪው ላይ ጣታቸውን ቀስረዋል። ንግግራቸውም ሌሎች ባለስልጣናትን ይወክላል ብለዋል።

Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ሰሜን ኮሪያ ሶስት አሜሪካኖችን በቅርቡ ፈታለች

አሜሪካ የኒውክሌር መሳሪያ እንዳቆም ጫና የምትፈጥርብኝ ከሆነ ከአንድ ወር በኋላ የሚካሄደውን ጉባዔ ልሰርዝ እችላለሁ ብላለች ሰሜን ኮሪያ።

ይህንን የሰሜን ኮሪያ ውሳኔ ተከትሎ የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ የሆኑት ሳራህ ሳንደርስ "ፕሬዚደንት ትራምፕ ለጉባዔው ዝግጁ ናቸው። የማይሆን ከሆነ ግን ግፊት ማድረጋችንን እንቀጥላለን" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል ።

ፕሬዚደንት ትራምፕ በበኩላቸው "የሚሆነው እናያለን፤ አሜሪካ የኮሪያ ሰርጥ ከኒውክሌር ነፃ እንዲሆን ግፊታችንን እንቀጥላለን" ሲሉ ተናግረዋል።

ጉባዔው ከአንድ ወር በኋላ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል ።