የማለዥያ ፖሊስ ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ ውድ ንብረቶችን ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ቤት ያዘ

Police remove items from Najib Razak's residence in Kuala Lumpur, Malaysia (18 May 2018) Image copyright EPA

የማሌዥያ ፖሊስ ከቀድሞው የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ናጂብ ራዛክ ቤት ውድ ንብረቶችንና የውጭ ሃገር ገንዘቦችን መያዙን አስታወቀ።

በዋና ከተማዋ ኩዋላ ሉምፑር የተደረገው ምርመራ ከመንግሥት የልማት ፈንድ ጋር በተያያዘ መሆኑን ተገልጿል።

ከፈንዱ ጋር በተያያዘ የቀረበው የሙስና ክስ ናጂብ ባለፈው ጊዜ በማሌዥያ ምርጫ እንዲሸነፉ ምክንያት ነበር ተብሏል።

ናጂብ ያቋቋሙት የመንግሥት የልማት ፈንድ የሚያንቀሳቅሰው በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ኦዲት አለመደረጉ ተገልጿል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር 700 ሚሊዮን ዶላር ከፈንዱ ወስደዋል ቢባሉም ውንጀላውን አጣጥለውታል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የማሌዥያ ባለስልጣናት ነጻ ናቸው ብለው ምርመራ ቢያቋርጡም በሌሎች ሃገራት ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።

Image copyright EPA

የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ምርመራውን እንደ አዲስ ከመጀመር ባለፈ ጠፋ የተባለውን ገንዘብ እንደሚያገኙ አስታውቀዋል።

ይህን ተከትሎም ናጂብ ከሃገር እንዳይወጡ ዕገዳ ተጥሎባቸዋል። የሃገሪቱ ፖሊስም ለቀናት በመኖሪያ ቤታቸው እና ከእሳቸው ጋር ግንኙነት አላቸው በሚባሉ ቦታዎች ላይ ፍተሻ አድርጓል።

የፖሊስ የወንጀል ምርመራ ኃላፊው አማር ሲንግ 284 ሳጥን ውድ የእጅ ቦርሳዎች መያዛቸውን ተናግረዋል።

ቦርሳዎቹ ጌጣ ጌጦችንና የተለያዩ ሃገራት ጥሬ ገንዘብ መያዛቸውን አስታውቀዋል።

ተያያዥ ርዕሶች