በኩባ የአውሮፕላን አደጋ የሟቾች ቁጥር 111 ደርሷል

የግሬቴል ላንድሮቭ እናት አምፓሮ ፎንት ለ ቢቢሲ ሲናገሩ

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty

በሰላሳ ዓመታት ውስጥ አደገኛ በተባለለት የኩባ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የሟቾች ቁጥር 111 እንዳሻቀበ ተገልጿል።

ባዛሬው ዕለትም ዳንሰኛና የምህንድስና ተማሪ የነበረቸው የሃያ ሶስት ዓመቷ ግሬቴል ላንድሮቭ አርፋለች።

ቢቢሲ በሆስፒታል አግኝቶ ያነጋገራቸው የሟች እናት "ልጄ ለህይወቷ ታጋይ ናት" ቢሉም ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ህይወቷ ማለፉ ተነግሯቸዋል።

የአውሮፕላኑ አብራሪ አባላት ሜክሲኮያውያን ሲሆኑ አብዛኞቹ ተጓዦች ግን ኩባውያን ነበሩ።

ከተጓዦቹ ማካከል ለጉብኝት ከምዕራብ አፍሪካ ወደ ሜክሲኮ ሲያቀኑ የነበሩ ሁለት ሰዎች እንዲሁም አርጀንቲናውያን ጥንዶች ይገኙበታል።

ግሬቴል ላንድሮቭ ባለፈው አርብ ከተከሰከሰው የአውሮፕላን አደጋ ከሶስቱ አንዷ የነበረች ሲሆን ሌሎች ሁለት ሰዎች በአስጊ ሁኔታ እንዳሉ ተገልጿል ።

በዚሁም ዕለት የሜክሲኮ አቪየሽን ባለስልጣናት አውሮፕላን የተከሰከሰበት ኩባንያ ባለቤት ፈቃድ አግደዋል።

ባለሥልጣናቱ በመግለጫቸው እንዳተቱት አውሮፕላኑ የምርመራ ስራው ሳያልቅ ኩባንያው ግን ለኩባ አየር መንገድ አስተላልፈው መስጠታቸውን ገልፀዋል።

"አውሮፕላኑ በ1979 ተመርቶ ጥገና የተደረገለስ ሲሆን በጣም ደካማ ነበር፤ ከራዳር ቁጥጥር ውጭ ሆኖም ነበር"። ሲል የቀድሞ የአውሮፕላኑ አብራሪ ተናግረዋል።

የሜክሲኮ አቪየሽን ዋና ዳሬክተር ባለስልጣን የአደጋውን መንስዔ ለማጣራት መረጃዎችን እየሰበሰበ እንደሆነ ገልጿል።