የናይጀሪያ ምጣኔ ኃብት መዳከም አሳየ

የናይጀሪያ ኢኮኖሚ መዳከም አሳይቷል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የናይጀሪያ ባለስልጣናት እንደተናገሩት የአገሪቷ ምጣኔ ኃብት በያዝነው የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ማሽቆልቆል አሳይቷል።

እንደ አገሪቱ ብሄራዊ ስታስቲክስ መረጃ መሰረት በአውሮፓውያኑ 2017 የመጨረሻ ሩብ ዓመት ከተመዘገበው 2.11 በመቶ ዕድገት ጋር ሲነፃፀር የአሁኑ 1.95 በመቶ በማስመዝገብ ዝቅተኛ ሆኗል።

የናይጀሪያ ምጣኔ ኃብት ሲያሽቆለቁል ከአውሮፓውያኑ 2017 ጥር አንስቶ የመጀመሪያው ነው ብለዋል።

የናይጀሪያ ብሔራዊ ስታስቲክስ ቢሮ እንዳስታወቀው በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የናይጀሪያ የነዳጅ ምርት የጨመረ ሲሆን ሌሎች ምርቶች ላይ መዳከም ታይቷል።

የአገሪቷ ባለስልጣናት በበኩላቸው ምጣኔ ኃብቷ በተወሰነ መልኩ ከመዳከሙ በስተቀር እድገቱ አሁንም ጠንካራ ነው ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት የናይጀሪያ ፓርላማ የሚቀጥለው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ከማካሄዷ አስቀድሞ የአገሪቷን እድገት ለማፋጠን በሚል ለ 2018 የበጀት ዓመት 29 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መድቧል።

የናይጀሪያ ምጣኔ ኃብት የተመሰረተው በነዳጅ ዘይት የወጭ ንግድ ላይ የተመሰረተ ሲሆን መንግሰት ሌሎች ዘርፎችም ላይ ለመስራት ጥረት እያደረገ ነው።