በናይጀሪያ መቶ ተማሪዎች ለህገ ወጥ ዝውውር ተዳረጉ

ሰሎሞን ኦኮዱዋ ኢዶ በተባለ የናይጀሪያ ግዛት በሚገኝ ት/ቤት ስለ ህፃናት ዝውውር ያስተምራሉ

በደቡብ ናይጀሪያ በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ከተወሰዱት ሌላ በግዛቱ የሚገኝ ትምህርት ቤት ባለፉት አራት ወራት ውስጥ በትንሹ አንድ መቶ የሚሆኑ ተማሪዎች መጥፋታቸውን የትምህርት ቤቱ መምህራን አስታወቁ።

የሰዎች ዝውውርና ህገ ወጥ ስደት ባለሙያ የሆኑት ሶሎሞን ኦኮዱዋ በቤኒን ከተማ የሚገኘውን ትምህርት ቤት ለመጎብኘት በሄዱበት ወቅት የተማሪዎቹን መጥፋት ከመምህራኖቹ እንደሰሙ ተናግረዋል ።

ሰሎሞን ጨምረው እንደተናገሩት መምህራኖቹ መጀመሪያ የጠፉት ተማሪዎች ታመው መስሏቸው የነበረ ቢሆንም ከሌሎች ተማሪዎች እንደተረዱት አውሮፓ ለመድረስ በሊቢያ በኩል እንደሄዱ ተረድተዋል።

ነገር ግን ለምን እንደሄዱና ፤ ማን እንዳነሳሳቸው የታወቀ ነገር የለም።

ተማሪዎቹ መረጃውን እንዴት እንዳገኙ መምህራኑ በተጠየቁ ጊዜ ከዚህ ቀደም ተጉዘው ከነበሩ ሰዎች መረጃ ያገኙ ተማሪዎች አማካኝነት ሰምተው ሳይሆን እንዳልቀረ ገልፀዋል ።

ባለሙያው ኦኮዲዋ በትምህርት ቤቱ ግንዛቤ የመስጠቱ ስራ እንደቀጠለና ኢዶ በምትባለው የናይጀሪያ ግዛት ባሉ ሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም ግንዛቤው መሰጠት ይጀምራል ብለዋል።