በደቡብ አፍሪካ ለሴቶችና ህፃናት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲመቻች ተጠየቀ

በደቡብ አፍሪካ የመንገደኞች ባቡር

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ጥምረት ቡድን ለሴቶችና ህፃናት ምቹ የሆነ የመጓጓዣ አገልግሎት እንደገና መሰጠት እንዲጀመር የባቡር ትራንስፖርት ኤጀንሲን ጠየቁ።

ጥምረቱ ኤጀንሲውን የጠየቀው ሴት ተሳፋሪዎች በህዝብ ትራንስፖርት ላይ ደህንነታቸው ባልተጠበቀ ሁኔታ እንደሚጓዙና ችግሮች እየገጠማቸው በመሆኑ ነው ብለዋል።

በመሆኑም የባቡር ትራንሰፖርት አገልግሎት ኤጀንሲው ይህን ተገንዝቦ ለእነርሱ ቅድሚያ በመስጠት አማራጭ ትራንስፖርት ማቅረብ አለበት ሲሉ ነው ድምፃቸውን ያሰሙት።

ሌላ የመጓጓዣ መንገድ መመቻቸቱም ለህፃናት ምቹ ቦታን ለመፍጠር ያስችላል ሲሉም አስረድተዋል።

ከደቡብ አፍሪካ የመንገደኞች ባቡር ኤጀንሲ አስተዳደር ባለሙያዎች ጋር የተነጋገረው ጥምረቱ ጥያቄያቸውን ለመመለስ ቃል ገብተውላቸዋል።

ይህም ተቋርጦ የነበረውን ለህፃናት ምቹ የሆነውን ትራንስፖርት እንደገና ማስጀመርን ያጠቃልላል ብለዋል ።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ናና ዜናኒ እንደተናገሩት በጥምረቱ የቀረበው ጥያቄ በቀጣይ ውይይት ከምናደርግባቸው ጉዳዮች ዋናው ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ከዚህ ቀደም ይሰጥ የነበረው አገልግሎት በምን ምክንያት እንደተቋረጠ አይታወቅም።