የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር አልተሳካም

ተቃዋሚዎች ስምምነቱ ለፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ብዙ ስልጣን ይሰጣል ብለዋል

በቅርቡ የተካሄደው የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር ስምምነት ላይ ሳይደረስ ተጠናቀቀ።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) በሶስት አዳዲስ ሃላፊነቶች የስልጣን ክፍፍል ዕቅድ አቅርቦ ነበር።

ከእነዚህ ሃላፊነቶች አንዱ የአማፂያኑ መሪ ለሆኑት ሪያክ ማቻር እንዲተላለፍ የሚጠይቅ ነበር ።

ተቃዋሚ የሆነው የኤስፒኤልኤአይኦ አባል የሆኑት ማቢኦር ጋራንግ እንደተናገሩት "የቀረበው የስልጣን ክፍፍል ዕቅድ ፍትሃዊ አይደለም፤ ያለውን ችግር የሚያባብስና ስልጣን በገዥው መንግስት እጅ እንዲሆን የሚያጠናክር ነው" ብለዋል።

በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና የቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ሪያክ ማቻር ከአምስት ዓመታት በፊት በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት አገሪቷ እርስ በርስ ግጭት እየታመሰች ነው።

በዚህም ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱ ሲሆን አራት ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ተፈናቅለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች