የሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ ለመሆን የሚያስችለው ሥነ-ልቦና

Liverpool celebrate their 1984 European Cup win Image copyright Rex Features

በ1984ቱ የአውሮፓዊያን ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ በፊት የነበረኝን ዓይነት ድንጋጤ ኖሮኝ አያውቅም። አብዛኛዎቹ የሊቨርፑል አባላት ይህ ስሜት ነው የሚኖራቸው።

በውድድሩ ተጉዘን ለፍጻሜ ስንደርስ ሙሉው ከተማ በደስታ ስሜት ውስጥ ነበር።

ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን ደጋፊዎች ውጭ አብዛኛው የሃገሪቱ ክፍል ከኋላችን እንደሆነ እናውቃለን።

Image copyright Rex Features

26 ዓመቴ ከመሆኑም በላይ የትልልቅ ጨዋታዎች ልምድም ነበረኝ። ሆኖም ግምቶች ጨዋታውን የተለየ ያደርጉታል። ይህ ለአብዛኛው የየርገን ክሎፕ ቡድን እንደሚሰራ አውቃለሁ።

ይህ ችግር የሚሆነው ከጨዋታው አንድ ወይንም ሁለት ሰዓታት በፊት ሳይሆን ከቀናት በፊት ነው።

ለክሎ-ልቦና ከጨዋታ ታክቲክ እኩል ነው

ከጨዋታው በፊት ያለው ሳምንት እጅግ ረዥም ነው። በጨዋታው ቀን ስሜቱ ከመጣ በኋላ ግን ሁሉም ነገር ይቀየራል።

ፍርሃት አሁንም ሊኖር ይችላል። የ1984ቱ ፍጻሜ ጨዋታ ትልቁ የጨዋታ ዘመኔ ምሽት ነው። ከሮማ ጋር የሚደረገው ጨዋታ በስታዲዮ ኦሎምፒኮ ከመካሄዱም በላይ በሜዳቸው ነበር የሚጫወቱት።

ጨዋታው ያለው ውጥረት ትልቅ ቢሆንም ይህን መከላከል የሚቻልበት መንገድም አለ።

ከጨዋታው በፊት አሰልጣኛችን ጆ ፋጋን ትልቁ ጫና ያለው በባለሜዳው ቡድን ላይ እንደሆነ ነገረን።

Image copyright Getty Images

ይህም ነገሮችን ከመቀየሩም በላይ ከፊት ለፊታች ላለብን ሃላፊነት ትልቅ ስንቅ ሆነን።

በዚያን ወቅት ይህ የሥነ-ልቦና ጉዳይ እንደሆነ ባንገልጸውም በትልልቅ ጨዋታዎች ላይ በብቃት እንድንፎካከር የሚረዳ ነው።

ክሎፕ ከቅዳሜው ጨዋታ በፊት ይህንን እንደሚያደርግ እና ቡድኑ ጥሩ ሲጫወት ያለውን መንፈስ እንዲይዝ እንደሚያደርግ ተስፋ አደርጋለሁ።

'ትልቅነቱን እና በቴሌቪዥን የሚከታተለውን እርሱት'

ሊቨርፑል ከማድሪድ ጋር እንደሚጫወት እና ደጋፊዎቹ እንዳሉ እንዲረሱ እንዲሁም ተጫዋቾቹ ሥራቸው መስራት እንዳለባቸው ክሎፕ ያውቃል።

ጨዋታውን እንደሁልጊዜውም እንዲመለከቱት እና በራሳቸው መንገድ እንዲጫወቱ እንደሚነግራቸው አስባለሁ። ይህ ከሆነ ጥሩ ተስፋ ይኖራቸዋል።

ተጫዋች ይህን ማድረግ የሚችለው ስለአሰላለፍ፣ ደጋፊው በቲቪ ስለሚመለከተው በመርሳት ጨዋታውን ከተጫዋተ ነው።

'ሁሉም ትልቅ ቡድኖች ድንቅ አጨዋወት በማሳየት ድል አላስመዘገቡም'

ጨዋታው ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ለመሆን ከሚጥሩት ሪያል ማድሪዶች አንጻር ለሊቨርፑል አዲስ ነው።

ካላቸው አውሮፓ ድል አንጻር ቡድኖቹን ማይደግፉት ሊያዩት የሚመርጡት አይነት ጨዋታ ነው።

የሁለቱ ቡድኖች ልዩነት ሪያል ማድሪድ ያለው ልምድ ነው።

አንዴ መምራት ከጀመሩ ጨዋታውን ማጠናቀቅ የሚችሉ ሲሆን ሊቨርፑሎች ግን ይህን ማድረግ ስለመቻላቸው አላሳዩም።

ማድሪድ ቀድሞ ጎል ካስቆጠረ ሊቨርፑልን ለማቆም የትኛውንም መንገድ ይጠቀማል።

የዚዳን ቡድን ለማሸነፍ ጥሩ መጫወት ለበትም። ሁሉም ትልቅ ቡድኖች ድንቅ አጨዋወት በማሳየት ድል አላስመዘገቡም።

የላውሮ ግምት፡ ሊቨርፑል 2 ለ 1 ያሸንፋል (ከተጨማሪ ሰዓት በኋላ)

ሪያል ማድሪድ እንደሚያሸንፍ ቢገመትም ሊቨርፑል የበላይ የሚሆንበት መንገድ አያጣም ብዬ አስባለሁ።

ይህን በማድረግ እና ብዙ ጎል በማስቆጠር ነው ለፍፃሜ የደረሱት።

ከማንቸስተር ሲቲ ጀምሮ አንድ የሚከተላቸው ነገር እንዳለ እና ትልልቅ ስህተት የሆኑ ውሳኔዎች ሲጠቅሟቸው ተመልክተናል።

ይህን መሰለው ነገር ገጥሞኝ እና እምነታችንን አሳድጎት ያውቃል።

ራሴን እንደሊቨርፑል ተጫዋች ባየው ከማንቸስተር ሲቲ እና ከሮማ ጋር ከነበረው ሁኔታ አንጻር "ለማሸነፍ እየተጓዝን ነው ምክንያቱም ሁሉም ነገር የእኛ እየሆነ ነው" ብዬ አስባለሁ።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሊቨርፑል በ12 የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች 40 ጎሎችን አስቆጥሯል

እንደገመትኩት ለስድስተኛ ጊዜ ካሸነፉ ትልቅ ስኬት ነው። ለክሎፕ በሊቨርፑል ከዋንጫም በላይ ነው የሚሆነው።

ከውድድሩ የሚያገኙት ገንዘብና ስም በሚቀጥለው ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ለዋንጫ እንዲፎካከሩ ይረዳቸዋል።

ማርክ ላውረንስ ከቢቢሲው ስፖርት ጋዜጠኛ ክሪስ ቤቫን ጋር ነው የተነጋገረው።

ባለፈው ሳምንት ላውሮ በኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ ፍሜ ቼልሲ ማንቸስተር ይናይትድን 1 ለ 0 እንደሚያሽንፍ በትክክል ገምቶ ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች