የአፍሪካ በዚህ ሳምንት፡ በድንቅ ፎቶዎች

አፍሪከሰሞኑ እንዴት እንደ ሰነበተች የሚሳዩ ምርጥ ምስሎችን እነሆ

በሶማሊያ መናገሻ ሞጋዲሹ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ፣ በተፈጠረው ጎርፍ መሃል የቤት ቁሳቁሶቹን ቦታ ቦታ የሚያሲዝ ወጣት ይታያል። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በሶማሊያ መናገሻ ሞጋዲሹ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ፣ በተፈጠረው ጎርፍ መሃል የቤት ቁሳቁሶቹን ቦታ ቦታ የሚያሲዝ ወጣት ይታያል።
ይህ ሰው ደግሞ በጎርፍ በተጥለቀለቀው ጎዳና ላይ ለማለፍ በአህያ የሚሳብ ጋሪውን ተጠቅሟል። Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ይህ ሰው ደግሞ በጎርፍ በተጥለቀለቀው ጎዳና ላይ ለማለፍ በአህያ የሚሳብ ጋሪውን ተጠቅሟል።
ይህ በፈረንሳይ ሙዚየም ለዕይታ የቀረበው የጥንቷ ዳሆሚ(የአሁኗ ቤኒን) ግዛተ አፄ የንጉስ ወንበር ነው ።ቤኒን በቅኝ ግዛት ወቅት የተወሰዱ መሰል ቅርሶች እንዲመለሱላት ጥያቄ አቅርባለች። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ይህ በፈረንሳይ ሙዚየም ለዕይታ የቀረበው የጥንቷ ዳሆሚ(የአሁኗ ቤኒን) ግዛተ አፄ የንጉስ ወንበር ነው። ቤኒን በቅኝ ግዛት ወቅት የተወሰዱ መሰል ቅርሶች እንዲመለሱላት ጥያቄ አቅርባለች።
ምስሉ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በምትገኘው ባንዳካ ከተማገበያ ለሸያጭ የቀረበ የዱር እንስሳ ስጋን ያሳያል።ከተማዎ ሰዎች የዱር እንስሳት ስጋን በመብላታቸው ሊባባስ በሚችል የኢቦላ ወረርሽኝ ተመትታለች። Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ምስሉ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በምትገኘው ባንዳካ ከተማ ገበያ ለሸያጭ የቀረበ የዱር እንስሳ ሥጋን ያሳያል። ከተማዋ ሰዎች የዱር እንስሳ ሥጋን በመብላታቸው ሊባባስ በሚችል የኢቦላ ወረርሽኝ ተመትታለች።
አንድ የሴኔጋል ቡድን ደጋፊ የሀገሩን ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለበ ሀገሩ በሩሲያው የዓለም ዋንጫ የሚኖራትን የምድብ ደልድል በሚጠብቅበት ወቅት የተነሳ ምስል ነው። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ አንድ የሴኔጋል ቡድን ደጋፊ የሀገሩን ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለበ ሀገሩ በሩሲያው የዓለም ዋንጫ የሚኖራትን የምድብ ደልድል በሚጠብቅበት ወቅት የተነሳ ምስል ነው።
ጋናዊው ጆሴፍ አፍራን ደግሞ የብሪታኒያ ንጉሳዊ ጋብቻን ለመመልከት ዊንደሶር በተባለ ቦታ ይሄን ማስታወሻ ተነስቷል። Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ጋናዊው ጆሴፍ አፍራን ደግሞ የብሪታኒያ ንጉሣዊ ጋብቻን ለመመልከት በዊንደሰር የተነሳው ማስታወሻ።
ደቡብ አፍሪቃዊቷ ጉብል ደግሞ የሜጋን ማርከል እና የልዑል ሃሪ ጋብቻን በኬፕታውን በሚገኝ ደሳሳ እልፍኝ በቴሌቭዥን ስትከታተል ነበር። Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ደቡብ አፍሪቃዊቷ ጉብል ደግሞ የሜጋን ማርከል እና የልዑል ሃሪ ጋብቻን በኬፕታውን በሚገኝ ደሳሳ ቤት በቴሌቭዥን ስትከታተል ነበር።
ይህ ሰው በአይቮሪኮስታዊ ፀሃፊ ኢፒፋኒ ዞሮ የተደረሰውን መፅሃፍ እያነበበ ነው።መፅሃፉ ከ60ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ስላጡበት የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ አይቱሪ ክልል ይተርካል። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ይህ ሰው በአይቮሪኮስታዊ ፀሃፊ ኢፒፋኒ ዞሮ የተደረሰውን መፅሃፍ እያነበበ ነው። መፅሃፉ ከ60ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ስላጡበት የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ኢቱሪ ክልል ይተርካል።
በአንፃሩ በግብፅ ካይሮ ይሄ ወጣት ከከባዱ ሞቃት ራሱን ለማቀዝቀዝ በማሰብ ራሱን ወደ ውሃ መጨመር መርጧል። Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በአንፃሩ በግብፅ ካይሮ ይሄ ወጣት ከከባዱ ሙቀት እራሱን ለማቀዝቀዝ ውሃ ውስጥ
በናይጄሪያ አብይ ከተማ ሌጎስ ከሰሞኑ የተገደሉ ቀሳውስትን ጨምሮ በሀገሪቱ ዙሪያ ከሰሞኑ ህይታቸውን ላጡት በሙሉ በመንበርከክ ፀሎት አድርሰዋል። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በናይጄሪያ ሌጎስ ከሰሞኑ የተገደሉ ቀሳውስትን ጨምሮ በሀገሪቱ ህይታቸውን ላጡት ሰዎች ፀሎት

Pictures from AFP, Getty Images, Reuters and EPA

በቢቢሲ ዙሪያ