በ90 ሚሊዮን ዶላር የተጠረጠሩ በኬንያ ፖሊስ ተያዙ

የኬንያ ባንዲራ

የኬንያ ብሔራዊ የወጣቶች አገልግሎት ዋና ዳይሬክትር የሆኑት ሪቻርድ ንዱባይ በተቋሙ ውስጥ አጋጥሟል ከተባለ የ90 ሚሊዮን ዶላር መጥፋት ጋር በተያያዘ እየተደረገ ላለው ምርመራ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ትናንት ምሽት ፖሊስ የተቋሙን የሂሳብ ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ 16 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ከመቅረባቸው በፊት ለጊዜው በናይሮቢ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ውስጥ ይገኛሉ።

ተጠርታሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከተለያዩ 10 ድርጅቶች ጋር በተያያዘ በሚሊየን ዶላሮች የሚቆጠር የጨረታ ማጭበርበር እንደተካሄደ የሚያሳይ መረጃ የሃገሪቱ ፍርድ ቤቶች ዋና ሃላፊ ኑርዲን ሃጂ ከደረሳቸው በኋላ ነው።

ገንዘቡ የጠፋው ባለፉት ሦስት ዓመታት ሲሆን፤ ብዙ ምንጮች እንደገለጹት ጉዳዩ በደንብ የተቀነባበረና ብዙ የመንግሥት ሃላፊዎችን ያካተተ ነው።

ይህ የአስር ነጥብ 5 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ መጉደል ፕሬዝዳነት ኡሁሩ ኬንያታ በቅርቡ ለጀመሩት የፀረ-ሙስና ዘመቻ ፈተና ሆኗል።

ተያያዥ ርዕሶች