ኢንዶኔዥያዊቷ ድዛይነር አኔይሳ በማጨበርበር ለእስር ተዳረገች

የፋሽን ዲዛይነሯ አኔይሳ ሃሲቧን Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ አኔይሳ ሃሲቡአን ከፋሽን ዲዛይን ስራዋ በተጨማሪ የጉዞ ወኪልንም ታስተዳድራለች።

በቅርቡ በኒውዮርክ በተካሄደው የፋሽን ዲዛይን ሞዶሎቿን ስካርፍ እንዲጠመጥሙ በማድረግ ታሪክ የሰራችው የፋሽን ዲዛይነር በማጭበርበር ወንጀል የ18 ዓመት እስር ተፈረደባት።

ኢንዶኔዥያዊቷ ዲዛይነር አኔይሳ ሃሲቡአንና ባለቤቷ አንዲካ ሱራችማን በጉዞ ወኪላቸው አማካኝነት ገንዘብ በማጭበርበራቸው ጥፋተኛ ተብለዋል።

አቃቤ ህጉ እንደገለፁት ወደ መካ ለሚደረገው መንፈሳዊ ጉዞ ለማስተባበር ከ 60 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ከፍለዋል።

ይሁን እንጂ ጥንዶቹ ጥፋተኛ የተባሉት ገንዘቡን በማጭበርበራቸውና መንፈሳዊው ጉዞው እንዳይካሄድ እንቅፋት በመሆናቸው ነው።

ዲዛይነሯ በምትሰራቸው ዘመነኛ ድዛይኖቿ የእስልምና ፋሽን መሪ ብለው ይገልጿታል።

በእንግሊዝ፣ በቱርክ፣ በፈረንሳይና አሜሪካ በተካሄዱ የፋሽን ዝግጅቶች ላይ ሥራዎቿን አቅርባለች።

ተያያዥ ርዕሶች