በየቀኑ ወደ ምድር የሚመጡ እንስሳት ቁጥር ሲሰላ ስንት ይሆን?

አእዋፍት፣ ንቦችም፣ ትሎችም ሳይቀሩ ይዋለዳሉ።

ምድራችን ወደ 7.7 ሚሊየን የሚሆኑ እንስሳት መኖሪያ ናት። እነዚህ እንስሳት እንደ ሰው ልጆች በፍቅር ክንፍ ሲሉ ባይታዩም ይዋለዳሉ። ዘር ይቀጥላሉ።

ለመሆኑ በየቀኑ በአለም ዙሪያ ስንት እንስሳት ይወለዳሉ ብለው ያስባሉ?

ቢቢሲ 'ሞር ኦር ለስ' የተሰኘ መርሀ ግብር አለው። ታዲያ ከዝግጅቱ አድማጮች አንዱ አለም በየቀኑ ስንት እንስሳትን ትቀበላለች? ሲል ጠየቀ።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ዘር በመተካት ረገድ ጥንቸሎች ተወዳዳሪ የላቸውም። ከየትኛውም እንስሳ በላቀ ይዋለዳሉ።

እንግሊዝን እንደምሳሌ ብንወስድ የእንግሊዝ የዱር ጥንቸሎች ርቢ 40 ሚሊየን ይደርሳል። አንዲት ጥንቸል ከሶስት ወደ ሰባት ጥንቸሎችን ታፈራለች በሚለው ስሌት በየቀኑ 1,917,808 ጥንቸሎች ይወለዳሉ ማለት ነው።

ሆኖም ከጥንቸሎች ውስጥ ተወለወደው ብዙም ሳይቆዩ የሚሞቱ አሉና አለም ከምትቀበላቸው ጥንቸሎች ብዙዎቹን ታጣለች።

በአንዳንድ አካባቢዎች ብቻ ተወሰወነው የሚኖሩ ብርቅዬ እንስሳትን ደግሞ እንመልከት።

በቺሊና ፔሩ የሚኖሩት ሀምቦልት ፔንግዊኖች ጥሩ ምሳሌ ናቸው።

የፎቶው ባለመብት, ZSL

እነዚህ እንስሳት የሚራቡት እንቁላል በመጣል ነው። በአንዴ የሚጥሉት ሁለት እንቁላል ሲሆን፣ እያንዳንዳቸው በአመት ሁለት እንቁላል ይጥላሉ።

ስለዚህም በቀን 40 ሀምቦልት ፔንግዊኖች እንዲሁም በአመት 14,400 ይጣላሉ።

ወደ ዶሮ አለም እንዝለቅ። የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ዘርፍ ክፍል በቀን 62 ሚሊየን ዶሮዎች ወደ ምድር ይመጣሉ ይላል።

በአንጻሩ ንቦች በሞቃትና በቀዝቃዛ ወቅት ዘራቸውን የሚተኩበት ፍጥነት ይለያያል። በሞቃት ወራት ንግስቲቷ ንብ በየቀኑ 1,500 እንቁላል ትጥላለች።

ባጠቃላይ ሞቃታማ ጊዜ ላይ 371,191,500 እንቁላል ይጥላሉ።

የፎቶው ባለመብት, Science Photo Library

በለንደን ዙስ ኢንስቲትዪት ኦፍ ዙኦሎጂ የምትሰራው ሞኒካ ቦሀም እንደመሚሉት የእንስሳትን አለም ከሀ እስከ ፐ ማወቅ አልተቻለምና ስለሚራቡበት መንገድ የተሟላ መረጃ የለም።

የክዊን ሜሪ ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር ኣክሰል ሮስበርግ በበኩሉ የእንስሳት አካል ግዝፈት ከሚራቡበት መጠን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው ይላሉ።

ጥቃቅን እንስሳት በብዛት ሲራቡ ግዙፎቹ የሚወዋለዱበት ፍጥነት ዝግ ይላል።

በፕሮፌሰሩ ስሌት መሰረት በምድር ላይ ካሉ ዝሆኖች የንቦች መጠን ይበልጣል ማለት ነው።

ለምሳሌ ኔማቶድ የተባሉት አነስተኛ ትሎች ከመጠናቸው ትንሽነት አንጻር በአንድ ካሬ ሜትር ሶስት ሚሊየን ይገኛሉ።

የፎቶው ባለመብት, Science Photo Library

የምስሉ መግለጫ,

በአንድ ካሬ ሜትር ሶስት ሚሊየን ኔማቶዶች ይገኛሉ

ከትሉ ዝርያዎች መሀከል በአንድ ሰአት አምስት እንቁላል የሚጥለው ይጠቀሳል።

ከ100 እንቁላሎች አንዱ ስለሚፈለፈል በየቀኑ 600 ካትሪልየን ይወለዳሉ ማለት ነው።

የተለያዩ ዝርያዎች በየቀኑ ወደ ምድር የሚያመጧቸውን እንስሳት ብንደምር ያጠቃላይ እንስሳት ቁጥር ላይ መድረስ ይቻላል።