በአንድ ጀንበር ሁለት ሚስት ያገባው ጎረምሳ

ባሺር ሙሐመድ ይባላል። ድል ባለ ሠርግ ሁለት ሚስቶችን በአንድ ቀን በማግባቱ መነጋገሪያ ሆኗል።

ባሽር ለቢቢሲ እንደተናገረው ወንዶች የኔን ተምሳሌት እንዲከተሉ አበረታታለሁ ብሏል።

አስገራሚው ነገር ባሺር ሁለቱን ሴቶች ከትዳር በፊትም ቢሆን አንድ ላይ ነበር የሚጋብዛቸው።

"ለአንደኛዋ እንኳ አዳልቼ አላውቅም። እኩል 'እወዳችኋለሁ' ነው የምላቸው" ሲል ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ ተናግሯል።

በሽር እንደሚለው በተመሳሳይ ጊዜ ሁለት ሴት ማፍቀርና ማግባት ኋላ በሚስቶች መሐል መቀናናትን ያስወግዳል።

በሽር ለምን ሁለት ሴት ማግባት እንደፈለገ ሲጠየቅ በርካታ ልጆችን ማፍራት በመፈለጉ እንደሆነ ተናግሯል።

ሌሎች ወንዶችም አቅሙ ካላቸው እንደኔው ቢያደርጉ መልካም ነው ብሏል።

በርከት ያሉ ሚስቶችን ማግባት በሶማሊያ ባሕል የተለመደ ቢሆንም በአንድ ቀን ከሁለት ሴቶች ጋር ትዳር መመሥረት ግን እንግዳ ነገር ነው።

የበሽር ሚስቶች ኢቅራ እና ኒሞ ይባላሉ።