ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ተወያዩ

የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳዉድ ኢብሳ Image copyright ONN
አጭር የምስል መግለጫ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳዉድ ኢብሳ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኤርትራ ጉብኝታቸው ወቅት ከኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውዲ ኢብሳ ጋር ተገናኘተው ተወያይተዋል።

የግንባሩ ቃል-አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ ለቢቢሲ እንደገለፁት ''ሁለቱ አካላት ፊት ለፈት ተገናኘተው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከተወያዩ በኋላ በመርህ ደረጃ ተግባብተዋል'' ብለዋል።

አቶ ቶሌራ ጨምረው እንደተናገሩት ሁለቱ አካላት ካገር ውጭ ውይይታቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል።

ውይይቱ የት እና መቼ ይካሄዳል ተብሎ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄም ውይይቱ በቅርብ ቀን እንደሚካሄድ አቶ ቶሌራ ገልፀወው ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የኦነግ እና መንግሥት ተወካዮች በሚገናኙበት ወቅት በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮችም ላይ እንደሚወያያዩ አቶ ቶሌራ ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር ማንሳቱ ይታወሳል።

ምክር ቤቱ ከዓመታት በፊት እነዚህን የፖለቲካ ድርጅቶችን ጨምሮ አልቃይዳንና አልሻባብን በአሸባሪነት መፈረጁ የሚታወስ ነው።

ፓርላማው የኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 የሽብርተኝነት ፍረጃ መነሳትን አፀደቀ

ከሳምንታት በፊትም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደግብፅ አምርተው ከፕሬዝዳንት አልሲሲ ጋር ከተወያዩ በኋላ የኦነግ ከፍተኛ አመራር የነበሩትን ኮሎኔል አበበ ገረሱን እና የአህዴድ መስራቸ የነበሩትን አቶ ዮናታን ዲቢሳን ወደ አገር ቤት ይዘው ገብተዋል።

በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ