የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አባት አቶ አህመድ አሊ፡ "አብዮት ነበር ስሙ። ዐብይ ሁን ብዬ ዐብይ ስል ሰየምኩት''

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አባት አቶ አህመድ አሊ፡ "አብዮት ነበር ስሙ። ዐብይ ሁን ብዬ ዐብይ ስል ሰየምኩት''

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወላጅ አባት አቶ አህመድ ዓሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ቢቢሲ ከቅርብ ቤተሰብና ከአካባቢው ኮምዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት እንዳረጋገጠው አቶ አህመድ ዓሊ ያረፉት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ነው። ቢቢሲ ለመላው ቤተሰባቸው መጽናናትን ይመኛል።

ቢቢሲ የዛሬ አንድ ዓመት ገደማ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የትውልድ ቀዬ በሻሻ አምርቶ አባታቸውን፣ ወንድሞቻቸውንና ጓደኞቻቸውን አግኝቶ ነበር።