የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ማወጁን ገለፀ

የኦነግ ወታደሮች Image copyright Jonathan Alpeyrie

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኤርትራ ቆይታቸው ከኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ድርጅቱ ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ማወጁን የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ ደባ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በኤርትራ ተቀማጭነቱን ያደረገው ድርጅት ካለው ለውጥጋር ተያይዞ ጦርነት እንደማያስፈልግ መረዳታቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

መንግሥት ከኦነግ ጋር ካገር ውጭ ሊወያይ ነው

በሰላም ትግላቸውንም ለመቀጠል እንደወሰኑ የሚናገሩት አቶ ቶሌራ ከመንግሥት ጋር የሚደረገውም ውይይትም በቅርቡ ይቀጥላል ብለዋል።

ግንባሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫም የተጀመሩት ውይይቶች ጥሩ ለውጥ እንደሚያመጡ እምነታቸውን ገልፀው በአጠቃላይ በኦሮሚያ ክልል ጊዜያዊ ተኩስ አቁም እንዲተገበር መወሰናቸውን ገልፀዋል።

ፓርላማው የኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 የሽብርተኝነት ፍረጃ መነሳትን አፀደቀ

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ