ተዘግቶ ለ20 ዓመታት በቆየው የኤርትራ ኤምባሲ ውስጥ ምን ተገኘ?

ቢራ፣ ወይንና የወይራ ዘይት የያዙ ጠርሙሶችም ተገኝተዋል
አጭር የምስል መግለጫ ቢራ፣ ወይንና የወይራ ዘይት የያዙ ጠርሙሶችም ተገኝተዋል

በ1990 የድንበር ጦርነቱ ሲቀሰቀስ አዲስ አበባ ውስጥ ለሁለት አስርታት ተዘግቶ ከቆየው የኤርትራ ኤምባሲ በሮች በኤርትራ ባለስልጣናት ሲከፈት ክፍሎች ውስጥ በአቧራ የተሸፈኑ መኪኖች፣ የቤት ውስጥ እቃዎች እና የተለያዩ መጠጦች ባሉበት ተገኝተዋል።

ጦርነቱ በ1992 ቢያበቃም ግንኙነታቸው ሻክሮ እስካሁን ድረስ ቆይቶ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ኤርትራ መጓዛቸውን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ነው ኤምባሲው መልሶ የተከፈተው።

እነዚህ ፎቶግራፎች የኤርትራ ኤምባሲ ዛሬ ሲከፈት በቢቢሲ የተነሱ ናቸው።

እነዚህ መኪኖች በኤምባሲው ውስጥ ከሃያ ዓመታት በላይ ባሉበት ቆይተዋል
አጭር የምስል መግለጫ እነዚህ መኪኖች በኤምባሲው ውስጥ ከሃያ ዓመታት በላይ ባሉበት ቆይተዋል
እነዚህ ወንበሮች የመጨረሻው የኤርትራ አምባሳደር ይገለገሉበት ነበር
አጭር የምስል መግለጫ በእነዚህ ወንበሮች የመጨረሻው የኤርትራ አምባሳደር ይገለገሉበት ነበር
በኤምባሲው ክፍሎች ውስጥ ከተገኙ የቤት መገልገያዎች ውስጥ ይህ አልጋ ይገኝበታል።
አጭር የምስል መግለጫ በኤምባሲው ክፍሎች ውስጥ ከተገኙ የቤት መገልገያዎች ውስጥ ይህ አልጋ ይገኝበታል።
የኤምባሲው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የታደሙ የማርሽ ሙዚቃ ቡድን አባላት
አጭር የምስል መግለጫ የኤምባሲው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የታደሙ የማርሽ ሙዚቃ ቡድን አባላት
ፕሬዝዳንት ኢሳያስና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የኤምባሲውን የውስጥ ክፍል ሲመለከቱ
አጭር የምስል መግለጫ ፕሬዝዳንት ኢሳያስና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የኤምባሲውን የውስጥ ክፍል ሲመለከቱ
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተገኙበት የኤርትራን ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ከ20 ዓመታት በኋላ ኤምባሲውን ከፍተዋል
አጭር የምስል መግለጫ ፕሬዝዳንት ኢሳያስና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተገኙበት የኤርትራን ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ከ20 ዓመታት በኋላ ኤምባሲውን ከፍተዋል

የፎቶግራፎቹ ባለቤትነት መብት በሕግ የተጠበቀ ነው

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ