«ከእወደድ ባይ ፖለቲከኞች ተጠንቀቁ» ባራክ ኦባማ

«ከእወደድ ባይ ፖለቲከኞች ተጠንቀቁ» ባራክ ኦባማ Image copyright AFP

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ከፍ ባለ መድረክ ላይ አሰሙት የተባለው ንግግር ብዙዎችን አስደንቋል። ንግግራቸው አሁን አሜሪካ ውስጥ ሥልጣን ይዞ ያለውን መንግሥት በሾርኔ ወጋ ለማድረግ የተጠቀሙበት ነው እየተባለ ይገኛል።

15 ሺህ ያህል ሰው በታደመበትና የደቡብ አፍሪቃውን የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላን ለመዘከር በተዘጋጀው መድረክ ላይ ንግግር ያሰሙት ኦባማ የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መነጋገሪያም ሆነው ነበር።

እስቲ ኦባማ ካሰሙት ንግግር መካከል አምስት አበይት ነጥቦች መርጠን ወደእናንተ እናድርስ።

ማንዴላን ውትድርና ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ

፩. እውነት የተቀደሰች ናት

«በእውነታ ልታምኑ ይገባል» አሉ ኦባማ፤ «እውነታውን መሠረት ያላደረገ ነገር ለትብብር አይገፋፋምና።»

«እኔ ይሄ አትሮነስ ነው ስል፤ 'አይ አቶ ኦባማ ተሳስተዋል እንዴት ዝሆኑን አትሮነስ ይሉታል' ካላችሁኝ ነገር ተበላሸ ማለት ነው።»

በተመሳሳይ ርዕስ ላይ የቆዩት ኦባማ በአየር ንብረት ለውጥ የማይስማሙ ሰዎች ጋር መስማማት ሊከብዳቸው እንደሚችል ጠቁመዋል።

ተቀማጩ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ሃገራቸውን ማግለላቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

የዐብይ ቀጣይ ፈተናዎች

፪. ስደተኞች ጥንካሬ ናቸው

ኦባማ ብዙ ስብጥር ያለው ማሕበረሰብ አቅሙ የዳበረና ስጦታ የታከለበት ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

«እስቲ የፈረንሳይ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድንን ተመለክቱት» ሲሉ ጎዜ የአዳራሹ ጣራ ጭብጨባ ሊሰጠነቅ ሆነ።

«የቡድኑ አባላት ስትመለከቷቸው ሁሉም ጎል (ምዕራብ አውሮጳዊ) አይመስሉም፤ ግን ፈረንሳውያን ናቸው።»

«ሆኖም አሁን ባለንበት ጊዜ እንኳን ዘርን መሠረት ያደረጉ ማግለሎች በሃገረ አሜሪካም ይሁን በደቡብ አፍሪቃ በሰፊው ይንፀባረቃሉ።»

Image copyright Getty Images

፫. ቱጃሮች ከሌላው ተነጥለው የሚኖሩ ናቸው

ኦባማ «ዓለማችን 'ልጥጥ' ሃብታሞች ከደሃው ማሕበረሰብ ተነጥለው የተለየ ኑሮ የሚኖሩባት ናት» ሲሉም ተደምጠዋል።

«ቱጃሮቹ ሲያስቡ የሚውሉት የሚያድሩት ስለሚያስተዳድሩት ድርጅት እንጂ ስሌላ ነገር አይደለም፤ ከሚኖሩባት ሃገር ጋር ያላቸውም ቁርኝት እጅግ የላላ ነው። ለእነሱ አንድ ድርጅትን መዝጋት ማለት ከትርፍና ኪሳራ አንፃር የሚታእ አንጂ ሌላው ላይ ከሚኖረው ተፅዕኖ አኳያ አይደለም።»

ኦባማ እና ቡሽ ትራምፕን ተቹ

፬. ድል ለዲሞክራሲ

«ፍራቻን፣ ቂም በቀልንና ማስወገድን እንደ ፖለቲካ መሣሪያ የሚጠቀሙ ፖለተከኞች አሁን ላይ ቁጥራቸው እጅግ እየላቀ መጥቷል» ሲሉ ኦባማ ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል።

«ዴሞክራሲ ልሙጥሙጥ ነው» ያሉት ኦባማ «ሃሰት የተመላ ቃል የሚገቡ ፖለቲከኞች ደግሞ አምባገነኖች ናቸው» በማት ወርፈዋል።

«ጊዜው ከኛ በላይ ወዳሉት የምንጋጥጥበት ሳይሆን ወደታች ዝቅ ብለን የምንሠራበት ነው፤ ዲሞክራሲ ያለው እዚያ ነውና።»

«ከሕዝባዊ ፖለቲከኞች ተጠንቀቁ» ሲሉ ያስጠነቀቁት ኦባማ «ነፃ ዴሞክራሲ ለሰብዓዊው ፍጡር ቅድሚያ የሚሰጥ ነው» በማለት አክለዋል።

«አኔ በኔልሰን ማንዴላ ርዕይ አምናለሁ፤ በመሰል ሰዎች የሚመራ ዓለም የተሻለ እንደሆነም አስባለሁ።»

ኤርትራዊያን የሚሿቸው አምስት ለውጦች

፭. ሁሌም ተስፋ እንሰንቅ

«በእምነታችሁ ፅኑ፤ ሁሌም ወደፊት ሂዱ፤ ማነፃችሁን አታቁሙ፤ ድምፃችሁን አሰሙ። ሁሉም ትውልድ ይህችን ዓለም የተሻለች የማድረግ ዕድል አለው» ኦባማ ንግግራቸውን ወደ መቋጨቱ ሲጠጉ የተናገሩት ነው።

በጭብጨባና ፉጨት አጅቦ ሲያዳምጣቸው ለነበረው ወጣት ለሚበዛው ታዳሚ «እንነሳ» የሚል ድምፅ አሰምተዋል።

«አንድ መሪ ብቻ አይበቃንም፤ እጅጉን የሚያስፈልገን የጋራ ትብብር ነው።»

«ማንዴላ 'ወጣቶች የጭቆና ማማን ደርምሰው የነፃነት አርማን የመስቀል ኃይል አላቸው' ብለውናል፤ ይህንን ተግባራዊ የማድረጊያው ጊዜ አሁን ነው።»

ኦባማ የማንዴላ 100ኛ ዓመት ክብረ በዓልን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሥነ-ሥርዓት ላይ ይህንን ንግግር ያሰሙት።

ኦባማም ሆነ ማንዴላ በሃገራቸው የመጀመሪያዎቹ ጥቁር ፕሬዝደንቶች ናቸው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ