ቻይና በግዙፎቹ ማሽኖቿ ዓለምን እንድታገናኝ እያደረጉ ነው

ቁጥር እና እውነታዎች

ቻይና በታሪክ ግዙፍ የሆነው የመሠረተ ልማት ሥራ ላይ ከመሰማራት ባለፈ ባቡሮች የሚገነቡበትን መንገድም እየለወጠች ነው።

በፍጥነት እያደገ የሚገኘውን ኢኮኖሚዋን ለማሳለጥ ቻይና በየብስ እና ባህር ከአፍሪካ እና አውሮፓ ጋር ለማገናኘት ተስፈኛ ዕቅድ ይዛለች።

እአአ 2013 የተጀመረው የፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ተስፈኛ ዕቅድ የዓለማችንን አንድ ሶስተኛ የሚሆኑ ሰባ አገራትን በየብስ በባህር ማገናኘትን ያለመ ነው።

ሁሉንም በደህንነት ካሜራ የምትመለከተው ቻይና

የቻይና የዕርዳታ ሚስጢር ሲገለጥ

ከባንኮች፣ ከተሳታፊ አገራትና ከቻይና መንግሥት በሚሰበሰበው በትሪሊዮን ዶላሮች በሚገመት ወጪ የሚከናወነው ግንባታ ዘመን ተሻጋሪ ኢንቨስትመንት እንደሆነ እየተወራለት ነው።

ይህ ዕቅድ የማይሳካ ቢመስልም የዚህ የግዙፍ ማሽኖች ግንባታ መዋዕለ ንዋዩ ፍሰት በቻይናና እና በሌሎችም አካባቢዎች እየታየ ነው።

የድልድይ ግንባታ

በስምጥ ሸለቆዎችና ጠመዝማዛ ቦታዎች ላይ እንዴት ፈጣን የባቡር መስመር ዝርጋታ ሊካሄድ ይችላል?

ድልድይን ከድልድይ የሚያገናኘው ኤስ ኤል900/32 ማሽን ግዙፉ ብረት ገጣጣሚ።

ኤስ ኤል ጄ ሁሉንም በአንድ ያጠቃለለ ማሽን ሲሆን አንድን ማዕዘን ከሌላኛው ማዕዘን ጋር የሚያያይዙ የድልድይ ክፍሎችን መሸከም፣ ማንሳትና ማስቀመጥ የሚችል ነው።

SLJ900"፡ ''ብረት ገጣጣሚው''

 • ክብደት: 580 ቶን

 • ርዝመት: 92 ሜትር

 • ቁመት: 9 ሜትር

 • ጭነት ሳይዝ የሚኖረው ፍጥነት: 8ኪ.ሜ/በሰዓት

 • ጭኖ የሚኖረው ፍጥነት: 5ኪ.ሜ/በሰዓት

CHINA RAILWAY 11 BUREAU GROUP

92 ሜትር የሚረዝመው እና 64 ጎማዎች ያሉት ማሽን አንዱን የድልድይ ክፍል ካስቀመጠ በኋላ፤ የሌላ ድልድይ ክፍል ለመውሰድ ይመለሳል። በዚህም ቀደም ሲል ያስቀመጠው ድልድይ ክፍል ላይ ይሄዳል።

የቻይናውያንን ኑሮ ለማወቅ አምስት ነጥቦች

ማሽኑ ወደ ጎንም የመሄድ ብቃት ያለው ነው።

ሙሉ ጭነት ተሸክሞም በሰዓት 5 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይችላል። ይህም ሙሉ ሂደቱ ብዙ እቃ ማንሻ ክሬኖችን በመጠቀም ከመሬት ይሰራበት ከነበረው ባህላዊው አሠራር የፈጠነ ያደርገዋል።

580 ቶን ጭኖ ቀደም ሲል ባስቀመጠው ድልድይ ክፍል ላይ አለፈ ማለት ደግሞ ድልድዩ ከመደበኛው ባቡር መስመር የመሸከም ብቃት በላይ መሆኑን ያሳያል።

ይህ ማሽን ከወዲሁ ብዛት ያላቸው ፈጣን የባቡር መስመር ዝርጋታዎች ላይ ጥቅም ላይ ውሏል። ከእነዚህ ውስጥ በ2020 ቻይና 30 ሺህ ኪሎ ሜትር የፈጣን ባቡር ባለቤት ለመሆን ያላእ ዕቅድ አካል የሆነው የቻይና ማዕከላዊ ሞንጎሊያ ባቡር መስመር አንዱ ነው።

የዋሻዎች ቁፋሮ

ከሆንግ ኮንግ ብዙም በማይርቀውና በስተደቡብ በሚገኘው ሱአይ ሃይዌይ በሚሰኘው የሻንቱ ፕሮጀክት በአንዴ ስድስት መኪና የሚያስተናግድ 5 ኪሎ ሜትር የዋሻ መንገድ ለመገንባት ተስፈኛ ዕቅድ ተቀምጧል። መንገዱ የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጠቃው አካባቢ የሚሠራ ነው።

ዋሻው በ2019 ሲከፈት ሻንቱን ከወደብ ጋር በማገናኘት የትራንስፖርት ዘርፉን ያዘምነዋል ሲሉ ባለስልጣናት ያምናሉ። መንገዱ ቁልፍ ከሆኑ 15 የወደብ መስመሮች መካከል አንዱ ነው።

አንድ የጀርመን አምራች የሰራው ዋሻ ቦርቧሪ ማሽን በዘርፉ ፈር ቀዳጅ ከሆኑት መካከል ይመራ ነበር። ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቻይና ኩባንያዎች ክፍያ እየፈጸሙ ስመጥር ሆኑ ድርጅቶች የዋሻ ቦርቧሪ ቴክኖሎጂውን ለመጠቀም የሚያስችል ፈቃድ እያደረጉ ነው።

በውጤቱም 15.3 ሜትር ስፋት ያለው ዋሻ ቦርቧሪ ማሽን በቻይና ሬይልዌይ ኢንጂነሪንግ ኢኪውፕመንት ግሩፕ ካምፓኒ ከተባባሪ የጀርመን መሃንዲሶች ጋር ስራ መጀመራቸውን በ2017 ይፋ አድርገዋል።

15.3 ሜትር ቲቢኤም ስለሪ

የቻይና የባቡር መንገድ ምህንድስና አቅራቢዎች ኩባንያ

 • የክበቡ አጋማሽ: 15.3 ሜትር

 • ርዝመት: 100 ሜትር

 • ክብደት: 4,000 ቶን

 • የሱዓኢ የዋሻ ውስጥ መተላለፊያ ሲጠናቀቅ የሚኖረው ርዝመት፡ 5 ኪ.ሜ

STDAILY.COM

እንደጀርመን አጋሮቻቸው ማሽኖቹ ከፊት ለፊት የሚሽከረከሩ ጠፍጣፋ መቁረጫ ያላቸው ሲሆን ይህም መሬትን ሆነ አለቶችን ለመሰርሰር የሚያስችል ነው።

4 ሺህ ቶን ሚመዝን ሲሆን መቶ ሜትር ድረስ ማሽኖችን ማስከተል ይችላል። ይህ ደግሞ መሣሪያው እቦረቦረ በሚሄድበት ወቅት የዋሻውን ግድግዳ እግር በእግር እተከተሉ ለመስራት የሚያስችላቸው ነው።

ከመቦርቦሪያው ማሽን የሚወጣ አፈርና ስብርባሪዎች ተሰብስበው ዝቃጩ በቱቦ አማካኝነት ይወገዳል። ማቀላቀያው ፍርስራሹን ከሸክላ ጋር በማዋሃድ ዝቃጩ እንዲፈጠር ያደርጋል።

ሰፊው መቦርቦሪያ ማሽን አይደለም። በዚህ ዘርፍ ቀዳሚ ሸላሚው ቤርታ ነው። ቤርታ 17.4 ሜትር ስፋት ያለው ማሽን ለሲያትሉ አላስካን ዌይ ገንብቷል።

ሆኖም 15.3 ሜትር መሠራቱ በራሱ ቻይና በዋሻ ግንብታ ውሰጥ ቁልፍ ሚና ለመጫወት ስለማቀዷ ማሳያ ነው።

የሃዲድ ዝርጋታ

የቤልት እና ሮድ ኢኒሽዬቲቭን መሠረት በመላው ቻይና የተጣለ ሲሆን በቻይና ድጋፍ የሚሰሠሩ ፕሮጀክቶች በሺህ ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ ተግባራዊ መደረግ ጀምረዋል።

የኬንያው የሞምባሳ-ናይሮቢ የባቡር መስመር ግንቦት 2017 ሲጠናቀቅ ዓለም አቀፍ ትኩረትን የሳበው መጠናቀቅ ከነበረበት በ18 ወራት ቀደም ብሎ ሥራ በመጀመሩ አይደለም።

480 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ባቡር መስመር ሃገሪቱ ነጻነቷን ካገኘች በኋላ መጀመሪያዋ ነው።

90 በመቶ ሚሆነው የግንባታው ገንዘብ ከቻይናው ኤግዚም ባንክ የተገኘው ነው። መስመሩ ከቻይና ውጭ በሀገሪቱ የግንባታ መስፈርት እና በሃገሪቱ ማሽኖች የተሰራ የመጀመሪያው የባቡር መስመር ነው።

መስመሩ እንዴት 700 ሜትር በቀን በሚፈጥን ጊዜ እንደተሰራ ለማወቅ ሃዲዱን የሚዘረጋውን ማሽን መመልከት አስፈላጊ ነው።

ሃዲድ የሚደረድር ማሽን

የቻይና የመንገድ እና ድልድይ ኮርፖሬሽን

 • በቀን ሊዘረጋ የሚችለው ርቀት: 700 ሜትር

 • ስህተት ሊኖር የሚችለው: 2 ሴ.ሜትር

 • የአንዱ ማሽን ክፍል ክብደት: 15 ቶን

 • የአንዱ ማሽን ክፍል ርዝመት: 25 ሜትር

CHINA ROAD AND BRIDGE CORP

ሃዲድ የሚዘረጋው ማሽን የተመረተ የባቡር ሃዲድ ያስቀምጥና ባስቀመጠው ሃዲድ ላይ በመጓዝ አዲስ የባቡር ሃዲድ ያስቀምጣል።

ይህ ከተከናወነ በኋላ አጭር ሆነው የተገጣጠሙት የባቡር ሃዲዶች በረዣዥሙ እንዲያያዙ በማድረግ የባቡሩ ጉዞ የተቃና እንዲሆን ያደርጉታል።

እያንዳንዱን የባቡር ሃዲድ ክፍል ለመግጠም አራት ደቂቃ ብቻ በቂ ነው።

ይህ አዲስ ሃሳብ ሳይሆን ለአስር ዓመታት በብዙ ሃገራት ተግባራዊ ሲደረግ የቆየ ነው። ሆኖም ቻይና በፍጥነት መሥራቱን ቻለችበት። ለዚህ ደግሞ የረዳት በፍጥነትና በርካሽ ዋጋ ማሽኖችን ከመስራት ባለፈ ከፍተኛ ክብደት ያለው የባቡር ሃዲድ ክፍል እንዲሸከሙ በማድረግ ነው።

ማሽኖቹ እጅግ ዘመናዊ ቢሆኑም አሁንም ቢሆን ከፍተኛ ሰው ጉልብት የሚጠይቁ ናቸው።

የአካባቢው ሠራተኞች በቻይና መሃንዲሶች በመታገዝ በባቡር መስመሩ አካባቢ ባሉት ጊዜያዊ ፋብሪካዎች ውስጥ የባቡር ሃዲዱን የተወሰነ ከፍል ይሠራሉ።

ከዚህ በተጨማሪ የባቡር ሃዲዱ ክፍሎች በትክክለኛው መጠን መሠራታቸውን ይቆጣጠራሉ። ስህተት ሊፈጠር የሚችለው 2 ሴንቲ ሜትር ላይ ብቻ ነው።

በደህንነታቸው ዙሪያ ስጋቶች አሉ። "በሥራ ቦታ ሚከሰቱ አደጋዎች የሚኖሩ ናቸው" ሲሉ በሞምባሳ-ናይሮቢ የባቡር መስመር ላይ የሚሠሩ አንድ ቻይናዊ ከፍተኛ መሃንዲስ ባለፈው ዓመት ለዢኑዋ አስታውቀዋል።

"በሚከሰቱበት ወቅት ከፍተኛ ከመሆናቸውም በላይ አንዳንዴ እስከ ሞት የሚያደርሱ ናቸው።"

ሆኖም እስካሁን ባለው ሁኔታ የቻይና ባቡር መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክቶች በአፍሪካ ሃገራት ያላቸው ተቀባይነት ከፍተኛ ነው።

የናይሮቢ-ሞምባሳ ባቡር መስመር በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ጊዜ የተሰራውንና 10 ሰዓት የሚፈጀውን የመኪና መንገድ ጉዞ ወደ 4 ሰዓታት የቀነሰ ነው። እስከ የካቲት ድረስ ብቻ 870 ሺህ መንገደኞች ባቡሩን ተጠቅመዋል።

ምስጋና ለኤግዚም ባንክ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ይግባውና መስመሩን በምዕራብ የሃገሪቱ ክፍል የምትገኘው ኪሱሙ ድረስ ለማድረስ ስራዎች ከወዲሁ ተጀምረዋል። ይህም ዩጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያን የሚያገኛኝ ነው።

እነዚህ ትልልቅ ማሽኖች እውን ያደረጉትን የግንባታ ፍጥነት ከግምት በማስገባት ሁሉም ነገር በእቅዱ መሠረት ከተሠራ ኬንያ በቻይና ድጋፍ የተሰራው የምስራቅ አፍሪካ የባቡር መሥመር ማዕከል ለመሆን ረዥም ጊዜ አይፈጅባትም።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ