አፍሪካ ያሳለፈችው ሳምንት በፎቶ ካሜራ አይን ምን ይመስል ነበር? ከዓለም ዋንጫ እስከ ባራክ ኦባማ ጉብኝት

የአህጉረ አፍሪካ ውብ ፎቶዎችና ከመላው ለም የተውጣጡ የአፍሪካውያን ምስሎች

የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ተከላካይ ፕሬስናል ኪምፔቤ የ2018 የሩስያ አለም ዋንጫ ድልን ዋንጫውን በመሳም አጣጥሟል። የዋንጫ ፍልሚያው በፈረንሳይና ክሮሽያ መሀከል ነበር። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የፈረንሳይ ዓለም ዋንጫ ድል የአፍሪካም ነው ተብሏል፤ ከፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን አባላት አብዛኞቹ የእናት አፍሪካ ልጆች ናቸውና።
በፈረንጆች ጁላይ 16፣ 2016 ኬንያውያን በኮጌሎ ግዛት ውስጥ የአሜሪካን ሰንደቅ አላማ ይዘው ይታያሉ። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ወደ አባታቸው የትውልድ ቀዬ ዳግመኛ ሲያቀኑ ኬንያዊያን ሞቅ ደመቅ አድርገው ተቀብለዋቸዋል።
የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲው ራይላ ኦዲንጋና የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማና የሚያሳይ ፎቶ በአንገታቸው ያጠለቁ መነኩሴ። Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ እኚህ መነኩሴ ለባራክ ኦባማ ድጋፋቸውን ከማሳየት ያገዳቸው የለም። ኦባማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዕከል እስኪከፍቱ በጉጉት ይጠባበቁ ነበር።
በፈረንጆች ጁላይ 18፣ 2018 ኖርልተን የተባለ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ አንድ ታዳጊ የኔልሰን ማንዴላን ምስል ጠቁር ሰሌዳ ላይ ሲሰቅል። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ እለተ ረቡዕ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ መሪ ኔልሰን ማንዴላ 100ኛ ዓመት የልደት በዓል ተከብሯል። በደቡብ አፍሪካ፤ ደርባን የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ቀኑን ዘክረዋል።
ሱድርሸን ፓትናይክ የተባለ ህንዳዊ አርቲስት አሸዋ ላይ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ኔልሰን ማንዴላን ሲቅርጽ ይታያል። በፈረንጆች ጁላይ 18፣ 2018 የተሰራው የአሸዋ ቅርጽ የጎብኚዎችን ትኩረት ይስባል በሚል ፑሪ ውስጥ የቆመው የማንዴላን 100ኛ ዓመት ልደት በዐል ምክንያት በማድረግ ነው። Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ፑሪ ከተማ ወስጥ በአሸዋ የሚጠበብ ሙያተኛ የአድልዎ አገዛዝን የተዋጉትን የኔልሰን ማንዴላ ምስል በአሸዋ ግግር ቀርጿል።
በፈረንጆቹ ጁላይ 18፣ 2018 ጋዎ፣ ማሊ ውስጥ ግመል የሚጋልቡ ሰዎች Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በሰሜናዊ ማሊ ጋዎ ውስጥ የምርጫ ቅስቀሳ የተደረገው በግመል ጋላቢዎች ነበር።
በፈረንጆቹ ጁላይ 15፣ 2018 በሞሮኮ፣ ራባት የተካሄድ ተቃውሞ ተሳታፊዎች Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ የሞሮኮን መንግሥት በመቃወም ለእስር የተዳረጉ ሞሮኳዊያን እንዲፈቱ እሁድ እለት በመዲናዋ ራባት ሰልፍ ተካሄዶ ነበር።
በፈረንጆቹ ጁላይ 14፣ 2018 አይቮሪኮስት ውስጥ ሰዎች እስከወገባቸው በጎርፍ ተጥለቅልቀው ይታያል። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ቅዳሜ እለት በአይቮሪኮስት የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የደቡባዊት አይቮሪኮስት አቤሶ ነዋሪዎች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል።
በፈረንጆቹ ጁላይ 13፣ 2018 ግብጽ ውስጥ አንድ የፖሊስ ኃላፊ በባቡር ፊት ለፊት ቆሞ ይታያል። Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ አንድ የፖሊስ ኃላፊ አርብ እለት ከግብጽ መዲና ካይሮ የተነሳን ባቡር ሲጠብቅ።
በፈረንጆቹ ጁላይ 14፣ 2018 ናይጄሪያዊ ድምጻዊ ሰኡን ኩቲ ከባንዱ ጋር ስፔን ውስጥ ሲያቀነቅኑ። Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ስፔን በሚገኝ ተንሳፋፊ መድረክ ላይ ናይጄሪያዊው ድምጻዊ ሰኡን ኩቲ ከባንዱ ጋር ቅዳሜ እለት አቀንቀኗል።

Images from AFP, EPA, Getty Images and Reuters.

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ

በቢቢሲ ዙሪያ