ይህ የአፍሪካ ዋነኛው የፈጠራ አካባቢ ይሆን?

በርናርድ ኪዊያ የታንዛንያው የፈጠራ ትምህርት ቤት ትዌንዴ መስራች ነው
አጭር የምስል መግለጫ በርናርድ ኪዊያ የታንዛንያው የፈጠራ ትምህርት ቤት ትዌንዴ መስራች ነው

በርናንድ ኪዊያ ከብስክሌት እጅግ ብዙ ነገር መስራት ይችላል።

መጀመሪያ የታወቀው በብስክሌት የሚሰራ የተንቀሳቃሽ ስልክ ባትሪ መሙያ (ቻርጀር) በመፍጠር ነው።

በርናንድ ከብስክሌት መለዋወጫ እቃዎች በርካታ ተጨማሪ ነገሮችን መስራት እንደሚችል በኋላ ላይ ቢገነዘብም ሥራ የጀመረው የብስክሌት መካኒክ ሆኖ ነው።

"አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የምፈጥረው ቤተሰቤን እና ማህበረሰቡን የሚጠቅም ነገር መሆኑን ስለምገነዘብ ነው" ይላል በርናንድ፡፡

ነገር ግን ብስክሌቶች ብቻ አይደለም።

የቻይና ግዙፍ ማሽኖች

የወባ መድሃኒት ጥቅም ላይ ሊውል ነው

የእርሱ የፈጠራ ውጤት የሆነውና በንፋስ ኃይል የሚሰራው የልብስ ማጠቢያ ማሽን የቤተሰቡን አልባሳት ንፋስ በሚበረታበት ጊዜ በአንዴ ስለሚያጥብላቸው ልፋትና ጊዜያቸውን ቆጥቦላቸዋል።

የበርናንድ ፈጠራ አሁን ከራሱ ቤትና ጓሮ አልፎ ለማህበረሰቡ ተዳርሷል። ትዌንዴ የተባለውን እና እርሱ የጀመረውን የፈጠራ ሰርቶ ማሳያ 800 እና ከዚያ በላይ የሚሆኑ የአካባቢው የፈጠራ ሰዎች ተጠቅመውበታል።

በታንዛንያ "የገጠር የፈጠራ ውጤት አባት" እየተባለም ይጠራል።

"ለሰዎች ማሳየት የፈለገነው ሁሉም ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ራሳቸው ሊጠግኑት የሚችሉት እና የሚፈልጉትን መለዋወጫ ሊያገኙለት የሚችል የራሳቸውን ቴክኖሎጂ ለመፍጠር ክህሎቱ እንዳላቸው ነው" ይላል ብርናንድ።

"የሀገሬው ሰዎች ሁሌም ገቢያቸው ትንሽ ሲሆን በየሱቆቹ የሚሸጡት መሳሪያዎች ደግሞ ውድ በመሆናቸው ለእነዚህ ሰዎች አይሆኑም። ለዚያም ነው በአካባቢዬ በማገኛቸው ነገሮች ላይ ያተኮርኩት።"

አጭር የምስል መግለጫ ፍራንክ ሞሌል ማዳበሪያ ከሚያሰራጭበት ጋሪ ጋር

ማዳበሪያን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል ፈጠራ

ፈራንክ ሞሌል ከአካባቢው የፈጠራ ሰዎች አንዱ ሲሆን ማዳበሪያ እና ከከብቶች የሚወጣን ፍግ በእጅ ለመበተን የሚወስደውን ጊዜ ለማሳጠር የሚረዳውን የተሻሻለ ጋሪ 'ፈርት ካርት'ን ፈጥሯል።

የፍራንክ የፈጠራ ሃሳብ ተሻሽሎ የተሰራውን ጋሪ ለመግዛት በቂ መሬት እና ገቢ ለሌላቸው አርሶ አደሮች ማከራየትን ይጨምራል።

ትዌንዴ በሰርቶ ማሳያቸው ውስጥ ያሉ ሁሉ ጥሩ የንግድ ልምዶችን መቅሰማቸውን እና የንግድ እቅድ ማዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል።

ከደንበኛቹ መካከል አንዱ ይህን መሳሪያ መጠቀሙ ለልጆቹ የትምህርት ቤት የመክፈል አቅምን እንደፈጠረለት ይናገራል።

ሬሳን ከሞት አስነሳለሁ ያለው 'ነብይ' የሟች ቤተሰብን እንዴት አሳመነ?

"ተሻሽሎ የተሰራው ጋሪ 'ፈርት ካርት' በእርሻ ተግባራት የሚጠፋውን በቢሊዮን የሚቆጠር ሰዓት ቀንሶታል" ይላል ፍራንክ። "አፍሪካ በተለይ ደግሞ በታንዛኒያ አርሶ አደሮች ምርታማነታቸው እንዲጨምር እና አነስተኛ እርሻ ያላቸው ገበሬዎች ገቢያቸው እንዲያድግ የሚረዳቸውን ይህን ድንቅ ቴክኖሎጂ ትፈልገዋለች።"

አጭር የምስል መግለጫ የጄሲ ኦሊጃንጌ የአቮካዶ ዘይት መጭመቂያ በትዌንዴ ሰርቶ ማሳያ ለስድስተኛ ጊዜ እየተሰራ ነው

አረንጓዴ ወርቅ

የጄሲ ኦሊጃንጌ አቦካዶ መጭመቂያ የማበረሰቡን ህይወት እየቀየረው ነው።

"ትዌንዴ እራሱ ማህበራዊ የፈጠራ ግኝት ነው" ይላል ጄሲ። "በአንድ ክፍል ውስጥ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የሚሰሩ ሰዎች አሉ። እናም ችግር ቢገጥምህ ከመካከላቸው አንዱን በመጠየቅ መፍትሄውን ታገኛለህ።"

አርሶ አደሮቹ በገበያው ላይ የተሻለ ዋጋ ስለማያገኙ ዘይቱ ከመጨመቁ በፊት አቦካዶዎች በረገፉበት ቦታ ይበሰብሱ ነበር። አሁን በአካባቢው ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ሴቶች አቦካዶውን የሚሸጡትን ዘይት ለማውጣት ይጠቀሙበታል፡፡

ጄሲ እንደሚለው ትዌንዴ ውስጥ መሳተፉ ሰርቶ ማሳያውን እንደ እናት ድርጅት በመጠቀም የገንዘብ ድጋፍ ለመጠየቅም አስችሎታል። የገንዘብ ድጋፍ እና የመንቀሳቀሻ ገንዘብ ማግኘት እንደ ጄሲ ላሉ የአካባቢው የፈጠራ ሰዎች ሁለቱ ተግዳሮቶች ናቸው።

በአብዛኛዎቹ በርናርድን የመሳሰሉ የሚያግዟቸው አማካሪዎች አሏቸው።

"ችግር ካጋጠመህ ጭንቅላትህ ሊዞር አይገባም ለበርናርድ ትነግረዋለህ። ለሁለት ደቂቃዎች ያህል አስቦ በዚህ መንገድ ሥራው ይልሃል። እኛም ብዙ የምናማክረው አለን" ይላል ጄሲ።

አጭር የምስል መግለጫ የማግሬት ኦማሬ የሳሙና መቁረጫ ግኝት የብዙዎችን ሰዎች እጣ ፈንታ ቀይሮታል

የሳሙና እገዛ

የማገሬት ህይወት ትዌንዴ ሰርቶ ማሳያ ውስጥ በፈጠረችው የሳሙና መቁረጫ ማሽን ምክንያት ተቀይሯል።

የእራሷን የሳሙና ንግድ እንድትጀመር ከማስቻሉም ባሻገር ማሽኗን በከተማው ውስጥ ላሉ ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች በማጋራት ገቢ እንዲያገኙ ታደርጋለች።

"ልጆቼ ከዚህ በኋላ በክፍያ እጦት ምክንያት ከትምህርት ቤት ስለማይባረሩ ደስተኛ ነኝ" ትላለች።

ቀላል የፈጠራ ውጤት የብዙዎችን ህይወት እንዴት ሊቀየር እንደሚችል አስረጂ ነው።

አጭር የምስል መግለጫ በርናርድ ኪዊያ በአካባቢው የሚገኙ ትምህርትቤቶችን በማዳረስ አዲስ የፈጠራ ትውልድ ለማፍራት ተስፋ ያደርጋል

ምን ትምህርተቀሰሙ

"የወደፊት ህልሜ ታንዛንያዊያን በዘወትር እንቅስቃሴዎቻችን የምንጠቀምባቸው የራሳችን ምርቶች ኖረውን ማየት ነው" ይላል በርናርድ።

ይህ እንዲሆንም በአካባቢው ከሚገኙ ትምህርትቤቶች ልጆችን ወደ ትዌንዴ በመጋበዝ ለምርጥ የፈጠራ ውጤቶች እንዲበረታቱ ያደርጋል። ሰርቶ ማሳያው ልጆቹ መስሪያ እቃዎችን ይዘውም ሆነ ለስልጠና ወደ ገጠራማ መንደሮች የሚሄዱበት አነስተኛ መኪና አለው።

"ትዌንዴ ውስጥ ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ የፈጠራ ሥራዎች እንሰራለን። በመሆኑም ማህበረሰቡን የሚፈታተኑ ተግዳሮቶችን በማየት እሱኑ ለመወጣት ጥረት በማድረግ ችግሩን እንፈታለን" ይላል ተማሪው ላይትነስ ሲምኦን ኪኒሳ።

ብየዳን ለመሳሰሉ ትምህርቶች እንደሚያደርገው የተግባር ልምምድ ሁሉ በትዌንዴ ትምህርት ቤት አነስተኛ ንግድን እንዴት ማስኬድ እንደሚቻል እና የበጀት ዝግጅትን የተመለከቱ ሰርቶ ማሳያዎችም አሉ።

"በርናርድ ኪዊያ በጣም የተለየ ሰው ነው" ይላል ከታንዛኒያዊን የፈጠራ ሰዎች እና ቴክኖሎጂ አመንጪዎች ማህበር የመጣው ኢሳ ካንጉኒ።

እሱ እንደሚለው "በአፍሪካ ወይም በታንዛኒያ የፈጠራ ሰው መሆን በጣም ከባድ ነው። ምክንያቱም የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ሰዎች የሚተገብሩበት ሀብት የላቸውም።"

በርናንድ ኪዊያ በትዌንዴ ሀብትን በመጋራት ማህበረሰቡ ለራሱም ሆነ ከእነሱ ውጪ ላለው ዓለም መፍትሄ የሚሆን አዳዲስ የፈጠራ ሀሳብ ማመንጨቱን እንዲቀጥል ለማነቃቃት ተስፋ ያደርጋል።

"አንዳንድ ጊዜ ላይሳካልህ ይችላል፤ ስለዚህ እንደገና ትሰራዋለህ ይላል በርናርድ። አንዳንድ ጊዜ በድጋሚም ላይሳካልህ ይችላል፤ አሁንም እንደገና ትሰራዋለህ። ነገር ግን በመጨረሻ ጥሩ ነገር ላይ ትደርሳለህ።"

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ