በኬንያ በርካታ ትምህርት ቤቶች በተማሪዎች ተቃጠሉ

በእሳት የወደመ ትምህርት ቤት

ባለፉት ሰባት ወራት ኬንያ ውስጥ የሚገኙ ከ50 የሚበልጡ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የእሳት አደጋ ሲገጥማቸው ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ደግሞ ባለፉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ነው ያጋጠሙት።

ትናንት ምሽት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ውስጥ የሚገኙ ሁለት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሚገኙ የተማሪዎች ማደሪያ ክፍሎች ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ሳቢያ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘጉ ተደርጓል።

እሁድ ዕለት በአንደኛው ትምህርት ቤት ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ 31 ተማሪዎች በጭስ በመታፈንና በሌሎች ጉዳቶች ሳቢያ ሆስፒታል ገብተዋል።

ጉግል ኢንተርኔትን በላስቲክ ከረጢት ይዞ ኬንያ ገብቷል

ኬንያ ሺሻን አገደች

ኬንያ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው

ይህ አደጋ በዚህ ዓመት ብቻ ካጋጠሙ በትምህርት ቤቶች ላይ እሳት የማስነሳት 50 ተከታታይ የቃጠሎ ጥቃቶች መካከል አንዱ ነው። በዚህም ምክንያት ቢያንስ 40 የሚሆኑ የተለያዩ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እሳት በማስነሳት ክስ ቀርቦባቸዋል።

ተማሪዎቹ ትምህርት ቤታቸው ላይ እሳት እንዲያስነሱ ያደረጋቸው ምክንያት ምን እንደሆነ አከራካሪ ቢሆንም ለፈተና ያለቸው ፍርሃት፣ በኩረጃ ላይ ሚካሄድ ቁጥጥር፣ ጥብቅ የትምህርት ቤት ውስጥ ደንቦች ወይም በትምህርት ቤቶች አስተዳዳሪዎች ላይ የሚደረጉ ለውጦች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይታመናል።

በእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ወላጆች ባጋጠሙ ውድመቶች ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠር ዶላሮች ቅጣት ይጠብቃቸዋል። በቃጠሎ የተጎዱትን ትምህርት ቤቶች ለመጠገን እያንዳንዱ ተማሪ 10 እና 50 ዶላር እንዲከፍሉ ተደርጓል።

በአንድንድ ትምህርት ቤቶች ትምህርት ቢጀመርም ወደ ትምህርት ቤት የተመለሱ ተማሪዎች እንደሚሉት ባልተሟሉ የመማሪያ፣ የመመገቢያና የማደሪ ክፍሎች ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ቀደም ባሉ ጊዜያት ተመሳሳይ ንብረት የማውደም ድርጊቶች ያጋጠሙ ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በፊት 100 የሚደርሱ ትምህርት ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ከደረሰባቸው በኋላ ድርጊቱ እንዳይደገም ለመከላከል ምርመራ ተደርጎ ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ