ሰሜን ኮሪያ የኒውክለር ማስወንጨፊያ ስፍራዎቿን ማፈራረስ ጀመረች

ሰሜን ኮሪያ ሶሄ ጣቢያን ሮኬት ለማስወንጨፍ ትጠቀምበት ነበር Image copyright Reuters

ሰሜን ኮሪያ ሚሳዔል ታስወነጭፍ ከነበረችባቸው ስፍራዎች መካከል በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኘውንና ዋነኘውን ስፍራ ማፈራረስ ጀመረች።

ከሳተላይት የተነሱ ምስሎች በአሜሪካው የቁጥጥር ቡድን 38 ከታዩ በኋላ ፒዮንግያንግ ከአሜሪካ ጋር በሰኔ ወር የገባችውን ቃል እያከበረች እንደሆነ ተገምቷል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የኒውክለር ሞተሩ አካል ያለበትን ስፍራ ከጥቅም ውጭ እንደሚያደረጉ ቃል መግባታቸውን ገልፀው የነበረ ቢሆንም የትኛውን ግን እነደነበር አልተናገሩም።

"አሜሪካ ምኞቷ ሞላላት"፡ ዶናልድ ትራምፕ

ሰሜን ኮሪያን በምን መመከት ይቻላል?

ፒዮንግ ያንግ ሶሄን የሳተላይት ማስወንጨፊያ ስፍራ አድርጋ ስትጠቀምበት ቆይታለች።

የአሜሪካ ባለስልጣናት ግን ስፍራው የባለስቲክ ሚሳኤሎችን መፈተሻ ሆኖ ያገለግላል ሲሉ ይጠረጥሩ ነበር።

በፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ኪም ጆንግ ኡን በሲንጋፖር "ሙሉ በሙሉ ከኒውክለር የፀዳ የኮሪያ ባህረ ሰላጤ" እንዲኖር መፈራረማቸው ይታወሳል።

ስምምነቱ ግን ፒዮንግ ያንግ እንዴት እና መቼ የኒውክለር መሳሪያዎቿን ታስወግዳለች የሚለውን ዝርዝር ጉዳዮች ይጎድሉታል በሚል ትችት ይቀርብበት ነበር።

ሰሜን ኮሪያ ትልቁን የሚሳኤል ሙከራዋን አደረገች

ኪም ጆንግ ኡን ፍላጎታቸው ምን ይሆን?

የሶሄ የኒውክለር ማስወንጨፊያ ስፍራ ማፈራረስ መረጃ ይፋ የሆነው ሰሜን ኮሪያ ሰኔ 12 ለፈረመችው ሰነድ ተገዥ መሆንዋ ጥያቄ እየተነሳ ባለበት ወቅት ነው።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
ሰሜን ኮሪያ ለምን ኑክሊዬርን መረጠች?

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ሰኞ ሰሜን ኮሪያ ላለፉት ዘጠኝ ወራት አንድም ሚሳኤል አለማስወንጨፏን ወይም የኒውክለር ሙከራ አለማድረጓን በመጥቀስ ባላቸው ግንኙነት "ደስተኛ " መሆናቸውን ተናግረው ነበር።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ