ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካውያን ወታደሮችን አጽም መለሰች

የአሜሪካውያን ወታደሮች ቅሪተ አካል ለአሜሪካ ተመልሷል
አጭር የምስል መግለጫ የአሜሪካውያን ወታደሮች ቅሪተ አካል ለአሜሪካ ተመልሷል

የኮርያ ጦርነት በተካሄደበት ወቅት ህይወታቸው ያለፈ አሜሪካውያን ወታደሮች ቅሪተ አካል ለአሜሪካውያን ተመልሷል። ይህ የሆነው የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላን አጽሞቹን ይዞ ሰሜን ኮርያ ወደሚገኘው የአሜሪካ ማዕከል ተልኮ ነው።

አጽማቸው የተመለሰው ወታደሮች ከሰሜን ኮርያው ማዕከል ወደ አሜሪካ ይወሰዳሉ። የተመለሰው የ55 ሰዎች አጽም ሲሆን ሁሉም አሜሪካዊ ስለመሆናቸው ምርመራ ይደረጋል።

አጽም የመመለስ ሂደቱ በሁለቱ ሀገሮች መሀከል ያለውን ግንኙነት ለማለሳለስ ያለመ የዲፕሎማሲ እርምጃ ነው ተብሏል።

በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና በሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ-ኡን መሀከል የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የወታደሮቹ አጽም ተመልሷል። ሁለቱ ሀገሮች የጦርነቱ ማብቃት ምክንያት የሆነ ስምምነት የተፈራረሙበት 65ኛ ዓመት የሚዘከርበትን ወቅትም ያስታከከ ውሳኔ ነው።

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ

የመደመር ጉዞ ወደ አሜሪካ

የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን ከክፍፍል ወደ ውህደት

በጦርነቱ ወቅት ለደቡብ ኮርያ ወግነው 326,000 አሜሪካውያን መዋጋታቸው ይታወሳል። በጦርነቱ ከተዋጉ አሜሪካውያን የገቡበት ሳይታወቅ ቆይቷል። ወደ 5,300 የሚሆኑት ደቡብ ኮርያ ውስጥ ጠፍተዋል።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ወደ 5,300 የሚሆኑት ደቡብ ኮርያ ውስጥ ጠፍተዋል።

የደረሱበት ካልታወቀው ወታደሮች መሀከል ከፊሉ በወታደራዊ እስር ቤት እንደሚገኙ ይገመታል። ጦርነቱ በተካሄደበት ዋነኛ አካባቢ ላይ የ1,600 ሰዎች ቅሪተ አካል ይገኛል።

በወልዲያ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ሁለት ሰዎች ሞቱ

ሰሜን ኮርያ የመለሰቻቸውን የወታደሮች ቅሪት የክብር አቀባበል እንደሚደረግላቸው ከዋይት ሀውስ የተገኘ መረጃ ያመለክታል

የአሜሪካ መንግሥት የሰሜን ኮርያን ውሳኔ የመልካም ግንኙነት ተምሳሌት አድርጎ ወስዶታል።

የገቡበት ያልታወቀው 5,300 ወታደሮችን ለማፈላለግ ጅማሮ እንደሚሆንም ተመልክቷል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ