ምሩቁ ሙዝ ሻጭ እና ሌሎች ከአፍሪካ የተገኙ ድንቅ ፎቶግራፎች

ከተለያዩ የአፍሪ ክፍሎች የተገኙ ፎቶዎችን የምንቃኝበት አምድ። ከቱኒዚያ እንጀምር

ዕለተ ማክሰኞ፤ ከቱኒዚያ ዋና ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ወታ ብላ በምትገኘው የሞርናጉዋ ከተማ አንዲት ባልቴት ውሃ የጫነች አህያን ወደኋላ ስትጋልብ ካሜራ እይታ ውስጥ ገብታለች። Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ዕለተ ማክሰኞ፤ ከቱኒዚያ ዋና ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ወጣ ብላ በምትገኘው የሞርናጉዋ ከተማ አንዲት ባልቴት ውሃ የጫነች አህያን ወደኋላ ስትጋልብ ካሜራ እይታ ውስጥ ገብታለች።

ወደ ጋቦን እናቅና

የማሊው ፕሬዝደንት ደጋፊዎች ጋቦን ውስጥ የምረጡኝ ድጋፍ እያደረጉ ላሉት ኢብራሂም ቦባካር ፀሎት ሲያደርጉ ነበር። ፕሬዝደንቱ ጋቦን ለሚገኙ ደጋፊዎቻቸው የምረጡኝ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው። Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የማሊው ፕሬዝደንት ደጋፊዎች ጋቦን ውስጥ የምረጡኝ ድጋፍ እያደረጉ ላሉት ኢብራሂም ቦባካር ፀሎት ሲያደርጉ ነበር። ፕሬዝደንቱ ጋቦን ለሚገኙ ደጋፊዎቻቸው የምረጡኝ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው።

ደቡብ ሱዳን ለመኪና መግዣ 16 ሚሊየን ዶላር አወጣች

በኬንያ በርካታ ትምህርት ቤቶች በተማሪዎች ተቃጠሉ

ወደሃራሬ ስንዘልቅ

አርብ ዕለት ነው፤ የሶሲዮሎጂ ትምህርት ምሩቁ አቤል ካፖዶጎ በዚምባብዌ ከተማ ሃራሬ ሮበርት ሙጋቤ መንገድ ላይ ገዋኑን እንደለበሰ ሙዝ እየመዘነ ሲሸጥ የካሜራ ዓይን የገዛው። አቤል ከነገዋኑ ሙዝ ለመሸጥ የወሰነው በሃገሪቱ የሚስተዋለውን ሥራ አጥነት ለመቃወም በማሰብ ነው። Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ አርብ ዕለት ነው፤ የሶሲዮሎጂ ትምህርት ምሩቁ አቤል ካፖዶጎ በዚምባብዌ ዋና ከተማ ሃራሬ ሮበርት ሙጋቤ መንገድ ላይ ገዋኑን እንደለበሰ ሙዝ ሲሸጥ፤ አቤል ከነገዋኑ ሙዝ ለመሸጥ የወሰነው በሃገሪቱ የሚስተዋለውን ሥራ አጥነት ለመቃወም በማሰብ ነው።

የሐርጌሳ ተስፋ

ዕለተ ቅዳሜ፤ የ16 ዓመቱ ሶማሊያዊ ፀሐፊ አብዲሻኩር ሞሐመድ ካሳተመው መፅሐፍ ጋር ፎቶ የተነሳው ራሷን ነፃ ብላ ባወጀችው ሃገረ ሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሐርጌሳ ነው። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ዕለተ ቅዳሜ፤ የ16 ዓመቱ ሶማሊያዊ ፀሐፊ አብዲሻኩር ሞሐመድ ካሳተመው መፅሐፍ ጋር ፎቶ የተነሳው ራሷን ነፃ ብላ ባወጀችው ሃገረ ሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሐርጌሳ ነው።

ምፅዋ

ባለፈው እሁድ ነው፤ ከአስመራ ወጣ ብላ በምትገኘው ምፅዋ ተብላ በምትታወቀው የወደብ ከተማ አንዲት ሕፃን ልጅ ቀይ ባሕር ሃይቅ ዳርቻ ስትጫወት ታይታለች። Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ባለፈው እሁድ ነው፤ ከአሥመራ ወጣ ብላ በምትገኘው ምፅዋ ተብላ በምትታወቀው የወደብ ከተማ አንዲት ሕፃን ልጅ ቀይ ባሕር ዳርቻ ስትጫወት ታይታለች።

ከኤርትራ ሳንወጣ

አርጀት ብትልም በደንቡ የተያዘች ፊያት መኪና በአስመራ ጎዳና ስትንሸራሸር የካሜራ ዓይን ውስጥ የገባችው ባሳለፍነው ሳምንት ነው። Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ አርጀት ብትልም በደንቡ የተያዘች ፊያት መኪና በአሥመራ ጎዳና ስትንሸራሸር የካሜራ ዓይን ውስጥ የገባችው ባሳለፍነው ሳምንት ነው።

ደቡብ አፍሪ

የደቡብ አፍሪቃ ነፃነት አርማ ተደርገው የሚቆጠሩት ኔልሰን ማንዴላ ከእሥር እንደተለቀቁ መግለጫ በሰጡበት ሥፍራ የቆመላቸው የማስታወሻ ሐውልት ጎብኚ አያጣም። ማንዴላ በሕይወት ቢኖሩ ሐምሌ 11/2010 100 ዓመት ይሞላቸው ነበር። Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ የደቡብ አፍሪካ ነፃነት አርማ ተደርገው የሚቆጠሩት ኔልሰን ማንዴላ ከእሥር እንደተለቀቁ መግለጫ በሰጡበት ሥፍራ የቆመላቸው የማስታወሻ ሐውልት ጎብኚ አያጣም። ማንዴላ በሕይወት ቢኖሩ ሐምሌ 11/2010 100 ዓመት ይሞላቸው ነበር።

ፎቶዎች ከኤኤፍፒ፣ ኢፒኤ፣ ጌቲ ኢሜጅስ እና ሮይተርስ የተወሰዱ ናቸው።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ