በሞባይሎ ኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል? በሞባይሎ ላይ እነዚህን ማስተካከያዎች ያድርጉ

Image copyright NurPhoto

ኢትዮ ቴሌኮም ወደ 60 ሚሊዮን የሚገመቱ ደንበኞች እንዳሉት ይነገርለታል። ከእነዚህ መካከል ደግሞ 17 ሚሊዮን ያህሉ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የኢንተርኔት አገልግሎትን ይጠቀማሉ።

ኢትዮ ቴሌኮም ዝቀተኛ በማይባል ዋጋ ኢንተርኔትን ለተጠቃሚዎች ከሚያደርሱ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች መካከል አንዱ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ።

ምናልባትም እርሶም ''አሁን የገዛሁት ኢንተርኔት ከምኔው አለቀ?'' ''ካርድ ዛሬ አይደል እንዴ የሞላሁት ወዴት ሄደ?'' ብለው እራሶን ጠይቀው ሊሆን ይችላል።

በአንድሮይድ አና በአይኦኤስ ስልኮቻችን ላይ አንዳንድ ማስተካካያዎች በማድረግ የኢንተርኔትን ወጪ መቀነስ የሚቻልበትን መንገድ እንጠቁማችሁ።

በቅደሚያ አንድሮይድ አና አይኦኤስ ምንድናቸው?

አንድሮይድ በጉግል የተሰራ የተለያዩ የሞባይል አይነቶች የሚጠቀሙበት የመተግበሪያ ስርዓት ነው። ለምሳሌ ሳምሰንግ፣ ሁዋዌ፣ ኤል ጂ (LG) እና ቴክኖን የመሳሰሉ ሞባይሎች አንድሮይድ የተባለውን የመተግበሪያ ስርዓትን ይጠቀማሉ።

አይኦኤስ (iOS) በአፕል የተሰራ ሲሆን አይፎን፣ አይፓድ እና አይፓድ ተች የሚጠቀሙበት የመተግበሪያ ስርዓት ነው።

እንደ ፌስቡክ እና ዋትሰአፕ የመሳሰሉ በዕለት ተለት በምንጠቀምባቸው መተግባሪያዎች ላይ ቀላል ማስተካከያዎችን በማድረግ እንዴት የኢንተርኔት ወጪያችንን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ እንደምንችል እንጠቁማችሁ።

ፌስቡክ (Facebook)

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፌስቡክ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በራሳቸው ጊዜ እንዲጫወቱ ፍቅዷል። ይህም ብዙ ዳታን ይጠቀማል። ተንቀሳቃሽ ምስሎች በራሳቸው ጊዜ እንዳይጫወቱ ለማድረግ (Video Autoplay off) ለማድረግ፡-

በአንድሮይድ ስልኮች ላይ ይህን ይከተሉ፡ ሴቲንግ ኤንድ ፕራይቬሲ (Setting and Privacy) >ዳታ ሴቨር (Data Saver) የሚለውን On ያድርጉ።

በአይኦኤስ (አይፎን) ላይ ይህን ይከተሉ፡ ሴቲንግ (Setting) >ሚዲያ ኤንድ ኮንታክት (Media and Contact) >ቪዲዮ ኤንድ ፎቶስ (Video and Photos) >አውቶ ፕለይ (Auto-play) >ኦን ወይፋይ ኮኔክሽን ኦንልይ (On Wi-Fi connections only) የሚለውን On ያድርጉ።

ከዚህ በተጨማሪም በአንድሮይድ ስልኮች ላይ አነስተኛ ዳታ የሚጠቀመውን ፌስቡክ ላይት (Facebook Lite) የተባለውን የፌስቡክ ስሪት መተግበሪያን ከጉግል ፕለይ ላይ በማውረድ መጠቀም ይቻላል።

ሌላኛው አማራጭ ደግሞ ፌስቡክ የሚለውን መተግበሪያ ከመጠቀም ይልቅ እንደ ኦፔራ ሚኒ (Opera Mini) ያሉ የኢንተርኔት መቅዘፊያ መተግበሪያዎችን (Internet Browser Apps) በመጠቀም የዳታ ወጪን መቀነስ ይቻላል።

ያስታውሱ ፌስቡክን በፌስቡክ ላይት ወይም በመተግበሪያዎች ስጠቀሙ የፌስቡክ ማራኪነት እና አማራጮች ሊቀንሱ ይችላሉ።

ዋትስአፕ (WhatsApp)

ስንት የዋስትአ ግሩፕ (ቡድን) ውስጥ አሉ? በዋትስአፕ የሚላክሎት ፎቶ እና ቪዲዮ በፎቶ ጋለሪ ውስጥ አለ ማለት ብዙ የሞባይል ዳታ እየተጠቀሙ ነው። ዋትስአፕ የሚጠቀመውን የዳታ መጠን ለመቀነስ ይህን ይከተሉ።

የዋትስአፕን ሴቲንግ (Setting) ይክፈቱ >ዳታ ኤንደ ስቶሬጅ ዩሴጅ (Data and Storage Usage) >ከዚያም ሰሌክት ሚዲያ አውቶ ዳዎንሎድ ኦፕሽንስ (Select Media Auto Download Options) የሚለውን በመምረጥ >ዌን ዩዚንግ ሞባይል ዳታ (When Using Mobile Data) የሚለውን በመጫን ''ኖ ሚዲያ (No Media)'' በሚለው ይቀይሩት።

በይበልጥ ዋትስአፕ የሚጠቀመውን ዳታ ወጪ ለመቀነስ ኮል ሴቲንግ (Call Setting) ከሚለው በታች ያለውን ሎው ዳታ ዩዜጅ (Low Data Usage) መምረጥ ይቻላል።

ዩቱዩብ (YouTube)

በዩቱዩብ ቪዲዮችን መመልከት ብዙ ዳታ ይወስዳል። በሞባይል ዳታ ቪዲዮን መመልከት ካስፈለጎው ግን የሴቲንግ ምልክቷን በመጫን 240p ወይም 144p ላይ በማድረግ በአነስተኛ ጥራት በመመልከት እስከ 60 በመቶ ሊያወጡ የሚችሉትን የHD (720p) የዳታ መጠን መቀነስ ይችላሉ።

ሌላው አማራጭ የቪዲዮ ባለመብት ፍቃድ ካለ የወደድነውን ቪዲዮ ከዩቱብ ላይ የዋይፋይ አግልግሎት ያለበት ቦታ ላይ በማውረድ ለ30 ቀናት የለ ኢንተርኔት ደጋግምን መመልከት እንችላለን።

ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት?

ኢትዮ-ቴሌኮም፡ አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ?

የሰሞኑ የኢትዮ-ቴሌኮም ምዝገባ ነፃነትን ይገድብ ይሆን?

መተግበሪያዎችን ማሻሻል (Updating Apps)

በስልኮቻችን ላይ ተጭነው የሚገኙ መተግበሪያዎች በፈጣሪዎቻቸው በተለያየ ጊዜ በአዳዲስ ቅጂዎች ይሻሻላሉ። መተግበሪያዎቹን ለማሻሻል የሞባይል ዳታን መጠቀም ብዙ የኢንተርኔት ወጪን ያስከትላል። ስለዚህም የዋይፋይ (Wi-Fi) አገልግሎት ባለበት ቦታ ብቻ ማሻሻል ይመከራል።

መተግበሪያዎችን ለማሻሻል ዋይፋይን ብቻ ለመጠቀም የሚከተሉትን ቅድመ ተከተሎች ይከተሉ።

አንድሮይድ ስልኮች ላይ፡ ጉግል ፕለይ ስቶር (Google Play Store) >ሴቲን (Setting) >አውቶ አፕዴት አፕስ (Auto-update apps) >አውቶ አፕዴት አፕስ ኦቨር ዋይፋይ ኦንልይ (Auto-update apps over Wi-Fi only) የሚለውን On ያድርጉት።

ለአይፎን ስልኮች ላይ፡ ሴቲንግ (Setting) >አይቲዩንስ & አፕ ስቶር (iTunes & App Stores) >ዩዝ ሞባይል ዳታ (Use Mobile Data) የሚለውን Off ያድርጉት።

አጠቃላይ ስልካችን ሊጠቀም የሚችለውን ዳታ መቀነስ

የእርሶ ስልክ አንድሮይድ መተግበሪያ ስርዓትን የሚጠቀም ከሆነ በስልኮ ላይ የሚከተሉትን ማስተካከያዎች በማድረግ የኢንተርኔት አጠቃቀሞው ላይ ገደብ ሊያደርጉ ይችላሉ።

Setting > Network & Internet > Data Usage > Data Saver >

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ