አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም በቤተሰቦቹና በሙያ አጋሮቹ ዓይን

አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም Image copyright BogasTube

"ለኔ ወንድሜ ጓደኛዬ ነው። አባቴም ነው።"ግርማ ተክለማርያም

ግርማ ተክለማርያም የፍቃዱ ወንድም ነው። ፍቃዱ ከወንድምነት ባሻገር ጓደኛውም እንደሆነ ይናገራል. . .

"ለኔ ወንድሜ፣ ጓደኛዬ ነው። ከዚያ በላይ አባቴም ነው።" ይላል።

ፍቃዱ ጥሩ ጤንነት ላይ ነበር ፤ እየተሻለውም ነበር። የፍልሰታን ጾም ልጨርስና ወደ አዲስ አበባ እመጣለሁ ብሎ አስቦ በነበረበት ሁኔታ ነው በሞት የተለየው።

ዶክተር ብርሃኑ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ምን ተወያዩ?

40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ

ያልተነገረለት የኮንሶ ጥያቄ

በገዳም ህግ ገዳም ውስጥ ያረፈ ሰው አስከሬን ከገዳም አይወጣም። ነገር ግን ገዳሙ ትልቅ ትብብር አድርጎልናል። ፍቃዱ የህዝብ ልጅ ነው። ስለዚህ ህዝብ በይፋ እንዲቀብረው አስከሬኑን ሰጥተውናል።

ጸበል ቦታ ሳለ አንድ ወር ከሰባት ቀን አብረው ቆይቻለሁ። ባለቤቱም ነበረች። በየግዜው በስልክ አገኘው ነበር።

ከህክምና በፊት የተወሰነ ጊዜ ስላለው ወደ ኩላሊት እጥበት ከመግባቱ በፊት ሀይማኖታዊ ህክምና ላድርግ አለና ተስማማን። ሀይማኖቱ ላይ ጠንካራ አቋም ነበረው።

ሀይማኖታዊ ህክምናውን እያደረገ ጤናው ተመልሶ ነበር። ከዚያ ሲመለስ ከኢትዮጵያ ውጪ ህክምናውን ሊቀጥል ወስኖ ነበር።

''የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ዕቅድ የተነደፈው በኢትዮጵያ ሃብት ላይ ነበር'' አምባሳደር አውዓሎም ወልዱ

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሙሉ የህክምና ወጪውን ችዬ በነጻ ለማሳከም ፍቃደኛ ነኝ አለ። በማመስገን ተቀበልን። ጳውሎስ ሆስፒታል ንቅለ ተከላ የሚደረግላቸው ሰዎች ኩላሊት ከቅርብ ዘመዶቻቸው የተሰጣቸው ብቻ ናቸው።

እኔና ሌሎችም ቤተሰቦች በጤና እክል ምክንያት ኩላሊት መስጠት አልቻልንም። ኩላሊት ፍለጋ ወደሚድያ የተወጣው ለዚህ ነው።

እግዚአብሔር ይመስገን ከውጪና ከሀገር ውስጥም ከ100 ሰው በላይ ኩላሊት ለመስጠት ፍቃደኛ ሆነ። ስለዚህ የሀገር ውስጥ ህክምና ቀርቶ ውጪ ለህክምና ለመሄድ ነበር።

ትላንት አይኑን ልመልከት ብዬ የአውሮፕላን ትኬት ቆርጬ ሄጄ ነበር። ግን ኮምቦልቻ ላይ ዝናብ ስለዘነበ አውሮፕላኑ ማረፍ አልቻለምና ወደ አዲስ አበባ ተመለሰን።

"ፍቄ የሀገር ቅርስ ነው። የሁሉም አባት ነው"

ዮርዳኖስ ለፍቃዱ እንደ ልጅ ቅርቡ ነው። ፍቃዱ የሱ ብቻ ሳይሆን የሀገር ቅርስ እንደሆነ እንዲህ ያወሳል. . .

ከትንሳኤ በአል በኃላ ወደ ጸበል ሄደ። ጳውሎስ ሆስፒታል ቀጠሮ ላይ ነበር። የቀጠሮው ግዜ እስከሚደርስ 'ቤቴ አልቀመጥም ጸበል ቦታ ገብቼ እግዚአብሄርን እማጸናለሁ' ብሎ ነበር።

ከበቂ በላይ ገንዘብ ተሰባስቧል። እሱም ደስተኛ ነበር። የሌላ ሰው ኩላሊት ወስጄ ባልተርፍስ የሚል ስጋት ግን ነበረው።

ትላንት ወደ 11 ሰዓት ነው ሞቱን የሰማነው። ፍቄ የሀገር ቅርስ ነው የሀገር ባለውለታ ነው።

ፍቄ ከምንም በላይ አባት ነው። የሁሉም ሰው አባት ነው።

"መጨረሻ የተናገረው በርቺ የሚል ቃል ነበር"

ፍቃዱ ህክምና እንደሚያስፈልገው ከታወቀ ጊዜ አንስቶ ኮሚቴ ተቋቁሞ ገንዘብ ሲያሰባስቡ፣ ኩላሊት የሚለግስ ሲፈልጉም ነበር።

በዚህ ሂደት ወቅት እንደ ፍቃዱ በኩላሊት ህመም ትሰቃይ የነበረቸው የሜላት አሰፋ ጉዳይ በማህበራዊ ድረ ገጾች ይዘዋወር ጀመር። ሜላት በኩላሊት ህመም ምክንያት ትምህርቷን ከአስረኛ ክፍል ለማቋረጥ ተደዳለች።

ፍቃዱ ስለ ሜላት ሲሰማ 'ወጣትን መታደግ ይሻላል' ብሎ ለህክምናው ከተሰባሰበለት ገንዘብ 200,000 ብር ለሜላት እንዲሰጥ አደረገ። ሜላት ስለ ፍቃዱ እንደምትናገረው. . .

ያኔ የፍቃዱ ጥሪ የመጣልኝ በጌታነህ ጸሀዬ በኩል ነበር። ገንዘቡን የሰጠኝ ምንም ባልጠበቅኩበት ወቅት ነበር። በሰዓቱ እጄ ላይ ብር አልነበረኝም።

ሲጠራኝ እንዲሁ ሊያናግረኝ የፈለገኝ ነበር የመሰለኝ። መልካም ነገር ነው ያደረገልኝ፤ አመሰግነዋለሁ።

በኛ ሀገር የኩላሊት እጥበት ወጪ ከባድ ነው። እሱ ግን ረዳኝ። ከሀገር ውስጥም ከውጪም ሰዎች ባሰባሰቡልኝ ገንዘብ እየታከምኩ ነው። አሁን በኮርያ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት እየተከታልኩ ነው።

ከረዳኝ በኃላ በስልክ አንገናኝ ነበር።

ለመጨረሻ ጊዜ የተነጋገርነውን አስታውሳለሁ። 'በርቺ' የሚል ቃል ነበር የተናገረው። 'እንድናለን' ይለኝ ነበር።

ድኖ እንገናኛለን ብዬ ነበር። ነገር ግን አልሆነም።

"በጣም ግሩም፣ ድንቅና ብርቅ አርቲስት ነበር"

ተስፋዬ አበበ (ፋዘር በሚል የቁልምጫ ስምም ይጠራሉ) በቴአትርና በሙዚቃ ዘርፍ በጽሁፍና በዝግጅትም ይታወቃሉ። እውቁ የተስፋዬ የስልጠና ማዕከል የበርካታ ተዋንያንና ጸሀፊ ተውኔቶች መነሻ ነው። ከነዚህ አንዱ ደግሞ ፍቃዱ ነው። ፋዘር ስለ ፍቃዱ ሲናገሩ. . .

በልጅነቱ የሰለጠነው እኔጋ ነበር። ያኔ ሱራፌል ጋሻው ከሚባል ጓደኛው ጋር የመጣው በ 1965 ዓ. ም. ነበር።

እኔጋ ከመምጣቱ በፊት በትምህርት ቤቱ ሙዚቃ ይጫወት ነበር። ከተዋናይነቱ ባሻገር መለስተኛ ድምጻዊም ነው።

እኔጋ ሲመጣ ልጅ ቢሆንም እንደልጅነቱ ሳይሆን ሁሉም ነገር ላይ ይሳተፍ ነበር። በዝማሬና በአጫጭር ድራማ ውስጥም ይገባል። ከእድሜው በላይ የሚያስብ ነበር።

ከዛ እሱ፣ ስዩም ተፈራና ሱራፌል ጋሻው ወደ ማዘጋጃ ቤት ሄዱ።

በሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን "ቴዎድሮስ" ቴአትር ላይ አጼ ቴዎድሮስን ሆኖ ትልቅ ስራ የሰራ ጀግና አርቲስት ነው። በጣም ግሩም፣ ድንቅና ብርቅ አርቲስት ነበር።

የፊልም ኢንዱስትሪው እየተስፋፋ ከመጣ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ትልልቅ ፊልሞች ሰርቷል።

በጣም በቅርቡ ደግሞ ከኔ ጋር "መለከት" በተባለ የቴሌቭዥን ድራማ ላይ ይሰራ ነበር።

40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ

ሰመጉ በኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የፀጥታ አካላት የመብት ጥሰቶችን መፈፀማቸውን በሪፖርቱ ገለፀ

ፍቃዱ በገሀዱ አለም ውስጥ ሰውን አክባሪና ታማኝ ነበር። ለጥበቡ የቆመ ለጥበቡ የቆመ ሰው ነበር። ነገር ግን በኩላሊት ህመም ምክንያት ትልቅ አደጋ ደረሰበት። ለህልፈት በቃ። እናም ሁላችንም ሀዘን ላይ ነው ያለነው።

ቴአትር ሲሰራ እውነታን ይዞ፣ እውነታን አስመስሎ ነው። ሆኖ ነው የሚጫወተው። በተለይ የማደንቀው ቴዎድሮስን ሆኖ ሲጫወት ነው።

አጼ ቴዎድሮስን ሆኖ ሲጫወት ሰውነቱ ሁሉ ይለወጣል። በቃ ፍጹም ቴዎድሮስን ነው የምናገኘው። ቴዎድሮስ በጣም መወደድና አድናቆት ያተረፈበት ስራ ነው። እኔም በጣም የማከብረው የማደንቀው በዛ ስራ ነው።

ፍቄ ሩህሩህ፣ ልበ ግልጽ ነው። የታመመ የሚጠይቅ፣ እከሌ ሞተ ሲባል ፈጥኖ የሚደርስም ነው።

"የእሱ አባት ኩራዝ የላቸውም፤ እሱ ግን ኢትዮጵያን ሊያበራ ነው የሞተው"

ፍቄ ቁጭ ብለው ሲያዋሩት 'የገበታ አርቲስት ነው'። የሚያመጣቸው ጨዋታዎች ያስፈነድቃሉ። አኩርፎ የሚቀመጥ ባህሪ ያለው አይደለም።

"መጨረሻ ወደ ገዳም ሊሄድ ሲል ደውሎ በጣም ትልቅ የአባት ምርቃት መረቀኝ"

የቴዎድሮስ ተሾመ "ጉዲፈቻ" ፊልም ከፍቃዱ ተጠቃሽ ስራዎች አንዱ ነው። ቴዎድሮስ ፍቃዱ የኩላሊት ህመም ከገጠመው በኃላ ለመታከሚያ የሚሆን ገንዘብ እያሰባሰበ የነበረው ኮሚቴ ውስጥ ይገኝበታል። ይህንንም ብሎናል. . .

በኮሚቴው ገንዘብ እንዲሰባሰብለት አድርገን ነበር። ከበቂ በላይ ገንዘብ ተሰብስቦለትም ነበር።

ከሁለት ወይም ሶስት ወር በፊት አብረን ወደ ህንድ ሄደን ነበር። ህመሙ የጸና እንደሆነና መታከም አንዳለበት ተረጋግጦ ነበር። 'ቶሎ ኩላሊት የሚለግስ ሰው ይዛችሁ ኑ' ብለውን ነበር።

አዲስ አባባ ከመጣም በኃላ እንደ መድከም ሲለው ሸበሌ የሚባል ክሊኒክ ወስደውት ነበር። እዛ ማደር እንዳለበትና ህክምና ማድረግ እንዳለበት ቢነግሩትም መጀመሪያ ጸበል ልጠመቅ ብሎ ወደ ወሎ ሄደ።

ገንዘብ ተዋጥቶለታል ኩላሊት የሚሰጥም ተገኝቶለታል። መጥቶ እንዲታከም እየነዘነዝን ነበር። የእግዚአብሄር ፈቃድ ሆነ ብለን እንለፈው እንጂ ህክምና እንዳያደርግ የሚያደርግ ነገር አልነበረም።

ይመጣል ተብሎም እየጠበቅን ነበር። ትላንት ማታ ዜና እረፍቱን ሰማን። በጣም ያማል። አባት ነው። አማካሪ ነው። ጓደኛ ነው።

መጨረሻ ላይ ወደ ገዳም ሊሄድ ሲል ደውሎ በጣም ትልቅ የአባት ምርቃት መረቀኝ። ላደረግከው ነገር እግዚአብሔር ይባርክህ አለኝ። ተመልሼ እመጣለሁ። የልፋትህን ውጤት አሳይሀለሁ ብሎኝ ነበር።

እርዳታ ሲያሰባስብ የነበረው ኮሚቴ ከቤተሰብ ጋር ለቀብሩ መደረግ ያለበትን ቅድመ ሁኔታ እያመቻቸ ነው። በ 1948ዓ. ም. የተወለደው ፍቃዱ ነገ 8 ሰዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ስርዓተ ቀብሩ ይፈጸማል። ከቀብሩ በፊት ከ5 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በብሄራዊ ቴአትር መታሰቢያ መርሀ ግብር ይኖራል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ