በጣና በለስ ግድያ ፈፅመዋል የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ

በጣና በለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ጥቃት ደርሶባቸው የሞቱት ስርዓተ ቀብር ተፈፅሟል።

በአማራ ክልል አዊ ዞን በጣና በለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክት አቅራቢያ በምትገኘው ፈንድቃ ከተማ ጥቃት ደርሶባቸው ከሞቱት አንዱ የ24 ዓመት ወጣት ሃብቶም ሃይለ ነው።

ቤተሰቦቹ አስከሬኑን ለመቀበል ከሐውዜን አላማጣ ድረስ ተጉዘው ነበር። አስከሬኑን ተቀብለው መቐለ በደረሱበት ወቅት ወንድሙን መብራህቶም ሃይለን ቢቢሲ አናግሮታል።

"እኔ ምን ማለት እችላለሁ እጅግ አሳዛኝ እና ዘግናኝ ነገር ነው። ሰው ሰርቼ እበላለሁ ብሎ ሄዶ ይሄ መፈፀሙ አሳዛኝ ነው። ይህ ሊቆም ነው የሚገባው።" ብሏል።

ሌላኛው የጥቃቱ ሰለባ ሮቤል ያዕቆብ ትውልዱና እድገቱ አስመራ ከተማ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ 6 ዓመታትን አስቆጥሯል።

የቀድሞዎቹ መሪዎች ኃይለማርያም ደሳለኝና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ተገናኙ

40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ

ዶክተር ብርሃኑ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ምን ተወያዩ?

ወይዘሮ ይርጋለም ኪሮስ የሮቤል ያዕቆብ ዘመድ ሲሆኑ የሟቹ እናት እና እህቶቹ አሁንም አስመራ እንደሆኑም ይናገራሉ።

ሮቤል የክሬን ሰራተኛ ሆኖ በጣና በለስ ፕሮጀክት ውስጥ ይሰራ እንደነበር ወይዘሮ ይርጋለም ይናገራሉ።

"ይህን ምን ማለት ይቻላል? አምላክ እራሱ ያብረደው። ይህን ዘር እየለዩ መግደል፤ መንግስት አንድ ነገር እንዲያደርግ ነው የምንጠብቀው። ልጆቻችን ነገ ምንድነው እጣፈንታቸው? አይታወቅም! ልጆቻችን ለስራ በየቦታው ተበትነው ነው ያሉት። ሀገራችን ነው ብለው ነው የሚሄዱት? ከሃገራቸው ውጪስ የትስ መሄድ ይችላሉ?" በማለት ለቢቢሲ ገልፀዋል።

የሮቤል ያዕቆብና ሶስተኛው ተጠቂ የሆኑት አቶ ሐድጉ ካሳ ፤ የቀብር ስነስርዓት በትውልድ ቀያቸው መቐለ ዛሬ ተፈፅሟል።

ሰመጉ በኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የፀጥታ አካላት የመብት ጥሰቶችን መፈፀማቸውን በሪፖርቱ ገለፀ

ለሞት የተዳረጉት ሆን ተብሎ የኤክትሪክ ሃይል ተቋርጦብናል በሚል በተቆጡ የከተማዋ ወጣቶች በደረሰ ጥቃት እንደሆነ ተዘግቧል።

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጥቃቱ ብሄርን መሰረት ያደረገ ነው ሲል ያወገዘ ሲሆን አጣሪ ቡድን ወደ ስፍራው እልካለሁ ብሏል።

በዜጎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ምርመራ መጀመሩን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ማስታወቃቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ