ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ

ፋጡማ አብዱልቃድር አዳን ኳስ ይዛ

የፎቶው ባለመብት, Fatuma Abdulkadir Adan

የምስሉ መግለጫ,

ፋጡማ አብዱልቃድር አዳን እግር ኳስን እንደ የሴት ልጅ ግርዛት በመሳሰሉ ነውር ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ዝምታውን ለመስበር እየተጠቀመችበት ነው፡፡

"ናይሮቢ ውስጥ የህግ ሥራ በመስራት ጥሩ ገቢ እያገኘሁ ዘናጭ መርሴዲስ ቤንዝ እያሽከረከርኩ መኖር ለእኔ ቀላል አማራጭ ነበር። እኔ ግን ወደ ትውልድ ስፍራዬ መመለስ ነበር የፈለግሁት።"

የፋጡማ አብዱልቃድር ህይወት ይህን ሊመስል ይችል ነበር። እሷ ግን እግር ኳስን መጫወት ለልጃገረዶች ነውር በሆነበት አካባቢ ይህንን ስፖርት መረጠች።

"አካላዊ ድብደባ ደርሶብኛል። መሬት ላይም ተጥያለሁ" ትላለች ያኔ የዛሬ አስር ዓመት በሰሜን ኬንያ ማርሳቤት ግዛት የሴቶችን ቡድን ማቋቋም ስትጀምር የነበረውን ትግል ስትገልጽ።

ፋጡማ የአፍሪካ ቀንድ የልማት ተቋም ወይም በ2003 በሚጠራበት ስሙ ሆዲ የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም መስርታለች።

እግር ኳስ ሰዎችን በአንድ እንዲያሰባስብ እና በባህላዊ አመለካከት ዙሪያ ለውጥ እንዲያመጣ ትፈል ነበር።

እግር ኳስን በ2005 በጎሳዎች መካከል ከተፈጠረውና 100 ሰዎችን ከገደለው እልቂት በኋላ የማህበረሰቡን ወጣት ወንዶች ልብ ለማሸነፍ ተጠቅማበታለች።

"ኤኬ-47 ጠመንጃ የእግር ኳስ ቡድኑን ቦታ ተክቶ ነበር።"

ወዲያውኑ ወጣት ወንዶቹ መሳሪያቸውን መጣል ብቻ ሳይሆን ሊጣሏቸው ይገባ ከነበሩት የጎሳ አባላት ልጆች ጋር መጫዎት ጀመሩ።

የፎቶው ባለመብት, Fatuma Abdulkadir Adan

የምስሉ መግለጫ,

ከመጀመሪያዎቹ የእግር ኳስ ውድድሮች አንደኛው ግጭት በነበረባቸው ማህበረሰቦች መካከል ይቅርታን ለማውረድ ያለመ ነበር

ባህላዊ አመለካከትን መጋፈጥ

ፋጡማ ፊቷን ወደ ልጃገረዶች ባዞረች ጊዜ ያለእድሜ ጋብቻን እና የሴት ልጅ ግርዛትን ጨምሮ ችግራቸውን ማሰወገድ ፈልጋ ነበር።

ዝምታውን መስበር የተሰኘው ዘዴዋ በአስር ዓመት ውስጥ ከ152 የኬንያ ማርሳቤት ክልል መንደሮች 1645 ልጃገረዶችን እግር ኳስ እንዲጫወቱ አስችሏል።

በተለይ ባህላዊ የቤተሰብ እና የጎሳ መዋቅር ማለት ህጻናት እና ሴቶች አብዛኛውን ጊዜ ድምጽ አልባ ማድረግ በሚሆንበት አካባቢ ልጆች ለራሳቸው ዘብ እንዲቆሙ አቅማቸውን ማጎልበት የተልዕኮዋ ዋነኛው ክፍል ነው።

"በቀደመው ጊዜ የ13 ወይም የ12 ዓመት ልጃገረድን መዳር ምን ችግር አልነበረውም" በማለት የምተገልጸው ፋጡማ "ዛሬ የ13 ዓመት ልጅ ብታገባ አብረዋት በአንድ ክፍል ውስጥ የሚማሩ ሴቶች ይቃወማሉ። ወንዶች ልጆችም እንዲሁ" ይላል።

ምንም እንኳ የሴት ልጅ ግርዛትም ሆነ ያለ እድሜ ጋብቻ በኬንያ ህገ-ወጥ ቢሆኑም የአካባቢው ባህል ጠንካራና በቀላሉ የማይቀየሩ ናቸው። ፋጡማም እነዚህን ድርጊቶች ተቃርና ለመከራከርም ሆነ አብራቸው ለመስራት መጠንከር ነበረባት።

የተገበረችው አካባቢያዊ ዘዴም ለዚህ ጠቅሟታል።

እግር ኳስ መጫወት ለሚፈልጉ ልጃገረዶች የሚሆን በቂ የስፖርት ትጥቅ እንዴት ማሰፋት እንዳለባት ኢማሞች ካማከረች በኋላ፤ አሁን ሆዲ የእስልምና ትምህርት ቤት ውስጥ የልጃገረዶች ቡድን አቋቁሟል። "በህይወት ኖሬ ይህ ሲሆን ማየቴን እስካሁን ማመን አልቻልኩም" ትላለች።

የምስሉ መግለጫ,

ውድድሩ በ2008 ሲጀመር ለልጃገረዶች እግር ኳስ መጫወት በራሱ በሰሜን ኬንያ ነውር ነበር

አንድ ልጃገረድ በአንድ ጊዜ

የፋጡማ ሥራ በእያንዳንዳቸው ተሳታፊ ሴቶች ህይወት ላይ እየተጫወተው ያለውን አውንታዊ ውጤት መመልከት የተከተለችውን ፈጠራ የተሞላበት ዘዴ ስኬታማነትን ያሳያል።

የ14 ዓመቷ ፋጡማ ጉፉ የትምህርት ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ናት። ድሃ በሆነ ቤተሰብ ውስጥ ብቸኛ ሴት ልጅ ሆና በእናቷ እጅ ያደገችው ፋጡማ እንደምትለው "እግር ኳስ ህይወቷን ቀይሮታል።"

"በመጀመሪያ በጣም ዓይን አፋር ነበርኩ" ትላለች። "ነገር ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እግር ኳስ ቀየረኝ። ለበርካታ ዓመታት ወላጆች ልጃገረዶች እግር ኳስ እንዲጫወቱ አይደግፉም ነበር። ወደፊት ግን እኔ እናት ስሆን ልጃገረዶች እግርኳስ እንዲጫወቱ መደገፍ እፈልጋለሁ።"

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ወ/ሮ ካሜ ኮቶ እንደሚሉት እሷ በክፍል ውስጥ በአብዛኛው ለአንደበተ ርቱዕ ወንዶች ከሚተወው ከምርጥ አምስቶች ውስጥም ናት። "በእግር ኳስ መሳተፍ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በትምህርቷም ሆነ በአመራር በኩል ያላትን ክህሎት ማሳየት ችላለች'' ይላሉ።

"ይሄ ሁሉ የተቻለው በእግር ኳስ ነው" የምትለው ፋጡማ፤ "ልጃገረዶች ግፊት ማድረግ እና በክፍል ውስጥም ሆነ በእግር ኳስ ሜዳ ላይ ውጤት ማስመዝገብ ይችላሉ።"

የምስሉ መግለጫ,

የ14 ዓመቷ ፋጡማ ጉፍራ እንደምትናገረው እግር ኳስ የህይወት ግቧን ለመለወጥ በራስ መተማመን አጎናጽፏታል