ሳኡዲ አረቢያ ከካናዳ ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት አቋረጠች

የቀድሞዋ ቀዳማይ እመቤት ሚሼል ኦባማ (በስተግራ) እና የቀድሞዋ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ከ ሳዋር ባዳዊ ጋር Image copyright AFP

ሳኡዲ አረቢያ ከካናዳ ጋር የነበራትን ማንኛውም ዓይነት አዲስ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ማቋረጧን አስታወቀች።

የዚህ ውሳኔ ምክንያቱ ካናዳ በሳኡዲ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷ እንደሆነ በሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ይፋ ተደርጓል።

በተከታታይ የቲውተር መግለጫ ሳኡዲ የካናዳን አምባሳደር እንዳባረረች ጨምራም የራሷን አምባሳደር እንደጠራች አስታውቃለች።

ህገወጡ የአረብ አገራት ጉዞ በአዲሱ አዋጅ ይገታል?

የቤት ሰራተኞችን ለመላክ ከኩዌት ጋር ድርድር እንደሚያስፈልግ ኢትዮጵያ አስታወቀች

የመን ''የዓለማችን አስከፊው ረሃብ'' ተጋርጦባታል

የሳኡዲ ርምጃ የተሰማው ካናዳ በሳኡዲ ውስጥ የበርካታ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እስር በእጅጉ እንዳሳሰባት ባሳወቀች ማግስት ነው።

ከታሰሩት መካከል ሳኡዲ-አሜሪካዊት የሴቶች መብት አራማጅ ሳማር ባዳዊ ትገኝበታለች።

ሳማር ወንዶች በበርካታ የአደባባይ እና የቤት ውስጥ ጉዳዮች ብቸኛ ውሳኔ ሰጪ የሚሆኑበትን አሰራር በመሞገት ትታወቃለች።

የሳኡዲ መንግሥት «ማናቸውም ዓይነት ጣልቃ ገብነቶችን አልቀበልም» በሚል ባቋረጠው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ የካናዳ መንግስት እስከ አሁን ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ