ጅቡቲ ያሉ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን እንግልት እየደረሰብን ነው አሉ

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጅቡቲ መጠለያ ጣብያ ውስጥ እረፍት እያደረጉ Image copyright SIMON MAINA

በጅቡቲ የሚኖሩ ስደተኛ ኢትዮጵያኖች እንግልትና በደል እየተፈፀመብን ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በጂቡቲ ነዋሪነቱን ያደረገው አቶ ሐምዛ ቶላና በርካታ ኢትዮጵያውያዊያን ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ለቢቢሲ ገልጿል።

የአምስት ልጆች እናት የሆኑት ወይዘሮ ፋጤ ሁሴን በበኩላቸው "ወደ ኢትዮጵያ የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው ህፃናት ይዘን መጥተን የምንገባበትና የምንወጣበት ጠፍቶናል" ብለዋል።

ጉዳት ደረሰባቸው ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች የህክምና አገልግሎት እያገኙ እንዳልሆነና በጅቡቲ የሚገኘው ኢምባሲ ምንም አይነት ድጋፍ እያደረገላቸው እንዳልሆነ ገልፀዋል።

ጅቡቲ በኢትዮጵያ ቴሌኮም ዘርፍ

አቶ አብዲ ስለተናገሩት ጉዳይ እንደማያውቅ ኢህአዴግ ገለፀ

"አብዲ ሞሃመድ ኡመር ስልጣን ለመልቀቅ በተደጋጋሚ ጠይቀው ነበር" አዲሱ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት

አቶ ሐምዛ እንደሚናገሩት "ነጋዴ ነበርኩ የንግድ ስራዬን ትቼ ሸሽቼ ነው ያለሁት ወደ ቤቴ መመለስ እፈራለሁ" ብለዋል።

እንዲህ አይነት ችግር እሁድ እለት መከሰቱን ሰኞ ጠዋትም ቀጠሎ እንደነበር ስደተኞቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ያናገራቸው ስደተኞች በርካታ ሰዎች ስለመጎዳታቸው ገልፀው የሞተ ሰው ስለመኖሩ ባያውቁም ከመካከላቸው አንዱ ግን ስለሞቱ ሰዎች መረጃ እንዳለው ተናግሯል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሻሜቦ ፊታሞ በስደተኞችና በነዋሪው መካከል በተፈጠረ ግጭት ቀላል ጉዳት መድረሱን አረጋግጠዋል።

ግጭቱ በምን እንደተነሳና ምን ያህሉ ጉዳት እንደደረሰባቸው እንደማያውቁም አስረድተዋል።

አምባሳደሩ እንዲህ አይነት ግጭት ከ15 ቀን በፊት እንደጀመረና በትናንትናው እለት ወደ 7 ሰዎችን ቀላል ጉዳት አጋጥሟቸው ሆስፒታል መላካቸውንም ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በድሬዳዋ ከተማ በተከሰተ ግጭት የ10 ሰዎች ህይወት ጠፋ

በጅግጅጋ ግጭት ሸሽተው የተሸሸጉ ሰዎች በከፋ ችግር ላይ ናቸው ተባለ

ኢምባሲው በፌስ ቡክ በሚለቀቁ "ሀሰተኛ ወሬዎች" ምክንያት እንደሚቸገር ተናግረው የኢትዮጵያውያንን ደህንነት ለመጠበቅ ከጅቡቲ መንግስት ጋር አብረው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

" ከፖሊስ ኮሚሽነር፣ ከሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከውጭ ጉዳይና ከጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ኢትዮጵያውያዊያን ጥቃት ሳይደርስባቸው ፖሊስ ደህንነታቸውን እንዴት እንደሚጠብቃቸው ተነጋግረናል። በትናንትናውም ላይ የጁቡቲ መንግስት መግለጫ እንዲያወጣ አድርገናል" ብለዋል።

አክለውም ጥቃቱን ያደረሱ አካላትም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

በጅቡቲ በስፋት ስለተገደሉ ኢትዮጵያውያን መረጃዎች እየወጡ መሆናቸውንና ቢቢሲም ያነጋገራቸው አካላት ይህንን እንዳረጋገጡ በተጠየቁበት ወቅት"ተገደለ ብለው ሪፖርት ያደርጋሉ በስፍራው ስንሄድ ምንም ነገር የለም" በማለት የወሬውን ሀሰተኝነት ተናግረዋል።

በተጨማሪም በጅቡቲ 1500 ሕገወጥ ስደተኞች በቁጥጥር ስር ውለው በተለያዩ እስርቤቶች እንደሚገኙ ገልፀዋል።

አይ ኦ ኤም በጅቡቲ መጠለያ ስለሌለው ኢምባሲው ከጠባብ እስር ቤቶች ወደ ግቢ ወዳላቸው ሰፋፊ እስር ቤቶች እንዲዛወሩ እየሰራ ነው ብለዋል።

"በስፍራው ጥቃት እንዳይደርስባቸው አድርገናል" ብለዋል።

በጅቡቲ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ፍላጎት አላቸው ሲሉም ተናግረዋል።

የጅቡቲ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት አብደላ አብዲ በትንትናው ዕለት ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ