በእንግሊዝ የጠጪዎች ቁጥር ማሽቆልቆል ኮማሪዎችን አሳስቧል

ጓደኛሞች ተቀምጠው ቢራ እየጠጡ Image copyright Getty Images

በጠጪ እጥረት ምክንያት የሚዘጉ መጠጥ ቤቶች ቁጥር በእንግሊዝ እያሻቀበ ነው።

ስለ ጠጪዎች እና መጠጥ ቤቶች መብት ከ40 ዓመታት በላይ የተጋው በምህፃረ ቃሉ ካምራ በሚል የሚጠራው ተቋም እንዳስታወቀው ፤በያዝነው የጎረጎስያዊያኑ ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ብቻ 476 መጠጥ ቤቶች ተዘግተዋል።

በ2017 የመጨረሻ ስድስት ወራት 13 መጠጥ ቤቶች መዘጋታቸውንም አስታውሷል።

ለአንድ ወር ከአልኮል መታቀብ የሚኖረው አስደናቂ ውጤት

የትራፊክ አደጋንና የባርቴንደር ሙያን ምን ያገናኛቸዋል?

አንድ ሚሊዮን ፈረንሳዊያን ማጨስ አቆሙ

ኢትዮጵያ ከዓለም ጥቂት አጫሾች ያሉባት አገር ናት

የተቋሙ ሊቀመንበር ጃኪ ፓርከር መጠጥ ቤቶች ውስጥ ተቀምጦ ለመጠጣት በእጅጉ ውድ በመሆኑ በርከት ያሉ ሰዎች በቤታቸው ውስጥ መጎንጨትን ስለመምረጣቸው ተናግረዋል።

በመጠጦች ላይ እና በመላ የንግድ ስራው ላይ በሚጣሉ ቀረጦች ለመጠጥ ሻጮች ፈተና መተውን የሚያነሳው ተቋሙ አንድ ብርጭቆ መጠጥ ከሚሸጥበት ዋጋ ሲሶው ቀረጥ ለመሸፈን እንደሚውል በማንሳት ይከራከራል።

እንደ ካምራ ከሆነ መጠጥ ቤቶች ለእንግሊዝ ኢኮኖሚ በየዓመቱ 23.1ቢሊየን ፖውንድ ያበረክታሉ።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ