ከወንጀልነት ወደቀዳሚ መዋቢያነት የተሸጋገረው የከንፈር ቀለም

ሴቶች ለ5,000 ዓመታት የከንፈር ቀለም ሲቀቡ ነበር Image copyright iStock

በመላው ዓለም 800 ሚሊየን ዶላር ለከንፈር ቀለም እንደሚፈስ ያውቃሉ? ለዘመናት እምባዛም ተቀባይነት ያልነበረው የከንፈር ቀለም (ሊፒስቲክ ሌላ ስሙ ነው) እንዴት ከፍተኛ የገንዘብ ፍሰት ያለበት መዋቢያ ሆነ ብሎ መጠየቁ አይቀርም። ታሪኩን ወደኋላ መለስ ብሎ ማየት ምላሽ ይሰጣል።

በእርግጥ በጥንታዊ ስልጣኔም ሴቶች ከንፈራቸውን ያቀልሙ ነበር። 5,000 ዘመናት ወደኋላ ብንጓዝ በሜሲፖታሚያ ጥቅም ላይ ይውል ነበር።

ዛሬ በሚታወቅበት ቅርጽ ባይሆንም ጥንታዊ ሳሞርያኖች የከንፈር ቀለምን እንደፈጠሩ ይነገርላቸዋል። ቀለሙን ከንፈር ላይ ብቻ ሳይሆን አይናቸውንም ለማስዋብ ይጠቀሙበት ነበር።

ለግብጻውያን ደግሞ የመደብ መገለጫ ነበር። የክሊዩፓትራ የከንፈር ቀለም ከጉንዳንና ሌሎችም ነፍሳት የተሰራ ነበር።

የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት

የሒጃብ ፋሽን ድዛይነሯ በማጭበርበር ወንጀል ለእስር ተዳረገች

"ሌቱም አይነጋልኝ" የተባለላት የውቤ በረሃ ትዝታዎች

ጠጣር የከንፈር ቀለም ወደ አለም የተሰራጨው ከመካከለኛውም ምስራቅ ተነስቶ ነው። የእንግሊዟ ንግስት ኤልዛቤት አንደኛ በ16ኛው ክፍለ ዘመን የከንፈር ቀለምን እውቅና አሳድገዋል።

በወቅቱ የከንፈር ቀለም ከቅጠላ ቅጠል ይዘጋጅ ነበር። በሀገረ ቻይና የታንግ ዘመነ መንግሥት ላይ የከንፈር ቀለም ለስለስ እንዲል፤ መዓዛ ያለው ቅባታማ ፈሳሽ ይታከልበት ጀመር።

Image copyright iStock
አጭር የምስል መግለጫ የክሊዩፓትራ የከንፈር ቀለም ከጉንዳንና ሌሎችም ነፍሳት የተሰራ ነበር

ቀጥሎ በመጡት ዘመናት የከንፈር ቀለምን የሚጠቀሙት ተዋንያን አልያም ሴተኛ አዳሪዎች ነበሩ። የከንፈር ቀለም ሲሰራ መርዛማ ኬሚካሎችን መጨመር የተጀመረውም በዚሁ ጊዜ ነው።

በአንዳንድ ማህበረሰቦች የከንፈር ቀለም የሚጠቀሙት ጠንቋዮች እንደሆኑ ስለሚታመን መዋቢያው ክልክል ነበር።

አሜሪካዊቷ ኤልዛቤት አርደን ለከንፈር ቀለምና ሌሎችም መዋቢያዎች ያለውን የተዛባ አመለካከት በመስበር የመዋዋቢያዎች ማምረቻ አቋቋመች።

እንደ አውሮፓውያኑ በ1912 ሴቶች በምርጫ እንዲሳተፉ በተካሄደ ሰልፍ ለተሳተፉ ሴቶች የከንፈር ቀለም መሸጧም አይዘነጋም።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ እንደ አውሮፓውያኑ በ1912 ሴቶች ያደረጉት ሰልፍ

የፈረንሳዩ ጉሬሊን የመዋቢያ ተቋም እንደ አውሮፓውያኑ በ1870 የከንፈር ቀለም መሸጥ የጀመረ ሲሆን ፈረንሳይኛ መጠሪያው ወደ አማርኛ ሲመለስ 'አትዘንጉኝ' የሚል ነው።

ለከንፈር ቀለም ማስቀመጫ የሚሆንና መጠነኛ ትቦ የሚመስል የብረት እቃ መዘጋጀት የጀመረውም በዛው ወቅት ነው።

እንደ አውሮፓውያኑ ከ1930ዎቹ ወዲህ የከንፈር ቀለም መወገዙ እየቀረለት መጣ። እውቅናው ከመጨመሩ የተነሳ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የነበረው ትርምስ እንኳን የከንፈር ቀለም ከመጠቀም አላስቆመም።

የከንፈር ቀለም መጠቀም አስፈላጊ ነው በተባለበት በዚያ ወቅት የከንፈር ቀለም ለመግዛት አቅም ያልነበራቸው ሴቶች ከሰል ወይም ቀይ ስር ይጠቀሙ ነበር።

ፒ ኤንድ ኤስ የተሰኘ ተቋም በሰራው ጥናት የከንፈር ቀለም እስከዛሬ ዕውቅ ሆኖ የዘለቀው በቀላሉ ሊሸመት የሚችል መዋቢያ በመሆኑ ነው።

በጥናቱ መሰረት የከንፈር ቀለም ገናናነት እየጨመረ ቢሄድ እንጂ አያሽቆለቁልም። የከተሜነት መስፋፋትና የኑሮ ዘዬ መለወጥ ለከንፈር ቀለም ታዋቂነት ምክንያት ከሆኑት መካከል ይጠቀሳሉ።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ