የአየር ንብረት ለውጥ-ምድር በአስፈሪ ሁኔታ እየሞቀች ነው

ሙቀት Image copyright Getty Images

ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት በቅርቡ መቋቋም የማንችለው ሙቀት ምድራችን ታስተናግዳለች፤ የምድር የውሃ አካላትም ከፍታቸው ይጨምራል። ምንም እንኳን የካርቦንዳይ ኦክሳይድ ልቀት መጠንን ለመቆጣጠር ሃገራት ስምምነት ላይ ቢደርሱም፤ የምድር ሙቀት ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መጥቷል።

ተመራማሪዎቹ የሰሩት ጥናት እንደሚያመላክተው የምድር ሙቀት በየአመቱ 2 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሚጨምር ከሆነ፤ የሁላችንም ስጋት የሆነው ከፍተኛ ሙቀትና ተያያዥ ችግሮች አይቀሬ ይመስላሉ።

አንድ አለማቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ የተመራማሪዎች ቡድን ያደረገው ጥናት ምድራችን የምትተማመንባቸው የተፈጥሮ ሃብቶቿ በቅርብ አስርት አመታት ውስጥ ለኑሮ አስቸጋሪ ወደሆነ መልክአ ምድርነት ይቀየራሉ ይላል።

የቡና ምርትና ጣዕም አደጋ ላይ ነው

የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ በአየር ፀባይ ይመራ ነበር

2017: ያልተጠበቁ ቁጥሮች የተመዘገቡበት ዓመት

በየዓመቱ የምድር ትላልቅ ጫካዎች፥ ባህሮችና አፈር ወደ ምድር ከባቢ አየር ሊቀላቀል የሚችል እስከ 4.5 ቢሊዮን ቶን የሚደርስ ካርቦንዳይ ኦክሳይድ መጠው ያስቀራሉ።

Image copyright Getty Images

ነገር ግን ምድራችን እያስተናገደችው ባለው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ተመጥጦ ቀርቶ የነበረው ካርቦንዳይኦክሳይድ ወደ ምድር ተመልሶ ከፍተኛ የአየር ንብረት ችግር ሊያስከትል ይችላል።

እ.አ.አ በ2015 የአለም መንግስታት የየሃገራቸው የሙቀት መጠን ከ2 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ለማድረግ ተስማምተው የነበረ ሲሆን፤ 2 ዲግሪ ሴልሺየስ ከደረሰ ግን ምድር የራሷን ምላሽ መስጠት ትጀምራለች የሚሉት የጥናቱ ተባባሪ ፕሮፌሰር ጆሃን ሮክስቶርም ናቸው።

እሳቸው እንደሚሉት በአሁኑ ሰአት የሰው ልጅ ነው የምድርን ሙቀትና የአየር ንብረት ለውጥ አየተቆጣጠረ ያለው። የምድር ሙቀት 2 ዲግሪ ሴልሺየስና ከዚያ በላይ ከሆነ ግን ምድር ከምቹ መኖሪያነት ወደ ጠላትነት ትቀየራለች።

የካርቦንዳይኦክሳይድ ከፍተኛ ክምችት አደጋዎችን ይጨምር ይሆን?

ኬንያዊያን ፍየል አርቢ ቤተሰቦች የአውሮፓ ህብረትን ሊከሱ ነው

የምድር ሙቀት ደግሞ በሚያስፈራ ሁኔታ በየአመቱ 0.17 ዲግሪ ሴልሺየስ እየጨመረ ነው። የከፋ ከሚባል አይነት አደጋ ሰዎችን እየጠበቁ ያሉት ደግሞ ትላልቅ ጫካዎች፤ እየቀለጠ የሚገኘው የአርክቲክ ባህር የበረዶ ግግር እና የውቂያኖሶች ቅዝቃዜ ናቸው።

Image copyright Getty Images

ይህን የማስቀረት እድል ይኖረን ይሆን?

በጥናቱ መሰረት የከፋ ጉዳት ከመድረሱ በፊት መከላከል ይቻላል። ነገር ግን ከእራሷ ከምድር ጋር ከፍተኛ የሆነ እርቅ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ይጠቁማል።

የሰውን ልጅ በከፍተኛ ሁኔታ እያሳሰቡ ያሉት የአየር ንብረት ለውጥና ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎች አጠቃላይ የምድርን ተፈጥሯዊ ሂደት እየጎዱት እንደሆነ ማስተዋል ቀላል ነው። ይህ ማለት ደግሞ ከምድራችን ጋር ያለንን ግንኙነት ካስተካከልን የወደፊቱን እጣ ፈንታ ማስተካከል እንችላለን ማለት ነው።

እንደ መፍትሄ ተብለው የተቀመጡት ደግሞ ለተለያዩ ግልጋሎቶች ብለን የምናቃጥላቸውን ነገሮች መቀነስ፤ ብዙ ዛፎችን መትከል፤ ጥቅጥቅ ደኖቻችንን መንከባበከብና ካርቦንዳይኦክሳይድን ከከባቢ አየር መምጠጥ የሚችሉ የፈጠራ ውጤቶችን ማበረታታት ይጠቀሱበታል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ