በየመን በሳዑዲ የሚመራው ቡድን ከአየር ላይ በሰነዘረው ጥቃት በአውቶቡስ ውስጥ የነበሩ 29 ህፃናት ተገደሉ

የሕክምና ባለሙያዎች በአየር ጥቃቱ የተጎዳ ህፃንን እያከሙ Image copyright Reuters

በሳዑዲ የሚመራው ቡድን የመን ላይ በሚያደርገው የአየር ጥቃት ቢያንስ 29 ህፃናት እንደተገደሉና 30 እንደቆሰሉ አለም አቀፉ የቀይመስቀል ድርጅት አስታወቀ።

ህፃናቱ በአውቶብስ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ነው ዳህያን በምትባል የገበያ ስፍራ ላይ የተመቱት።

በአማፂው ሁቲ የሚመራው የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የሆኑት ግለሰብ የሟቾች ቁጥር 43 የቆሰሉት ደግሞ 61 እንደሆነ ገልጿል።

"የምንመለሰው ያፈረሰን የምርጫ ቦርድ እራሱ ከፈረሰ ብቻ ነው'' ልደቱ አያሌው

ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ታጭተዋል?

ሰመጉ በወልዲያ እና አካባቢው የመብት ጥሰት ተፈጽሟል አለ

ከሁቲዎች ጋር በሚደረገው ጦርነት በየመን መንግስት የሚደገፈው ጥምረት ድርጊቱ "አግባብ" ነው ሲል ገልጾታል፤ ሆን ተብሎ ንፁኀን ላይ ያነጣጠረ አለመሆኑን ጨምሮ አስታውቋል።

የሰብዓዊ መብት ቡድኖች ግን የገበያ ስፍራዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና የመኖሪያ ስፍራዎች ሆን ተብለው ጥቃት ይደርስባቸዋል ሲሉ ይከሳሉ።

በዚህ መካከል በተባበሩት መንግስታት የየመን ልዩ ልዑክ የሆኑት የቀድሞው የእንግሊዝ መንግስት ዲፕሎማት፣ ማርቲን ግሪፊትሽ፣ በጦርነቱ ተፋላሚ የሆኑትን ወገኖች መስከረም ላይ ወደ ጄኔቫ በመጋበዝ ለስምምነት በሚረዱ ነጥቦች ላይ ለማወያየት አቅደዋል።

ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጦርነቱ ሳይፈታ ከቆየ "የአለም ህዝብ ልክ እንደሶሪያ የፈራረሰች የመንን በቅርብ አመት ውስጥ ይመለከታል።

"በየመን የሚደረገው ጦርነት በገፋ ቁጥር የበለጠ እየተወሳሰበ ይሄዳል። የበለጠ የአለም አቀፍ አካላት ፍላጎትና ውጥረት ይኖራል፤ አሁን ካለው በባሰ ሁኔታ ለመፍታትም አስቸጋሪ ይሆናል" ብለዋል።

የሁቲ ቃል አቀባይ የሆኑት መሃመድ አብዱል ሳላም ንፁኀን ዜጎች በተሰበሰቡበት ስፍራ ላይ የደረሰውን ጥቃት በሚመለከት ሲናገሩ "ለሰላማዊ ዜጎች ግድ የሌለው" በማለት ጥምረቱን ተችተዋል።

አለም አቀፉ የቀይመስቀል ኮሚቴ "በአለም አቀፍ የሰብዓዊ ህግ በጦርነት ወቅት ንፁኀን ከለላ ሊሰጣቸው ይገባል" ያለ ሲሆን የኖርዌይ የስደተኞች ጉባዔ ዋና ፀሀፊ ደግሞ "ማፈሪያ" የሆነ ተግባር በማለት "የህግ የበላይነትን በግድ የለሽነት አሽንቀጥሮ የጣለ" በማለት ድርጊቱን አውግዘዋል።

ሴቭ ዘ ችልድረን በበኩሉ ድርጊቱን "ዘግናኝ" ያለ ሲሆን ከዚህ ቀደም በንፁኀን ዜጎች ላይ የደረሱ ጥቃቶችን አካቶ በአፋጣኝ በገለልተኛ ወገን ጥናት እንዲደረግ አሳስቧል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ