የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኖርዌይን ከቻይና በዕቃ ጫኝ አውሮፕላን ሊያገናኝ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን Image copyright Anadolu Agency
አጭር የምስል መግለጫ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕቃ ማጓጓዣ አውሮፕላን ኦስሎና ጓዋንዡን ያገናኛል

በኢሲያ እያደገ የመጣውን የባሕር ውስጥ ምግብ ፍላጎት ለማርካት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአሳ ምርቶችን ከኖርዌይ ወደ ቻይና ማጓጓዝ ሊጀምር ነው።

ከመጪው መስከረም ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንግድ በቦይንግ 777 አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ ኖርዌይ መዲና ኦስሎ ካቀና በኋላ ወደ ቻይነዋ ጓዋንዡ ይጓዛል።

ዕቃ አጓጓዡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ በረራውን የሚያደርግ ሲሆን፤ ይህም ግዙፍ በሆነው ሰሜናዊ አውሮጳ ገበያ ውስጥ ድርሻ እንዲኖረው ያስችለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ

ወደ አሥመራ የሚደረገው በረራ ጀመረ

ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች

አየር መንገዱ ይህን በረራ ማድረጉ ለኖርዌይ የአሳ ምርት ኢንዱስትሪ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል ተብሎ የታመነበት ሲሆን፤ አዲሱ በረራ ኖርዌይን ለቻይና የአሳ ምርት ከሚልኩት አገራት ተመራጭ እንደሚያደርጋት የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከዚህ በተጨማሪም ለበርካቶች የሥራ ዕድልን መፍጠር ይችላል ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም ከኦስሎ ወደ ጉዋንዡ የሚጀምረው በረራ በዕቃ ማጓጓዝ ዘርፉ ላይ የተካነ አገልግሎት አቅራቢ ተቋም ስለመኾኔ ይመሰክርልኛል ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ በኦስሎ አውሮፕላን ማረፊያ አውደ ርዕይ በማዘጋጀት ዕቃ ላኪ እና ተቀባይ ድርጅቶች አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ እንደሚያበረታታ አስታውቋል።

ተያያዥ ርዕሶች