ለኑሮ ምቹ የሆኑት ቀዳሚዎቹ 10 ከተሞች ይፋ ሆኑ

ቬይና ምቹ ሀገር ተብላለች Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ቬይና ምቹ ከተማ ተብላለች

የኦስትሪያ መዲና ቬይና ቁጥር አንድ የዓለማችን ለኑሮ ምቹ ከተማ ተብላ ተሰይማለች። ቬይና ከዚህ ቀደም ቁጥር አንድ ለኑሮ ምቹ ከተማ ተብላ የነበረችው የአውስትራሊያዋ ሜልበርን ከተማን ተሽላ በመገኘት ነው ለዚህ ማዕረግ የበቃችው።

በኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት የዓለም ከተሞች የዳሰሳ ጥናት መሰረት፤ በአውሮፓ የሚገኝ ከተማ በዓለም ቁጥር አንድ ምቹ ከተማ ተብሎ ሲሰየም ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የዳሰሳ ጥናቱ በ140 ከተሞች ሲካሄድ የመጠነ ሀብትና ማህበራዊ መረጋጋት፣ የወንጀል መጠን፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶች እንዲሁም መሰል መስፈርቶችን ከግምት በማስገባት ነው።

በዳሰሳ ጥናቱ ውስጥ የእንግሊዟ ማንችስተር ከተማ 16 ደረጃዎችን በማሻሻል 35ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፤ ይህም በጥናቱ ከተካተቱ ከተሞች የተሻለ መሻሻል ያሳየች ከተማ አስብሏታል።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የአውስትራሊያዋ ሜልበርን ከተማ ላለፉት ሰባት ዓመታት በአንደኝነት ስትመራ ቆይታ ነበር

ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በዳሰሳ ጥናቱ ላይ የተካተቱት ሁሉም ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ በመሆን መሻሻል አሳይተዋል።

በዘንድሮው የዳሰሳ ጥናት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው የአውስትራሊያዋ ሜልበርን ከተማ ላለፉት ሰባት ዓመታት በአንደኝነት ስትመራ ቆይታ ነበር።

ሰሜን አሜሪካዊቷ ሃገር ካናዳና አውስትራሊያ እያንዳንዳቸው ለኑሮ ምቹ የሆኑ ሶስት ከተሞችን አስመርጠዋል።

በምስራቅ ሐረርጌ 37 ሰዎች ተገደሉ

በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ነው

ደቡብ ሱዳን ለበጎ ፍቃደኞች አስጊ ሃገር ተባለች

ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ ከተሞች በሚለው ዘርፍ ደግሞ ከቀዳሚዎቹ አስር ከተሞች አራቱ በአፍሪካ የሚገኙ ናቸው።

በጦርነት እየተመሰቃቀለች የምትገኘው የሶሪያዋ ደማስቆ ከተማ ፈጽሞ ለኑሮ የማትመች ተብላለች።

ዘ ኢኮኖሚስት እንደሚለው ከሆነ ''ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ ከተሞች'' በተባሉት ከተሞች ውስጥ ወንጀል፣ ማህበራዊ አለመረጋጋት፣ ሽብርተኝነት እና ጦርነት በስፋት ይስተዋላሉ ።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ደማስቆ በዓለም የማትመቸው ከተማ ተብላለች

የ2018 አስሩ ለኑሮ ምቹ የሆኑት ከተሞች

1. ቬይና፣ ኦስትሪያ

2. ሜልበርን፣ አውስትራሊያ

3. ኦሳካ፣ ጃፓን

4. ካልጋሪ፣ ካናዳ

5. ሲደኒ፣ አውስትራሊያ

6. ቫንኮቨር፣ ካናዳ

7. ቶኪዮ፣ ጃፓን

8. ቶሮንቶ፣ ካናዳ

9. ኮፐንሃገን፣ ዴንማርክ

10. አደሌይድ፣ አውስትራሊያ

የ2018 አስሩ ለኑሮ ምቹ ያልሆኑት ከተሞች ደረጃ

1. ደማስቆ፣ ሶሪያ

2. ዳካ፣ ባንግላዴሽ

3. ሌጎስ፣ ናይጄሪያ

4. ካራቺ፣ ፓኪስታን

5. ፖርት ሞሬስቤይ፣ ፓፓኦ ኒው ጊኒ

6. ሃራሬ፣ ዚምባብዌ

7. ትሪፖሊ፣ ሊቢያ

8. ዶኡላ፣ ካሜሮን

9. አልጀርስ፣ አልጄሪያ

10. ዳካር፣ ሴኔጋል

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ