ፌስቡክና ትዊተር ከሩሲያና ኢራና ዘመቻ ጋር የተገናኙ አካውንቶች ሊያግድ ነው

የፌስቡክና የትዊተር መለያ ምልክት Image copyright Reuters

ፌስቡክና ትዊተር ከኢራንና ከሩሲያ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉና ሃሰተኛ መረጃን የሚያሰራጩ በመቶዎች የሚቆጠሩ አካውንቶችን አግጃለሁ ሲሉ አስታውቀዋል።

ፌስቡክ ከወራቶች ጥናት በኋላ ኢራንና ሩሲያ ከሚያካሄዱት ዘመቻ ጋር ተያይዞ ሃሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ በርካታ አካውንቶችን ለይቻለሁ ሲል አስታውቆ ነበር። በዚህም መሰረት እስካሁን ከ650 የሚበልጡ የፌስቡክ ገፆች አሳሳች ሆነው ተገኝተዋል ሲሉ የፌስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ አስታውቀዋል።

'ሃሰተኛ ዜና '፡ የኢትዮጵያ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ስጋት?

ፌስቡክ በመረጃ ፍሰት ላይ ማሻሻያ ሊያደርግ ነው

ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መበርበሩን አመነ

ኩባንያው በመግለጫው ላይ እንዳለውም " እንደዚህ አይነት የቅጥፈት ባህሪ የሚታይባቸውን አካውንቶች ለማገድ ተገደናል። ምክንያቱም ሰዎች በሚያደርጉት የማህበራዊ ሚዲያ ግንኙነት እንዲተማመኑ ስለምንፈልግ ነው" ብሏል።

ትዊተር በበኩሉ ለጊዜው 284 አካውንቶች ከኢራን ጋር ግንኙነት ኖሯቸው በማግኘቱ ከመጠቀም አግዷቸዋል።

ይህ የሆነው ማይክሮሶፍት ኩባንያ ሩሲያ በአሜሪካ ወግ አጥባቂ ቡድኖች ላይ የምታደርገውን የመረጃ ምንተፋ አሰናክለዋል ካለ በኋላ ነው።

ምንም እንኳን ምርመራው አሁንም በሂደት ላይ ያለ ቢሆንም ዘመቻው በመካከለኛው ምስራቅ፣ ላቲን አሜሪካ፣ እንግሊዝና አሜሪካ የሚገኙና የተለያዩ በይነ መረብ አገልግሎት የሚጠቀሙ ሰዎች ላይም ተግባራዊ ይሆናል" ሲል የማህበራዊ ሚዲያ ኔትወርክ ጨምሮ ተናግሯል።

አካውንቶቹ ቁጥጥር የሚደረግባቸው እንዴት ነው?

የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች የመረጃ መረብ ደህነትን ጠንቅቀው ከሚያውቁና እሳት የላሰ ዓይን ካላቸው ድርጅቶች ጋር በጋራ ይሰራል።

ከድርጅቱ ጋር ባደረገው ስምምነትም የኢራንን ፕሮፖጋንዳ የሚያዛምቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው አካውንቶችን ለማወቅ ተችሏል።

ከአውሮፓውያኑ 2011 አንስቶ የነበሩት የተወሰኑት ዘመቻዎች ይዘታቸው በአብዛኛው ከመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ ጋር ግንኙነት የነበረው ነው ፤ ከዚህም ባሻገር በእንግሊዝና በአሜሪካ ያለውንም ፖለቲካ የተመለከተ ነበር።

ማይክሮ ሶፍት ኩባንያ በበኩሉ ከመረጃ ብርበራው ጀርባ መረጃ መንታፊዎች እንዳሉበት ተናግሯል።

ማይክሮ ሶፍት ወደ እርምጃ የገባው አሜሪካ 12 ሩሲያዊ የመረጃ በርባሪ ሊቆችን ሒላሪ ክሊንተንንና የዲሞክራቲክ ፓርቲ የሚጠቀሙበትን የኮምፒዩተር መረጃ እንዲመነትፉ መደራደሯን ተከትሎ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ