ኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ቅናሽ አደረገ

Image copyright Ethiotelecom

በአገልግሎት ጥራት ማነስ እና ከፍተኛ የአገልግሎት ከፍያ በመጠየቅ የሚታወቀው ኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ቅናሽ አደርጓል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በሰጡት መግለጫ፤ የስልክ ኢንተርኔት (ሙባይል ዳታ) አገልግሎት ላይ የ43 በመቶ ቅናሽ፣ የሃገር ውስጥ የድምፅ ጥሪ ላይ የ40 በመቶ ቅናሽ እንዲሁም በአጭር የሞባይል የፅሁፍ መልዕክት (SMS) ላይ የ43 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን ገልጸዋል።

ቅናሹ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ቅናሽ ከማድረጉ በተጨማሪ ካለፈው ዓመት ጀመሮ ሲያካሂድ የቆየውን የሞባይል ምዝገባ ማቆሙን ኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።

በኢትዮ ቴሌኮም ድረ-ገጽ ላይ በወጣው ዝርዝር መረጃ መሰረት፤ በደቂቃ 83 ሳንቲም ይከፈልበት የነበረው የስልክ ጥሪ አሁን 50 ሳንቲም ሆኗል።

1 ሜጋ ባይት 35 ሳንቲም ይከፈልበት ነበር ሲሆን አሁን የማስከፈለው ግን 20 ሳንቲም ብቻ ነው ብሏል ኢትዮ ቴሌኮም።

አንድ አጭር የጽሁፍ መልዕክት 35 ሳንቲም ያስከፍል የነበረ ሲሆን 20 ሳንቲም እንዲሆን ተደርጓል።

ለመኖሪያ ቤቶች ይሰጥ በነበረው አገልግሎት ላይ እስከ 1768 ብር የሚደርስ የ50 በመቶ ቅናሽ የተደረገ ሲሆን፤ ለድርጅቶች ይሰጥ በነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ደግሞ የ30 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል።

ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት?

ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በመበደል ከዓለም ቀዳሚ ሃገራት አንዷ ነች ተባለ

በሞባይልዎ የኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል?