ተጭበርብራ የተሞሸረችው ሴት አፋቱኝ እያለች ነው

የሙሽራ ልብስ የለበሰች ሴት Image copyright iStock

በሆንግ ኮንግ የምትኖረው የ21 ዓመቷ ሴት ለሥራ ቅጥር የተዘጋጀ ነው በተባለ የሰርግ ድግስ ላይ ሙሽራ ሆና እየተወነች እንደሆነ ነበር የምታውቀው። ጉዳዩ ሌላ ሆኖ የፈረመችው ፊርማ በቻይና ህጋዊ ሆኖ ባለትዳር ነሽ ተብላለች።

ሴትየዋ እነደምትለው የሰርግ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተሳተፈችው በአንድ ድርጅት ውስጥ የሰርግ አዘጋጅ ሆና ለመቀጠር የመጨረሻው ፈተና እንደ ሙሽራ መተወን እንዳለባት ከተነገራት በኋላ ነበር።

በስነ-ስርዓቱ ላይም እሷና እንደ ባል ሆኖ ይተውን የነበረው ባለቤቷ ህጋዊ ፊርማ ተፈራርመዋል። የሆነውን ሁሉ ያወቀችውም ወደ ሆንግ ስትመለስ እንደሆነ ታውቋል።

ወዲያው ለከተማው ፖሊስ ብታመለክትም ወንጀል መፈጸሙን እና ተገዳ የፈረመች መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ ስላልቻለች ጉዳዩ መፍትሄ ሊያገኝ አልቻለም።

ትዳር ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል

ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገችው ሴት ከሁለት ወራት በፊት በፌስቡክ በወጣ የስራ ማስታወቂያ ላይ ተመዝግባ ነበር። ስራውም ረዳት የሜክአፕ ባለሙያ ቢሆንም፤ ድርጅቱ ለሰርግ አዘጋጅነት እንድትወዳደር እንዳሳመኗት ገልጻለች።

ለስራው መመረጧ ከተነገራት በኋላም ለአንድ ሳምንት ስልጠና የወሰደች ሲሆን፤ በመጨረሻው ፈተናም በቻይናዋ ፉዞዉ ግዛት እንደ ሙሽራ ሆና አንድትተውን እንደተነገራት ትገልጻለች።

በየዋህነት ወደ ግዛቲቱ የመንግስት መስሪያ ቤት ሄዳ የፈረመችው የጋብቻ ወረቀትም ህጋዊ ሆኖ ተገኝቷል። ጉዳዩ እስከሚጣራና ያገባችው ሰው ማንነት እስከሚታወቅ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ ባለትዳር ሆና እንደምትቆይም ተነግሯታል።

የደሞዙን 100 እጥፍ በስህተት የተከፈለው ሰው

ሽጉጥ ይዘው ለመንቀሳቀስ የተገደዱት ከንቲባ

የሆንግ ኮንግ ፖሊስ እንደገለጸው በየዓመቱ ከ1000 በላይ ቻይናውያን ወደ ሆንግ ኮንግ የሚያስገባቸውን ህጋዊ ወረቀት ለማግኘት ከሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች ጋር የውሸት ጋብቻ ይፈጽማሉ።

የ21 ዓመቷ ወጣትም የዚህ ወንጀል ሰለባ ሳትሆን እንዳልቀረች ፖሊስ ገልጿል።

ተያያዥ ርዕሶች