ጀርመን በናሚቢያ በፈመጸችው የዘር ማጥፋት ወቅት የወሰደቻቸውን የራስ ቅሎችን መለሰች

የልኡካን ቡድኑ ስነስርአቱን ሲታደሙ Image copyright Reuters

ከ100 ዓመታት በፊት ናሚቢያ የጀርመን ቅኝ ግዛት በነበረችበት ወቅት በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል የተወሰዱ የናሚቢያውያን ቅሪተ አካላት ተመልሰዋል።

የናሚቢያ መንግስት የወከላቸው የልዑካን ቡድን አባላት በጀርመኗ ዋና ከተማ በርሊን በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተገኝተው የራስ ቅሎቹን ተረክበዋል። የራስ ቅሎቹና ሌሎች የአካል ክፍሎቹ ወደ ጀርመን የመጡት የአውሮፓውያንን የአእምሮ ልህቀት ለማረጋገጥ ይካሄድ ለነበር ምርምር እንዲረዳ ነበር።

ቀኝ ገዢዎቻቸውን የተቃወሙ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የሄሬሮ እና ናማ ብሄረሰብ ናሚቢያውያን ተገድለዋል። የልጅ ልጆቻቸው እስካሁንም ይፋዊ ይቅርታ ከጀርመን መንግስት እየጠበቁ ነው።

እ.አ.አ በ1904 የሄሬሮ እና ናማ ተወላጆች በግድ የተወሰደባቸውን መሬት ለማስመለስ ጥረት ማድረግ ሲጀምሩ ነበር የዘር ማጥፋቱ ትዕዛዝ የተላለፈው። ቁጥሩን በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም የሟቾች ቁጥር እስከ 100 ሺ ሊደርስ እንደሚችል ይገመታል።

ያለመከሰስ ለማን? እስከምን ድረስ?

ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አድማ ጀርባ

በመጨረሻም በህይወት የተረፉት የአካባቢው ተወላጆች ለኑሮ ወደማይመች የሃገሪቱ በረሃማ ክፍል እንዲሄዱ የተገደዱ ሲሆን፤ ወደ ድሮ መሬታቸው ለመመለስ የሞከሩት ደግሞ ይገደሉ አልያም የማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ይታሰሩ ነበር።

የዘር ማጥፋቱ ሲፈጸም ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑት የሄሬሮ እና ናማ ተወላጆች ተገድለዋል። በጀርመን በመቶዎች የሚቆጠሩ የናሚቢያውያን የራስ ቅሎች ቢኖሩም አሁን የተመለሱት ግን ሃያ አምስቱ ብቻ ናቸው።

የናሚቢያውያን ብቻ ሳይሆን እንደ ካሜሩን፤ ታንዛኒያ፤ ሩዋንዳ እና ቶጎ ባሉ የጀርመን ቅን ግዛት የነበሩ ሃገራትም ጭመር የራስ ቅሎች ይገኛሉ።

ጀርመን ከ100 ዓመታት በፊት ለፈጸመችው የዘር ማጽፋት ወንጀል ይቅርታ ለመጠየቅ እንዳሰበች እ.አ.አ በ2016 ብትገልጽም፤ በይቅርታ ሂደቱ ላይ ከናሚቢያ መንግስት ጋር እስካሁን እተደራደረች ነው።

አንዳንድ ናሚቢያውያን ጉዳዩን ኒውዮርክ ወደሚገኝ ፍርድ ቤት ወስደውታል። ጀርመን በበኩልዋ እስካሁን ድረስ የናሚቢያ ዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በእርዳታ መልክ መስጠቷን ትናገራለች።

ተጭበርብራ የተሞሸረችው ሴት አፋቱኝ እያለች ነው

ዕሮብ ዕለት በተከናወነው የራስ ቅሎቹን የመመለስ ስነ-ስርዓት ለሶስተኛ ጊዜ የተከናወነ ነው።

የተጎጂዎቹ የልጅ ልጆች አሁንም እየተሰራ ባለው ነገር ደስተኛ አይደሉም። የጀርመን መንግስት ይፋዊ ይቅርታ አለመጠየቁና እነሱ የድርድሩ አካል አለመሆናቸው ትክክል አይደለም እያሉ ነው።

የተመለሱት የራስ ቅሎች ወደ ናሚቢያ ተወስደው የት እንደሚቀበሩ እስከሚወሰን ድረስ በሃገሪቱ ብሄራዊ ሙዚየም እንደሚቀመጡ ተገልጿል።

ተያያዥ ርዕሶች