ወንዶች አዞ ለመምሰል ቆዳቸውን የሚበሱባት ሃገር

ቆዳው የተበሳ የአካባቢው ተወላጅ

በአለማችን ሁለተኛዋ ትልቅ ደሴት በሆነችው ፓፓ ኒው ጊኒ፤ 80 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች መኖሪያቸው ገጠራማ በሆኑት አካባቢዎች ነው። አብዛኛዎቹ ለሰለጠነው አለም ብዙም ቅርበት የላቸውም። በዚህ ዘመን ይኖራሉ ተብለው የማይታሰቡ ባህላዊ ስነ ስርአቶች አሁንም ድረስ በዚህች ደሴት ላይ ይስተዋላሉ።

በፓፓ ኒው ጊኒ ''የመንፈስ ቤቶች'' ተብለው የሚጠሩት የአምልኮ ቦታዎች በአብዛኛው ነዋሪ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ናቸው። በዚህ ቦታ የተለያዩ ሰዎች ነፍሳቸውን በተለያዩ የእንሰሳት መንፈስ የሚመሰሉላቸው ሲሆን፤ የአዞ መንፈስን የሚስተካከለው የለም።

እነዚህ የአምልኮ ቦታዎች በብዙ የእንስሳት ቅሪቶች የተሞሉ ሲሆን፤ ከአሳማ እስከ ፈረስ፤ ከእባብ እስከ ንስር አሞራ ቅሪቶች በግድግዳዎቹ ላይ ይሰቀላሉ። ነገር ግን ለዚህ አካባቢ ሰዎች እንደ አዞ ሃይል እና ብልሃትን ያጣመረ እንስሳ የለም።

ሻደይ፦ለሴቶች፣ በሴቶች ፌስቲቫል

የባለዳንቴሏ የክር ጫማዎች

ታዳጊ ወንዶች በእድሜ መብሰላቸውን ለማረጋገጥ ወደ እነዚህ የመንፈስ ቤቶች በመሄድ ጀርባቸው፣ ትከሻቸውና ደረታቸው ላይ ስለት ባላቸው ነገሮች ይበሳሉ። ምንም እንኳን ስነ ስርአቱ ከባድ ህመም ያለው ቢሆንም፤ ባህል ነውና ሁሉም የፓፓ ኒው ጊኒ ታዳጊዎች በጉጉትና በደስታ ያደርጉታል።

ለእነሱ አዞን መምሰል የጥንካሬያቸውና በእድሜ የመብሰላቸው ማሳያ ነው።

ታዳጊዎቹ ወደ መንፈስ ቤቶቹ የሚወሰዱት በአጎቶቻቸው ሲሆን፤ ቆዳቸውን የመብሳቱ ሂደት ከአንድ እስከ ሁለት ሰአት ሊፈጅ ይችላል። እንደውም ከዘመናዊ ፈጠራዎች መምጣት ጋር ተያይዞ የሚጠቀሟቸው ስለቶች እተሻሻሉ መጡ እንጂ፤ በድሮ ጊዜ የሚጠቀሙት ስል ቀርከሃ እንደነበር የአካባቢው ምክትል ተወካይ አሮን ማሊነጊ ይናገራሉ።

ታዳጊዎች ከህመሙ ብዛት አንዳንድ ጊዜ ራሳቸውን ስተው እንደሚወቀድቁም ተወካዩ ይናገራሉ። ቁስሉ ቶሎ እንዲድንና ሌላ ችግር እንዳይፈጥር በአካባቢው በብዛት ካለ ዛፍ የሚገኝ ዘይት ይደረግበታል።

ስነ ስርአቱ ያስፈለገው የታዳጊዎቹ እናቶች እነሱን ሲወልዱ ያፈሰሱትን ደም ለማስታወስና ከዚህ በኋላ የራሳቸውን ደም በማፍሰስ ትልቅ ሰው መሆናቸውን ለማሳየት ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ታዳጊዎች ስነ ስርአቱን ከጨረሱ በኋላ በመንፈስ ቤቶች ውስጥ ለወራት በመቀመጥ ከታላላቆቻቸው የህይወት መንገዶችንና እንደ አሳ ማጥመድ ያሉ ሌሎች አስፈላጊ እውቀቶችን ይማራሉ።

"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው"

የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት

ሃገሪቱን ቅኝ የገዛችው ጀርመን በ1885 አካባቢ ክርስትናን በፓፓ ኒው ጊኒ ካስተዋወቀች በኋላ ይህ ባህላዊ ስነ ስርአት ህልውናው ጥያቄ ውስጥ እየወደቀ መጥቷል። ነገር ግን የፓፓ ኒው ጊኒ ተወላጆች ባህላቸውን ለማስቀጠል እየተጣጣሩ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች