200 ዓመታትን ያስቆጠረው የብራዚል ሙዚየም የእሳት አደጋ ደረሰበት

በብራዚል መዲና ሪዮ ደጀኔሮ የሚገኘው ሙዚየሙ እድሜ ጠገብ ነው Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በብራዚል መዲና ሪዮ ደጀኔሮ የሚገኘው ሙዚየሙ እድሜ ጠገብ ነው

በብራዚል ብሔራዊ ሙዚየም ውስጥ የተነሳውን እሳት በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

በብራዚል መዲና ሪዮ ደጀኔሮ የሚገኘው ሙዚየሙ እድሜ ጠገብ ሲሆን የብራዚላውያን የታሪክ መገለጫም ነው። እሳቱ የተነሳበት ምክንያት እስካሁን አልታወቀም።

ሙዚየሙ 200ኛ ዓመቱን ያከበረው በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ነበር። በውስጡ ከ20 ሚሊየን በላይ ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን እሳቱ የተነሳው ትላንት ምሽት ላይ ነበር።

በአንድ ወቅት የፖርቹጋል ንጉሳውያን ቤተሰቦች መኖሪያ የነበረው ሙዚየሙ ውስጥ እሳቱ ከተነሳ በኋላ በመላው ህንጻው ተሰራጭቷል። በእሳቱ የደረሰው ጉዳት መጠን እስካሁን አልታወቀም።

«ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ»

ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት?

አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው"

የ2016ን ኦሎምፒክ ቢሊዮኖች አውጥታ ያስተናገደችው ሪዮ ደጀኔሮ በኢኮኖሚ ቀውስና በተቃውሞ እየተናጠች ትገኛለች።

አሁን ደግሞ የብራዚል ታሪክ ማህደር የሆነው ሙዚየም የእሳት አደጋ ተጨምሮባታል።

የብራዚል ፕሬዘዳንት ሚቼል ተሚር "ለብራዚላውያን አሳዛኝ ቀን ነው። የ200 ዓመታት ጥናት፣ እውቀትና ስራ አጥተናል" ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

ከሙዚየሙ ሰራተኞች አንዱ እንደተናገሩት የሙዚየሙ ውስጠኛ ክፍል ከእንጨት የተሰራ በመሆኑ በቀላሉ እሳቱ ሊቀጣጠል ይችላል።

ሙዚየሙ ውስጥ የብራዚልን ታሪክ ከሚያንጸባርቁ ስብስቦች በተጨማሪ የግብጽ ቅርሶችና ከ12,000 ዓመት በላይ የሆነው የሰው ቅሪተ አካል ይገኝበታል።

ሙዚየሙ እንደ አውሮፓውያኑ በ1818 የተሰራው የሳይንስ ጥናትና ምርምርን ለማበረታታት ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ