የሳምንቱ የጋሬዝ ክሩክስ ምርጥ ቡድን ውስጥ፡ ላካዜት፣ ካትካርት እና ሉካኩ ተካተዋል

ሩዊ ፓትሪሺዮ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ቶተንሃም በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ሲያስተናግድ ዋትፎርድ ደግሞ አራተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

ማንቸስትር ዩናይትድ ከሁለት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ ድል የተመለሰ ሲሆን፤ ዎልቭስም የመጀመሪያ ድሉን ዌስትሃም ላይ አስመዝገቧል። ቼልሲ እና ሊቨርፑል ደግሞ የማሸነፍ ጉዟቸው አስጠብቀዋል።

በዚህ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች እነማን የጋሬት ክሩክስ ምርጥ ቡድን ውስጥ ተካተቱ?

ግብ ጠባቂ - ሩ ፓትሪሲዮ

ፓትሪሲዮ: ዎልቭሶች ዌስትሃምን 1 ለ 0 ያሸነፉበት መንገድ አስገራሚ ነው።

ዌስትሃሞች ነጥብ ለማግኘት ያላደረጉት ሙከራ አልነበረም። እንደግብ ጠባቂው ሩዪ ፓትሪሲዮ ባይሆን ኖሮ የጨዋታው ውጤት ሌላ ይሆን ነበር።

ይህን ያውቃሉ? ፓትሪሲዮ 50 በመቶ ግብ የሚሆኑ ትልልቅ ዕድሎችን በዘንድሮው ዓመት ማዳን ችሏል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ተከላካዮች - ካይል ዎከር፣ ጆይ ጎሜዝ፣ ክሬግ ካትርት እና አንድሪው ሮበርትሰን

ካይል ዎከር: ምን ዓይነት ምርጥ ጎል ነው ኒውካስል ላይ ያስቆጠረው? ዎከር ለማንችስተር ሲቲ የመጀመሪያ ጎሉን በድንቅ ሁኔታ ነው በማስቆጠር የጀመረው።

ይህን ያውቃሉ? ዎከር ይህን ጎል ለማንቸስተር ሲቲ ያስቆጠረው ከ52 ጨዋታዎች በኋላ ነው።

ጆዬ ጎሜዝ: ትሬንት አሌክሳንደር- አርኖልድ እና አንድሪው ሮበርትስን የባለፈው ዓመት ግኝቶች ከሆኑ ጆዬል ጎሜዝ ደግሞ ዘንድሮ የተገኘ ተጫዋች ነው።

ይህ ተጫዋች ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን መጫወት አለበት። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ ቦቢ ሙር የተጠጋጋ ችሎታ ያለው ተጫዋች ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ይህን ያውቃሉ? ሊቨርፑል ከሌስተር ጋር በነበረው ጨዋታ ጎሜዝ ከየትኛውም ተጫዋች በልጦ ኳሶችን አጨናግፏል።

ክሬግ ካትርት: ስፐርሶች እንዴት በዋትፎርድ ተሸነፉ? የቆሙ ኳሶችን መከላከል የማይችል ዋንጫ አያነሳም።

ስፐርሶች የትሮይ ዴኒይን ቁርጠኝነት እና የክሬግ ካትካርትን በሳጥን ውስጥ ያላቸውን ሃይል አልነበራቸውም። አራት ተከታታይ ድል- ዋትፎርድ ውስጥ ምን እየተካሄደ ነው?

ይህን ያውቃሉ? ክሬግ ካትከርት ለዋትፎርድ ያስቆጠራቸው አምስቱም ጎሎች በሜዳቸው ቪካሬጅ ሮድ ላይ የተገኙ ናቸው።

አንድሪው ሮበርትሰን: ባለፈው ሳምንት ሙገሳዬን ለአሌክሳንደር- አርኖልድ አቅርቤ ነበር። በዚህ ሳምንት ሊቨርፑል ባስመዘገበው ድል ውስጥ የአንድሪው ሮበርትሰን ሚና ትልቅ ነበር።

የሊቨርፑልን ጠንካራ ተከላካይ መስመር ከፈጠሩት ተጫዋቾች መካከል ሮበርትሰን እና አሌክሳንደር-አርኖልድ ይገኙበታል።

ይህን ያውቃሉ? ጀምስ ሚልነር ብቻ ነው በተቃራኒ የግብ ክልል ከሮበርትሰን የበለጠ ኳስ ያቀበለው።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

አማካዮች - ራም ስተርሊንግ፣ ኤን ሃዛርድ እና ማርኮስ አሎንሶ

ም ስተርሊንግ: እግሊዛዊው ተጫዋች በልምምድ ቦታ ጠንክሮ በመስራት በተለይ ጎል ፊት ለፊት ያለውን አጨራረስ አሳድጓል።

እንግሊዛዊያን ተጫዋቾችን በብዛት ስለማፍራት የሚወራ ሲሆን፤ ጥሩ እንግሊዛዊያን አሰልጣኞች ቢኖሩ ብዙ ጥሩ እንግሊዛዊ ተጫዋቾች ሊኖሩ ይችሉ ነበር።

ይህን ያውቃሉ? ካለፈው የውድድር ዓመት ጀምሮ ሞሃመድ ሳላህ እና ሃሪ ኬን ብቻ ናቸው ብዙ ጎሎችን ከራሄም ስተርሊንግ በላይ ያስቆጠሩት።

ኤደን ሃዛርድ: ከቼልሲ ጠንካራ አጨዋወት በተጨማሪ የሃዛርድ ድንቅ መሆን ከበርንማውዝ ጋር የነበረውን ጨዋታ በቀላሉ የበላይ ሆነው እንዲያጠናቅዉ ረድቷቸዋል። ቼልሲ በአሁኑ ሰአት ከጆሴ ሞውሪንሆም ሆነ አንቶኒዮ ኮንቴ ጊዜ በተሻለ ለዓይን የሚስብ ቡድን ሆኗል።

ይህን ያውቃሉ? በዚህ ሳምንት ከየትኛውም ተጫዋች በበለጠ ሃዛርድ ብዙ የግብ ዕድሎችን ፈጥሯል።

ማርኮስ አሎንሶ: ለሶስተኛ ተከታታይ ሳምንት ማርኮስ አሎንሶ በሳምንቱ ምርጥ ቡድን ውስጥ ተካቷል። ስፔናዊው ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ እየተጫወተ ይገኛል። ቼልሲ ጨዋታውን ሲያሸንፍ አሎንሶ ደግሞ የድሉ ዋነኛ መሠረት ነበር።

ይህን ያውቃሉ? አሎንሶ በዘንድሮው ዓመት 12 የግብ ሙከራዎችን ያደረገ ሲሆን፤ ይህም ከየትኛውም የፕሪምር ሊጉ ተከላካይ የበለጠ ነው።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

አጥቂዎች - ሮሜሉ ሉካኩ፣ አሌክሳንደር ላካዜት፣ ሳዲዮ ማኔ

ሮሜሉ ሉካኩ: ማንቸስተር ዩናይትዶች ቤልጂየማዊው አጥቂ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች በርንሌዮችን ማሸነፍ ችለዋል። ከማርከስ ራሽፎርድ በቀይ ካርድ ከሜዳው መሰናበት ውጭ ከእግር ኳስ ስነምግባር ያፈነገጠ ነገር አላየሁም።

ይህን ያውቃሉ? ከመጀመሪያ ጨዋታው ወዲህ ሮሜሉ ሉካኩ ለማንቸስተር ዩናይትድ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር የመጀመሪያው ነው።

አሌክሳንደር ላካዜት: ኡናይ ኤምሬ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች አሌክሳንደር ላካዜትና ፒዬር-ኤመሪክ ኦባምያንግን በጋራ ቢያጫውቱ የተለየ ውጤት ሊያገኙ ይችሉ ነበር።

ሁለቱ ተጫዋቾች አንድ ላይ ሲጫወቱ ጥሩ መሆናቸውን ደግሞ በዚህ ሳምነት አስመስክረዋል።

ይህን ያውቃሉ? ላካዜት የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስት በገባባቸው አምስት የሊግ ጨዋታዎች ሰባት ጎሎች ላይ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ሳዲዮ ማኔ: ከሌስትር ጋር በነበረው ጨዋታ ለሊቨርፑል ድንቅ መሆን የሳዲዮ ማኔ ሚና ትልቅ ነበር። ባላፈው ዓመት የሞ ሳላህ የበለጠ መድመቅ እንጂ ሴኔጋላዊው ጥሩ የውድድር ዘመን አሳልፏል።

ጠንካራ እና አጥቂውን በሚደግፍ የተከላካይ መስመር ምን ማሳካት እንደሚቻል በመጨረሻም ቢሆን የርገን ክሎፕ ተረድተዋል። ይህን ለመረዳት ሶስት ዓመት ጠይቋል።

ይህን ያውቃሉ? ማኔ ከሌስተር ጋር ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች በአራት ጎሎች ላይ ሚና ነበረው።