ብራዚላዊው ፖለቲከኛ የምረጡኝ ቅስቀሳ እያደረጉ በስለት ተወጉ

የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በስለት ተወግተዋ

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty Images

የምስሉ መግለጫ,

የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በስለት ተወግተዋል

በብራዚል የፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ቀንደኛ ተፎካካሪ የሆኑት ጃይር ቦልሶኔሮ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በስለት ተወጉ። ቀኝ ዘመም ፖለቲከኛው የምረጡኝ ቅስቀሳ ያደርጉ የነበረው በደቡብ ምስራቃዊቷ ሚናስ ገሪያስ ግዛት ነበር።

ለምርጫ ቅስቀሳው ንግግራቸውን ሲጨርሱ ደጋፊዎቻቸው ትከሻቸው ላይ ተሸክመዋቸው ሳለ ነበር ያልተጠበቀው የሆነው።

በህዝብ ተከበው በስሜት ንግግር እያደረጉ ሳለ በነር ድንገተናው የስለት ጠጥቃት የተሰነዘረባቸው። አንጀታቸው ላይ የደረሰባቸውን ጉዳት ተከተወሎ ቀዶ ጥገና ያደረጉላቸው ሀኪሞች፤ ፖለቲከኛው በቅርቡ እንደሚያገግሙ ተናግረዋል።

የግዛቲቱ ፖሊስ በበኩሉ አዴሎ ኦቢሴፖ ደ ኦሊቬሪያ የተባለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ማዋሉን አስታውቋዋል።

የፖለቲከኛው ልጅ ፍላቪዮ አባቱ ስለደረሰባቸው ጉዳት "ብዙ ደም ፈሶታል፤ ሆስፒታል ስንደርስ ከሞት አፋፍ ላይ ነበር፤ አሁን እየተሻለው ነው፤ እባካችሁ ጸልዩለት" ሲል በትዊተር ገጹ ጽፏል።

የህክምና ባለሙያዎች እንዳሉት ጃይር ቦልሶኔሮ ቢያንስ ለአስር ቀናት በሆስፒታል መቆየት ይኖርባቸዋል።

የፖለቲከኛው ተቀናቃኞች ተግባሩን ያወገዙ ሲሆን፤ ፕሬዘዳንት ሚቼል ታሚር ድርጊቱ በዴሞክራሲያዊ ሀገር ውስጥ የማይጠበቅ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

አጥቂዎቹን በመቅጣት መቀጣጫ ማድረግ እንደሚያሻም ተመልክቷል።

አወዛጋቢ የሆኑት ፖለቲከኛ በሚሰጧቸው ዘረኛ አስተያየቶች በርካታ ብራዚላውያንን አስቀይመዋል። ሆኖም በሚቀጥለው ወር ምርጫ በርካታ ድምጽ እንደሚያገኙ ተነግሯል። ደጋፊዎቻቸው "ብራዚላዊው ትራምፕ" በሚል ቅጽል ስም ይጠሯቸዋል።

መሳሪያ የመታጠቅ መብትን መደገፍና ውርጃን መቃወም ከሚታወቁባቸው አቋሞች መካከል ይጠቀሳሉ።